Get Mystery Box with random crypto!

ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና zehabesha

የቴሌግራም ቻናል አርማ zehabesha_newes — ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና zehabesha
የቴሌግራም ቻናል አርማ zehabesha_newes — ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና zehabesha
የሰርጥ አድራሻ: @zehabesha_newes
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.06K
የሰርጥ መግለጫ

#𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨𝐩𝐢𝐚𝐧_𝐧𝐞𝐰𝐬
ዘ-ሐበሻ የኢትዮጲያና ኢትዮጲያዊነትን ሁለንተና የሚቃኝ፣ የሀገርንና የህዝብን ጉዳዮች በብዙ መንገዶች ተደራሽ የሚያደርግ፣ በርካታ ዝግጅቶችና አቀራረቦች ያሉት የሚድያ ተቋም ነው።
#𝓩𝓮𝓱𝓪𝓫𝓮𝓼𝓱𝓪_𝓸𝓯𝓯𝓲𝓬𝓲𝓪𝓵

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-08-29 20:11:18 ከወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር የፀጥታ ምክርቤት በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ

እንደሚታወቀው ሀገራችን ኢትዮጵያ ፈተናዎችን በድልና በብቃት :በብልሃት ና በጥበብ አሸባሪውን ትህነግ/ህወሐት እና ታሪካዊ ጠላቶቻችንን እያሸነፈች የምትሻገር እንጂ በፈተናዎች ብዛት ተደናቅፈን የምንወድቅ ኢትዮጵያውያን አይደለንም። ምክንያቱም እኛ ኢትዮጵያውያን ለሰላም የሚዘረጉ እጆች ያለን እንጂ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚመጣ ማንኛውም የሰማይም ይሁን የምድር ሃይል ሽንፈትና ውርደት ተከናንቦ የሚመልስ ታሪክ ያለን ህዝቦች መሆናችንን የአደባባይ ሚስጢር ነው ።

ስለሆነም ኢትዮጵያዊነት የአሸናፊነት ምልክት በመሆኑ አሁናዊ የአሸባሪው ህወሃት ሦስተኛው የጦርነት ትንኮሳዎች የመጨረሻው የመሞቻው ጊዜ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን የድልና የትንሳኤ ጊዜ ነው። ስለዚህ ወራሪው ቡድን የተሰጠውን የሰላም አማራጮችን እያጨናገፈና እያፈረሰ በትግራይ ህዝብ ጫንቃ ላይ ተጣብቆ ደሙን እየመጠጠ እና በውር ድንብር ጉዞ ለመኖር አማራና አፋር ክልሎችን በመውረርና በማዋረድ ኢትዮጵያን ማፍረስ የሚል ሰይጣናዊ ግቡ ለማሳካት በህዝባችን ያልፈነቀለው የሴራ ድንጋይ: ያልፈፀመው ደባ የለም።

ይሁን እንጂ መላው ኢትዮጵያውያን ይህንን ወራሪ ቡድን ለአንዴና መጨረሻ እስከወዲያኛው እንዲያሸልብ ከወትሮው በተለየ ኢትዮጵያዊነታችንን አጠናክረን እንደ አንድ ሰው አስበን እንደ አንድ ቃል ተናግረን ለታሪካዊ ጠላቶቻችንን ውርደት አከናንበን በዲፕሎማሲው ተሰሚነቷ የገነነች በኢኮኖሚው ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆነች ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ መላው ህዝባችን ድካ የለሽ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ ታሪካዊ ጥሪ ስናቀርብለት ትልቅ ኩራት ይሰማናል ። ስለሆነም የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር የፀጥታ ምክርቤት በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ :-

