Get Mystery Box with random crypto!

ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና zehabesha

የቴሌግራም ቻናል አርማ zehabesha_newes — ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና zehabesha
የቴሌግራም ቻናል አርማ zehabesha_newes — ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና zehabesha
የሰርጥ አድራሻ: @zehabesha_newes
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.06K
የሰርጥ መግለጫ

#𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨𝐩𝐢𝐚𝐧_𝐧𝐞𝐰𝐬
ዘ-ሐበሻ የኢትዮጲያና ኢትዮጲያዊነትን ሁለንተና የሚቃኝ፣ የሀገርንና የህዝብን ጉዳዮች በብዙ መንገዶች ተደራሽ የሚያደርግ፣ በርካታ ዝግጅቶችና አቀራረቦች ያሉት የሚድያ ተቋም ነው።
#𝓩𝓮𝓱𝓪𝓫𝓮𝓼𝓱𝓪_𝓸𝓯𝓯𝓲𝓬𝓲𝓪𝓵

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-07-06 17:10:14 በቄለም ወለጋ የጅምላ ግድያው ከመፈፀሙ አስቀድሞ ለስብሰባ ትፈለጋለችሁ በሚል ተጠርተን ነበር ሲሉ የዓይን እማኞች ተናገሩ፡፡

አሻም ያነጋገረቻቸው ከጅምላ ግድያው ያመለጡ የኦሮሚያ ክልል፣ ቄለም ወለጋ፣ ለምለም ቀበሌ፣ መንደር 20 እና 21 ነዋሪዎች ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም ”ጭፍጨፋው ከመፈፀሙ አስቀድሞ ለስብሰባ ትፈለጋላችሁ” በሚል በማስገደድ ጭምር ከየቤታቸው እንደተወሰዱ ተናግረዋል፡፡

የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ባነጣጠረው የጅምላ ግድያ 72 ሰዎች ሰርዓተ-ቀብራቸው መፈፀሙን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ደግሞ በመቶዎች የሚቆጠሩት የቀብር ስነ ሰርዓታቸው ሲፈፀም ጭምር መመልከታቸውን ለአሻም ነግረዋታል፡፡ ”አሁንም ድረስ የት እንዳሉ፣ ይሞቱ/ይኑሩ የማይታወቁ የአማራ ብሔር ተወላጆች እንዳሉም” ነዋሪዎቹ ገልፀዋል፡፡
707 views14:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 17:10:13 አብን የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች በንፁሃን አማራዎች ላይ ለደረሰው ጥቃት ተባባሪ ናቸው ሲል ወቀሰ፡፡

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን ከሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል ወለጋ በአማራ ተወላጆች ላይ በደረሰው የዘር ማጥፋት ወንጀሎች ላይ ሁለቱም ምክር ቤቶች ተባባሪ ናቸው ብሎ እንደሚያምን ገልጿል።

ፖርቲው በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ፣ በአማራ ክልል ተወላጆች ላይ የተቀናጀ ፣ተከታታይና ስልታዊ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈፀም፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክርቤት ጥቃቱን በግልፅ አለማውገዛቸው የጥቃቱ ተባባሪ ናቸው ብዬ እንዳምን አድርጎኛል ብሏል፡፡

ሁለቱ ምክር ቤቶች በክልሉ ተወላጆች ላይ የደረሰውን ጥቃት በግልፅ አለማውገዛቸው በአማራ ህዝብ ላይ ያላቸውን ንቀት በግልፅ ያሳያል ብሏል ፖርቲው።

የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶክተር በለጠ ሞላ በመግለጫው ላይ እንዳሉት፣ በአማራ ንፁሃን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት መንግስት ካላስቆመ ሀገሪቱ ወደ እርስ በእርስ ግጭት ልትገባ እንደምትችል አሳስበዋል።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን በክልሉ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለማስቆም ወለጋና አካባቢው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር እንዲሆን ሲል የመፍትሔ ሀሳቡን አቅርቧል።
በተጨማሪም በአገር አቀፍ ደረጃ ብሔራዊ ሀዘን እንዲታወጅ የጠየቀው አብን፣ ከዚህ ባለፈ ግጭቱ ያቀጣጠሉት የኦነግ፣የኦፌኮና የክልሉ አመራሮች በህግ እንዲጠየቁ ሲልም አሳስቧል።
725 views14:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 17:10:13
‹‹ስለ ጠላት ብለን የጅብ አካሄድ ሄደናል፤ ሲሸልሉብን እና ሲፎክሩብንም ታግሰናል ››

አቶ ግርማ የሺጥላ በአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ
684 views14:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 19:57:48
በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሬ ተደረገ!

ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሀምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ጭማሬ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባስተላለፈው የነዳጅ ውጤቶች የዋጋ ግንባታና የትርፍ ህዳግ አሰራር እና የመሸጫ ዋጋ ማስተካከያና የታለመ ድጎማ አፈጻጸም ውሳኔ ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራ ሲከናወን መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በዚህም መሠረት ከነገ ጀምሮ

ቤንዚን----47 ነጥብ 83 በሊትር

ነጭ ናፍጣ ….49 ነጥብ 02 በሊትር

ኬሮሲን…49 ነጥብ 02 በሊትር

ቀላል ጥቁር ናፍጣ…53 ነጥብ 10 በሊትር

ከባድ ጥቁር ናፍጣ…52 ነጥብ 37 በሊትር

የአውሮፕላን ነዳጅ…98 ነጥብ 83 በሊትር እንደሚሸጥ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
800 viewsedited  16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 16:55:34 2 ተጨማሪ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎችን መውረሱን ቢሮው አስታወቀ
****************

ከመንግስት የተሰጠውን መመሪያና ደንብ በመጣስ ወደ ከተማ እንዳይገቡ የተደረጉ 2 ተጨማሪ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎችን በዛሬው እለት በፀጥታ ሀይሎችና በህብረተሰቡ ጥቆማ በመውረስ የጫኑት ነዳጅ በነዳጅ ማደያዎች በኩል እንዲከፋፈል ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ መስፍን አሰፋ ይህንን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ በዛሬው እለት 2 ተጨማሪ ነዳጅ የጫኑ ተደብቀው በፀጥታ ሀይሎችና በህብረተሰቡ ትብብር ተይዘው የጫኑት ከ80 ሺህ ሊትር በላይ የሚገመት ነዳጅም በማደያዎች በኩል መከፋፈሉን ገልፀዋል።
769 views13:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 16:55:34 በወገኖቻችን ላይ ተጨማሪ ጥቃትና ጭፍጨፋ እንዳይከሰት ሁሉንም ተጋላጭ ቀበሌዎች እና መንደሮችን በመለየት አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግላቸው እንዲሁም ነዋሪው ራሱን በተደራጀ መልኩ እንዲከላከል የሚሊሻና የኮሙኒቲ ፖሊሲንግ ስርዓት ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንደሚደረግ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለፁ።
አቶ ደመቀ መኮንን በቄሌም ወለጋ ለተጨፈጨፉ ንጹሃን ዜጎች የተሰማቸውን ሃዘን ገልፀዋል።
አቶ ደመቀ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በወለጋ አካባቢ አሁንም አሸባሪው የሸኔ ቡድን በንፁሃን ወገኖቻችን ላይ አሳዛኝ ጭፍጨፋ አካሂዷል ያሉ ሲሆን፥ ጥቃቱ የአማራ ብሄር ተወላጆችን ዒላማ ያደረገና ተጠቂዎችን ለመከላከል ሙከራ ባደረጉ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ጭምር ያነጣጠረ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ይህ ቡድን ህፃናትን፣ እናቶችን እና ደካማ አረጋውያንን ለይቶ ተደጋጋሚ ጥፋት በመፈፀም ሃገር የማፍረስ ግልፅ ተልዕኮ ያነገበ የተስፋ ቢሶች ጥርቅም መሆኑን በተግባር ማረጋገጡንም ተናግረዋል፡፡
አቶ ደመቀ እንዳሉት ፥ መንግስት በመላው ሃገሪቱ በተለይም ተደጋጋሚ ጥቃት በሚፈፀምባቸው አካባቢዎች ህግ ለማስከበር፣ ሰላም እና ፀጥታ ለማስፈን እንዲሁም ዜጎች የተረጋጋ ህይወት እንዲመሩ ለማስቻል ጠንካራ ርብርብ እያደረገ ቢሆንም፤ አሁንም በተለያዩ አካባቢዎች አሸባሪ ቡድኑ በንፁሃን ዜጎች ላይ ያነጣጠረ ጥፋት መፈፀሙን ቀጥሏል።
በማንኛውም መመዘኛ ድርጊቱ በፀረ-ኢትዮጵያ ሃይሎች ቅንብር እየተፈፀመ ያለ ኢ-ሰብዓዊ እና ዘግናኝ በመሆኑ፤ መንግስት ከአካባቢው ህዝብ ጋር በመተባበር የጀመረውን ህግ የማስከበር እንቅስቃሴ አጠናክሮ መቀጠሉንም ነው የገለጹት፡፡።
በወገኖቻችን ላይ ተጨማሪ ጥቃትና ጭፍጨፋ እንዳይከሰትም በሁሉም አካባቢዎች ተጋላጭ ቀበሌዎች እና መንደሮችን በመለየት አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግላቸው እንዲሁም ነዋሪው ራሱን በተደራጀ መልኩ እንዲከላከል የሚሊሻና የኮሙኒቲ ፖሊሲንግ ስርዓት ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንደሚደረግም አንስተዋል፡፡
በመጨረሻም ህብረታዊ የትግል እንቅስቃሴያችን እንዲከሽፍ ጠላት አስልቶ በርቀት የሚጠባበቀው የሴራ ውጤት በመሆኑ፤ በተደጋጋሚ በደረሰብን ጥፋት ሳንበረከክ አንድነታችንን አጥብቀን በፅናት እንድንጓዝ አደራ እያልኩ በተጎጂ ወገኖች የተሰማኝን ልባዊ ሀዘን እገልፃለሁ ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን።
768 views13:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 11:28:58 የሱዳኑ ጄኔራል አል ቡርሐን ሥልጣን ለመልቀቅ ፈቃደኛ መሆናቸውን ገለጹ!

