2022-12-31 19:13:14
#በተውሒድ_ቀልድ_የለም
#በሽርክ_ጉዳይ_ከማንም_አንደራደርም
አላህ ሱብሀነሁወተአላ 18 መልእክተኛችን በተከታታይ በቁርአኑ
ካወደሰ
ካሞካሸ
ካላቀና
ገድላቸውን ከጠቀሰ በኋላ #የሽርክን አደገኝነት ሲገልፅ እንዲህ አላቸው
❞ وَلَوْ أَشْرَكُوا لَحَبِطَ عَنْهُمْ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ ❝
አል-ማኢዳ 88
《ቢያጋሩ ኖሮ ሲሰሩት የነበረ ስራ ሁሉ ይታበስ ነበር》
አስተውል ወዳጄ ነብያቶች የተላኩትና የደከሙትም ህዝቦቻቸው አላህን በብቸኝነት እንዲያመልኩት ለመሰድረግ ከመሆኑም ጋር ይህን ዛቻና ማስፈራሪያ ከተላለፈ
አብዱል ቃድር ጀይላኒ ድረሱልኝ ለሚሉት
ሰይድና ኸድር አስጥሉኝ
ንጉሶቹ በርሶ ተጠለልኩኝ
የአብሬት አባ ኧግዣናሁ ለሚሉት
ያረሱሉሏህ እጄን ይዘው ከጭንቅ ገላግሉኝ
የቦረናው ሸህዬ እርዱን አባብዬ
አባድር ፃም አያሳድር ለሚሉት
ለቆሌ ለጨሌ ለሚገብሩት
ለአድባር ለጅኑ ለቀብር ለሚያርዱት
መገን ነቢ ለሁሉ ቀላቢ በማለት ለሚቀጥፋት
የቃጥባሬ ሸኽን ሙጥኝ ብለው ለሚለምኑት
በየ አመቱ ቀብርን እንደጧፍ ለሚዞሩት
የአልከሶ ሸኽን ሀጃዬን አውጡ ለሚሉት
ሙታንን ይጠቅማሉ ለሚሉት
አምበሶ ራሄሎ በማለት ጅንን ለሚገዙት
አላህን ትተው ወደ ፍጡር ለሚዘነበሉት
አንይ ዳንይ በማለት ለተሸወዱት
ጌታ ሸኸዬ እያሉ መንገድ ለሳቱት
ወደ ጠንቋይ ቤት ለሚመላለሱት
ሁሉ ዛቻው እነሱንም ይመለከታል። ነብያቶች የተላኩበት ዋናው አላማ ተውሒድን ለማስተማር፣ ሽርክን ለመዋጋት ከመሆኑም ጋር እንዲሁም ከፍጡሮቹ ሁሉ አላህ ዘንድ የላቁና የከበሩ ከመሆናቸውም ጋር በሽርክ ጉዳይ ግን አልተደራደራቸውም ብታጋሩ ስራችሁን አበላሸው ነበር አላቸው
_የአይምሮ ባለቤት ለሆነ ሰው ይህ ትልቅ ትምህርት አለው
https://t.me/+LhY2Pp1VFwdiOGNk
88 views16:13