የተከበራችሁ የፀጥታ ጥምር ሃይሎች :የፖለቲካ አመራሮችና መላው ህዝባችን ዛሬም እንደትላንቱ የማያዳግም እርምጃ በአሸባሪው ህወሃት እና በታሪካዊ ጠላቶቻችን የመረረ ጥላቻ ይዘን የመረረ ምት አሳርፈንና አሳፍረን በሁለንተናዊ የተከበረችና የተፈራች ሀገር ለመገንባት ትግላችን ከውስጥ ባንዳ እስከ ውጭ ባንዳ ያለውን ሀገር የማፍረስ ቅንጅት አፍርሰንና ደርምሰን በሁለንተናዊ የበለፀገች ኢትዬጲያ እውን ለማድረግ የሚከተሉትን ተግባራትን እንድንሰራ የፀጥታው ምክርቤት ያቀረበው ጉዳይ:-

1.ሁሉም ወረዳዎችና ከተሞች ከመንግስት ተሽከርካሪወች ውጭ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ከጧቱ12:ሰአት እስከ ምሽት 1:ሰአት ብቻ እንዲሆን የወሰነ መሆኑ ታውቆ ይህን ተላልፎ የተገኘ የተሽከርካሪ ባለ ንብረትና አሽከርካሪ ህጋዊ እርምጃ የሚሰድ ይሆናል!!

2.መላው የዞናችን ህዝብ ከዚህ በፊት በተደራጀበት የመንግስት አደረጃጀት መሠረት አካባቢውን ከሰር-ጎገብና ከውስጥ ባንዳ ያላለሰለሰ ትግል በማካሄግ
ድ ከጠላት አስተሳሰብና ተግባር የፀዳ ከባቢ እንድታደርጉ ጥሪያችን እናቀርባለን!!

3.ማንኛውም ሀገሩን እንዳትፈርስና በጠላት እንዳት ወረር የሚፈልግ ሰው ሁሉ(ተቆርቋሪ) ፀጉረ-ልውጥ ሲያገኝ በፍጥነት በአካቢው ለተሰማራው የፀጥታ መዋቅር የመጠቆም:የመያዝ:ወደ ህግ አካላት እንዲያስረክቡ ጥሪያችንን እናቀርባለን !!

4.በወረዳ የቀበሌ ከተሞችን ጨምሮ ባለሆቴሎች ባለ ምግብ ቤቶች ማንነቱ/አድራሻው/ ያልታወቀ ሲያጋጥም ለሚመለከተው የፀጥታ አካል እንድታስረክቡ
ከዚህ ውጭ በመሆን ማንነቱ ያልታወቀ; ያስጠጋ; ያሳደረ; ለጠላት ተባባሪ በሆነ አካል ላይ እርምጃ ይወሰዳል።

5.በተለይ በከተሞች አካባቢ ተከራይተውና አከራይተው የሚኖሩ ዜጎች በፍጥነት ተመዝግበው በአቅራቢያ ላለው የፀጥታ ተቋም ሪፖር እንድታደርጉ

6.በዞናችን ጠላት የሚኖርባቸው አጎራባች ወይም አዋሳኝ ቦታዎች ቀይ መስመር መሆናቸውን ታውቆ በእነዚህ አካባቢ የእርሻና እርባታ ያላቹሁ አልሚዎቻችን ከጧቱ 12:ሰአት እስከ ቀኑ 12:ሰአት ብቻ እንቅስቃሴ የምታደርጉ መሆኑን እያሳሰብን ለጉልበት ስራ የምትወስዷቸውን አካላት ማንነት በማረጋገጥ ለሚለከተው የፀጥታ አካል አስመዝግባቹሁ የምታሰሩ ሆኖ ይህን የተላለፈ ባለ ሃብትም ይሁን ወኪል በህግ ይጠየቃል ።

7.በዞናችን በሁሉም አካባቢዎች የሰው እንቅስቃሴ እስከ ምሸቱ 3:ሰአት ብቻ መሆኑ ታውቆ እነዚህን ክልከላዎችን በሚተላለፍ አካል ላይ ህግ እንዲያስከብር ለጸጥታ መዋቅሩ ትዛዝ ተሰጥቷል።

8.በሁሉም የዞናች አካባቢወች አዲስ መታወቂያ እንዳይሰጥ ተከልክሏል

9.በዞናችን ውስጥ ያለ የታጠቀ ሃይል በሙሉ ካለበት ወረዳ ከተማና ቀበሌ አስፈላጊውን ወታደራዊ ዝግጅት አድርጎ እንዲጠብቅ ታዟል

10.መላው የዞናችን ህዝብ ለፀጥታ ጥምር ሃይሎች የተለመደውን ደጀንነቱን በአስተማማኝነት እያጠናከረ እንዲሄድ ጥሪያችንን እናቀርባለን !!