የሱዳን ጦር ኃይል አገሪቱ ወደ ሲቪል አስተዳደር እንድትመለስ ለማድረግ ቦታውን እንደሚለቅ ወታደራዊው መሪ ጄኔራል አብዱል ፋታህ አልቡርሐን ተናገሩ።ጄነራሉ ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው በደረጉት ንግግር የአገሪቱ ጦር ኃይል ሱዳን ወደ ዴሞክራሲ ለምታደርገው ሽግግር እንቅፋት እንደማይሆንና ምርጫ እንዲደረግ ወስኖ እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።

ጄኔራል አል ቡርሐን ጨምረውም በአገሪቱ ያለውን ፖለቲካዊ ቀውስ ለማብቃት ከሲቪል ቡድኖች ጋር በሚደረገው ድርድር ላይ ጦር ሠራዊቱ የሚያደርገውን ተሳትፎ እንደሚያቋርጥ አሳውቀዋል።ነገር ግን አገሪቱ ውስጥ ምርጫ ስለሚደረግበት እንዲሁም ጦር ኃይሉ ሥልጣን ስለሚያስረክብበት ሂደት የጊዜ ሰሌዳ ምንም አላሉም።በሱዳን ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲመሰረት የሚጠይቁት ተቃዋሚ ሰልፈኞች ሠራዊቱ ከፖለቲካው እንዲወጣ በመጠየቅ ለወራት የዘለቀ ተቃውሞ ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል።

BBC
772 views08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 11:28:57 ጭፍጨፋውን ለማስቆም ከተፈለገ!

1) በተለይ ወለጋ አካባቢ የሚኖሩ አማራዎችን ለመጠበቅ ምቹ ነው። በርካታ ሕዝብ አንድ አካባቢ ይኖራል። ይህን ሕዝብ መጠበቅ ቀላል ነው። የኦሮሚያ ክልል ፀጥታ ድረሱልኝ ተብሎ አይደርስም። የፌደራል ፀጥታ ማስፈር ነው። ይህ ካልተቻለ ከአካባቢው ነዋሪ ሚሊሻ አሰልጥኖ ማስታጠቅ ብቸኛው መፍትሔ ነው። ይህ ካልተፈለገ ከአንድ ሰፈር ሰላሳና አርባ አማራ ሚሊሻ ከሚታጠቅ ሺህ ህፃናትና እናቶች ይታረዱ የሚል ውሳኔ ተወስኗል ማለት ነው።