በመጨረሻም በጠላት ላይ የመረረ ጥላቻ በመያዝ እና በመዋጋት ክብራችንን እና ነፃነታችንን እንጂ ከቀያችን ሸሽተንና ተፈናቅለን ህልውናችንን አናረጋግጥም እና መታገልና መደራጀት ብቻ ነው አማራጫችን!!

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር የፀጥታ ምክርቤት
1.1K views17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 17:03:26
የቀድሞው የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸዉ ሆስፒታል ገብተዉ ህክምና ሲከታተሉ ነበር፡፡

ሺንዞ አቤ በምዕራባዊ ጃፓን በሚገኝና ናራ በተባለ ከተማ ጎዳና ላይ ንግግር በማድረግ ላይ ሳሉ ከበስተጀርባቸው በተተኮሰ ሁለት ጥይት ደረታቸውን ተመተው ሆስፒታል የገቡ ቢሆንም ህይወታቸዉን ማትረፍ እንዳልተቻለ ነዉ የተገለጸዉ፡፡
475 views14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 17:03:26 የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ 1443ኛው ዒድ አል አድሃ /አረፋ/ በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላልፋል

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1443ኛው ዒድ አል አድሃ /አረፋ/ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን ሲል መልዕክቱን ያስተላልፏል። ይህንን ታላቅ በዓል ለየት የሚያደርገው የውስጥና የውጭ ጠላቶቻችን በስተመጨረሻ መሸነፋቸውና መጥፋታቸው አይቀሬ ቢሆንም ሀገር የማፍረስ ዓላማቸውን በጦርነት ማሳካት ሲሳናቸው በየቦታው ባደራጇቸውና ባስታጠቋቸው አሸባሪዎች አማካኝነት ንፁሀንን የጥቃት ኢላማ በማድረግ ላይ በሚገኙበት ወቅት በመሆኑ ነው።

ከዚህ ባሻገር ወቅቱ ጠላቶቻችን የውስጥ ባንዳዎችን ተጠቅመው የማይቀረውን ሦስተኛ ዙር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት እንዳይሳካ ለማድረግ የሞት ሽረት ጥረት እያደረጉ የሚገኙበት ጊዜ ነው።
በመሆኑም እኛም የጠላቶቻችንን እንቅስቃሴ በሚገባ ተገንዝበን በአንድነትና በጽናት በመቆም ጠላቶቻችን ላይ ብርቱ ክንዳችንን እያሳረፍን እንገኛለን፡፡

መላው የፌደራልና የክልል ፖሊስ ኃይላችን ከሌሎች የፀጥታና ደህንነት አካላት ጋር በመቀናጀት በዓሉ በመላው ሀገራችን በሰላም እንዲከበር በቂ ዝግጅት ያደረግን መሆኑን እያሳወቅን የእስልምና እምነት ተከታዮች በዓሉ በሰላም እንዲከበር የፀጥታና ደህንነት አካላት ጎን በመቆም የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ በድጋሜ ለእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለዒድ አል አድሃ /አረፋ/ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን እያልን በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲሆንልን መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን።

ዒድ ሙባረክ!

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ
ሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ
481 views14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 20:16:30
አይ ህወሓት :) ትናንት አብይ ዛፍ መትከል እንጂ አገር መምራት አልቻለም እያላቹ ስትቀልዱ ዛሬ ራሳቹ ዛፍ መትከል ጀመራችሁ?
683 views17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 14:56:05 "የኢትዮጵያ መንግስት ሊያደርገው የነበረውን የህዝብ ቆጠራ አብን ተቃውሟል !!" ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ!!