2) በአማራ ሕዝብ ላይ አሁንም የሀሰት ትርክቱ ቀጥሏል። በይፋ፣ በሕግ ፀረ አማራ ትርክት የተባሉት ተለይተው መታገድ አለባቸው። ፀረ አማራ ቅስቀሳዎች ማስቀጣት አለባቸው። ማስወገዝ አለባቸው።

3) በኦሮሚያ ክልል መዋቅር ያሉ ኦነግን የሚደግፉ አሰራሮች ወንጀል ሆነው፣ እስካሁን አማራን ያስቀጡ ላይ ሕግ መከበር አለበት። ተጠያቂነት መኖር አለበት።

4) እስካሁን የተፈፀሙት ወንጀሎች ታምነው፣ በዝርዝር ለሕዝብ ተገልፀው፣ በመንግስት ደረጃ ይቅርታ ተጠይቆባቸው፣ ተጠቂዎች ተገቢው የሞራልና ቁሳዊ ካሳ ሊሰጣቸው ይገባል። ጭፍጨፋው የቀጠለው አማራን መግደል መንግስት በዘመቻ የሚያስተክለውን የመንገድ ዳር ችግር ከመርገጥ ያነሰ ወንጀል በመሆኑ ነው። ወንጀሉ ሲገለፅ፣ ይቅርታ ሲጠየቅ፣ ካሳ ሲሰጥ፣ ለአማራ ጥበቃ ሲደረግ፣ አማራን ማጥቃት የምር ወንጀል ሲሆን አማራን መግደል ወንጀል ነው ተብሎ ይታሰባል። በዚህ ወቅት የታጠቀው ብቻ ሳይሆን ሌላውም የአማራን አንገት መቅላት የዕለት ተዕለት ክንውን አድርጎ ለምዶታል። የአማራ ሞት ከመለመድ እንዲወጣ የተለየ እርምጃ ያስፈልጋል። ጌታቸዉ ሽፈራው
776 views08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 18:21:35
አርቲስ አብርሐም በላይነህ (ሻላየ )በነፃ ተለቀቀ!!

አርቲስት አብርሐም በላይነህ የእጮኛውን ከሶስተኛ ፎቅ ወድቃ መሞት ተከትሎ ባለፉት 50 ቀናት በእስር ቆይቶ በፍርድ ቤት ጉዳዩ ሲታይለት ቆይቷል።
ፖሊስ ከፍርድቤት የተሰጠውን በቂ ጊዜ ተጠቅሞ የእጮኛው ሞት ከእሱ ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር አለመኖሩን አረጋግጧል። በተለይም አርቲስቱ የእጮኛውን ሞት ተከትሎ ፍርድ ቤት ለፖሊስ የሰጠውን ተደጋጋሚ ቀጠሮ በመቀበል ሙሉ ምርመራ እንዲያደርግና እጮኛው እራሷን ከፍቅ መጣሏን እንዲረጋገጥ አድርጓል።

አርቲስት አብርሐም በላይነህ በዛሬው እለት ከእጮኛው ሞት ጋር የተገናኘ ምንም አይነት ጥፋት ስላተገኘበት በነፃ ተለቋል። ፍርድ ቤቱ በፖሊስ የተደረገውን ምርመራ ተመልክቶ ሙሉ በሙሉ የምርመራ መዝገቡን የዘጋ ሲሆን አርቲስት አብርሐም በላይነህም በነፃ እንዲለቀቅ በዛሬው እለት ወስኗልደ
ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተቀብሎ አርቲስቱን ዛራ ለቆታል።

በተለያዩ መንገዶች አርቱርቱን ስሙን ለማጥፋትና በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያጣ ለማድረግ ጉዳዩ በፖሊስ በተያዘበት ሁኔታ በርካታ ግለሰቦችና ሚዲያዎች ሀሰተኛ መረጃዎችን ሲያሰራጩ መቆየታቸው ይታወቃል።
824 views15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 17:58:44 Watch "Ethiopia: 3 የአሁን መረጃዎች Zehabesha ዘሃበሻ" on YouTube


741 views14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