የበጀት ድልድል ቀመርን ለመስራት የሚያስችል የህዝብ ቆጠራ መካሄድ እንዳለበት ቢታመንም ሳይካሄድ መቅረቱ ተነግሯል።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የህዝብ ቆጠራ ባልተካሄደበት አግባብ የበጀት ድልድሉ መስራቱ ተገቢ አይደለም ሲል ላነሳው ጥያቄ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ምላሽ ሰጥተዋል።

በምላሻቸው ከእዚህ ቀደም ከሁለት ዓመታት በፊት መንግስት ሊያደርገው የነበረውን የህዝብ ቆጠራ እንዳይካሄድ አብኖች ተቃውማችኋል ሲሉ ተናግረዋል።
727 views11:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 14:56:05 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የንጹሃን ዜጎችን ሕይወት መቀጠፍ በተመለከተ

• እነዚህ ዜጎች ባልሰሩት ወንጀል ፣ በማያውቁት ጉዳይ በገዛ ሀገራቸው እና ቀያቸው ህይወታቸውን ለማሻሻል ደፋ ቀና ሲሉ ባልተገባ መንገድ ህይወታቸውን የሚቀጥፉ ገዳዮች አጥፊ ስብስቦች ያደረሱባቸው ጥቃት በእጅጉ የሚያሳዝን ከመሆኑ ባሻገር ህይወታቸውን ለመታደግ ባለመቻላችን እንደ ሀገር እንደ መንግስት እንደ ህዝብ ጥልቅ ሀዘን ይሰማናል።

• የንፁሃንን ደም በከንቱ የሚያፈሱ የትኛውም ሸኔም ይሁን ሌሎች የጥፋት ኃይሎች መጥፋታቸው የማይቀር ነው፤ ማሸበር ይችሉ ይሆናል እንጂ ከዋና ዓላማችን አያስቀሩንም፤

• መንግስት 24 ሰዓት የዜጎች ህይወት ለመታደግ ከፍተኛ ስራ እያከናወነ ይገኛል፤ ከዚህ ውስጥ ያመለጠ እንዳለ ሆኖ። በዚህ ውስጥ መስዋዕት የሚሆኑ የፀጥታ አካላት፣ ወታደሮች እና የክልል ልዩ ሀይሎች ህይወታቸውን ገብረው እየጠበቁ ነው።

• ሽብር አሁን ባለው ሁኔታ የጠቅላላ የዓለም ሁሉ ፈተና ነው። ለኢትዮጵያ ተለይቶ የተሰጠ አድርገን ማሰብ የለብንም።
686 views11:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 11:24:33 ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ ከነሀሴ ጀምሮ የቴሌኮም አገልግሎት መስጠት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ

ድርጅቱ የመጀመሪያ አገልግሎቱን በድሬዳዋ ከተማ እንደሚጀምር ገልጿል። እስከ ሚያዝያ 2015 ዓ.ም ድረስ ለ25 ከተሞች የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት እቅድ ማስቀመጡን አስታውቋል።
https://am.al-ain.com/article/new-telecom-service-to-start-in-ethiopia
686 views08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 11:24:32
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥቦች

በግፍ ህይወታቸውን ላጡ ለተገደሉ ንፁሀን ዜጎች የሚሰማኝን ጥልቅ ኃዘን መግለፅ እፈልጋለሁ፤ ባልሰሩት ወንጀል በማይመለከታቸው ጉዳይ ባልተገባ መንገድ ህይወታቸውን ከሚቀጥፉ ገዳዮች አጥፊ ስብስቦች በእጅጉ ዜጎቻችንን ህይወታቸውን መታደግ ባመቻላችን ጥልቅ ሃዘን ይሰማናል፤

የንጹሀንን ደም በከንቱ የሚያፈሱ የትኛውንም ስብስብ ለማጥፋት በጀመርነው እንቀጥላለን፤ የጥፋት ሃይሎች ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን መግፋት ማጎሳቆል ይችሉ እንደሆነ እንጂ ከዋናው ዓላማ አያሰናክሉንም፤ መንግስት 24 ሰአት የዜጎቹን ህይወት ለመታደግ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋል፤

በሚፈጠሩ ችግሮች ሁሉ ህይወታቸውን የሚገብሩ የጸታ አካላት እንዳሉ ማወቅ ያስፈልጋል፤ ይሄንን ዋጋ የሚከፍለው የተለየ ጥቅም አግኝቶ ክፍያ ተሰጥቶት አይደለም፣ በማይመች ሁኔታ ውስጥ ሆነው ነው የጸጥታ ሃይሎቻችን ዋጋ እየከፈሉ ያሉት፤ ለእነሱ ክብር መስጠት ይገባል፤

ሽብር የዓለም ሁሉ ፈተና ነው፤ በኢትዮጵ ውስጥ ብቻ የሚፈጸም አድርገን ማሰብ የለብንም፤ ሽብር መልኩ ብዙ ነው፤ በዓለም ላይ እንድ አሜሪካ ጠንካራ የደህንነት ተቋመ ያለው አገር የለም፤ ነገር ግን ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተገድለውባታል፤

አሸባሪዎችን ከዘር ጋር ብቻ ማያያዝ ተገቢ አይደለም፤ የአልሸባብ አብዛኛው ታጣቂ ሶማሌ ነው፤ በቡድኑ የሚገደለውም ሶማሌ ነው፤ ተጨማሪ ይዘን እንመለሳለን
636 views08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 11:24:32
የንጹሀን ግድያ የሚከሰተዉ በመንግስት ቸልታ ነዉ የሚባለዉ የተሳሳተ ነዉ - ጠ/ሚ አብይ አህመድ

6 ኛዉ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ አመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት በሚያካሂደው መደበኛ ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በተገኙበት ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያየ ይገኛል።

ከምክርቤቱ አባላትም ለ ጠ/ሚኒስትሩ በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። ከቀረቡት ጥያቄዎች ዉስጥም የጸጥታ ችግር ከመፈጠሩ በፊት አስቀድሞ መከላከል አይገባም ነበር ወይ? የንጹሀንስ ሞት መቼ ያቆማል? በቀጣይስ ችግሩ እንዳይከሰት መንግስት ምንድነዉ እቅዱ? የሚሉት ጥያቄዎች ይነሳሉ።

ጠ/ሚኒስትር አብይ በመልሳቸዉ የሽብር ቡድኖች የሚፈጽሟቸዉ ጥቃቶች በመንግስት ቸልተኝነት የሚፈጠር ነዉ የሚለዉ የተሳሳተ ነዉ ብለዋል። የሚፈጠሩ የጸጥታ ስጋቶችን ለማረጋጋትም የጸጥታ አካላት ዉድ ህይወታቸዉን እያጡበትም ነዉ ሲሉ ተናግረዋል።

ለአብነትም በቅርቡ በወለጋ ደምቢዶሎ እና ጊምቢ ፣ ጋምቤላ ፣ አሙሮ በተከታታይ በተፈጸመሙ ጥቃትቶች በርካታ የጸጥታ ሀይሎች ህወታቸዉን አጥተዉበታል ብለዋል። ደራሼ ላይም የወረዳ አመራሮችን እና የጸጥታ አካላትን ጨምሮ 80 የሚሆኑ ሰዎች ህይወት አልፏልም ማለታቸዉን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

ከዚህ በተጨማሪም ጠ/ሚ አብይ ከሚፈጸሙ ጥቃቶች የበርካታ ንጹሀንንም ህይወት መታደግ ችለናልም ብለዋል።
647 views08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 17:10:14 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ጠየቀ።
719 views14:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