Get Mystery Box with random crypto!

ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና zehabesha

የቴሌግራም ቻናል አርማ zehabesha_newes — ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና zehabesha
የቴሌግራም ቻናል አርማ zehabesha_newes — ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና zehabesha
የሰርጥ አድራሻ: @zehabesha_newes
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.06K
የሰርጥ መግለጫ

#𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨𝐩𝐢𝐚𝐧_𝐧𝐞𝐰𝐬
ዘ-ሐበሻ የኢትዮጲያና ኢትዮጲያዊነትን ሁለንተና የሚቃኝ፣ የሀገርንና የህዝብን ጉዳዮች በብዙ መንገዶች ተደራሽ የሚያደርግ፣ በርካታ ዝግጅቶችና አቀራረቦች ያሉት የሚድያ ተቋም ነው።
#𝓩𝓮𝓱𝓪𝓫𝓮𝓼𝓱𝓪_𝓸𝓯𝓯𝓲𝓬𝓲𝓪𝓵

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-08-31 10:37:39 “ወልድያችን በጀግኖቿ ጥበቃ ሰላም አድራለች።” ወልዲያ ለመግባት አሰፍስፎ የነበረው የህወሓት ጉጀሌ ቡድን እንደ ቅጠል እረግፏል::
997 views07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:14:27 ታሪክ የማይረሳው ተጋድሎ!

ህወሓት ወያኔ በራያ ግንባር እስካሁን ባለው መረጃ ከሁለት መቶ ሺህ የማያንስ ኃይል ይዞ መጥቷል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ የምስራቅ አማራ ፋኖ እና ሚሊሻው የታገለው ከዚህ ኃይል ጋር ነው። ባለፈው ቆቦን፣ ትናንት ወልዲያን ለመያዝ የአሸባሪው ቡድን ብዙ ኃይል አልቆበታል። በህዝብ መአበል የጀመረው ጦርነት ለወገን ጦር ከፍተኛ ግፊት የፈጠረ ቢሆንም በጀግንነት ሲፋለም ከርሟል።

ፌስቡከኛው ሰግቶ የሸሸ ወገናችን ፎቶ ይለጥፋል እንጅ ብዙ የሚነገርለት ጀግናም ሞልቷል። ለሰራዊቱ ደጀን የሆኑ ወጣቶች፣ ምግብ እያበሰሉ የሚያቀርቡ እናቶች፣ ሰብሉን ትቶ ከሰራዊቱ ጎን የተሰለፈው አርሶ አደራችን ታሪክም በደማቅ ታሪክ የሚፃፍ ነው። እነዚህ ጀግኖች ለክብራችን ተዋድቀዋል። ሌላው ህዝባችን እንዳይጎዳ በርካታ ዋጋ ከፍለውልናል።

በአካል፣ በስልክ፣ በፌስቡክ የማውቃቸውን የራያ፣ የወልዲያ አካባቢ ወገኖች ደውዬ አነጋግሬያለሁ። ብርታታቸው የሚገርም ነው። ቤተሰቦቻቸው የተገደሉባቸው፣ የተዘረፉባቸው፣ ቤተሰቦቻቸው ይሙቱ ይኑሩ የማያውቁ ናቸው። ብዙ ነገሮችን እምቅ አድርገው ችለው መንፈሳቸውን ያበረቱ ጀግኖች ናቸው። የቤሰተቦቻቸውን ሕመምና ስጋት በሚገባ ያልተረዳናቸው፣ ነገር ግን በርካታ ፅኑ ወገኖች አሉን። አሉባልታና ወሬ፣ ሰበርና አሳዛኝ ዜና ከሚለጠፈው በላይ የእነዚህ ጀግኖቻችን ፅናት ብዙ ትርጉም ነበረው። ለእኛ ሲሉ በየጥሻው ትህነግ ጋር ተናንቀው መስዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖች፣ በአካባቢው ንቅንቅ ሳይል ለሰራዊቱ ደጀን የሆነው በርካታ ሕዝባችን ፅናት ሊያስተምረን፣ ላላወቀው ልናሳውቅ ሲገባ እንቶፈንቶው ሊያጨቃጭቀን አይገባም ነበር።

ጌታቸው ሽፈራው
774 views16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:10:27 ወያኔ አማራ ንቃ ካለ ነገር አለ ማለት ነው

አሸው አንበሳው
729 views16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:10:26
ከሱዳን ደብቀን ልናስገባ የነበረውን የጦር መሳሪያ የኢትዮጵያ አየር ሀይል አጋይቶብናል

He looks high
724 views16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:10:08 የተከፈተብንን ዘርፈ ብዙ ጦርነት ሁሉም ዜጋ በኅብረ ብሔራዊ አንድነት መመከት አለበት – ዶ/ር ለገሰ ቱሉ

የውስጥ ባንዳዎችና ታሪካዊ ጠላቶቻችን ተቀናጅተው የከፈቱብንን ዘርፈ ብዙ ጦርነት ሁሉም ዜጋ በኅብረ ብሔራዊ አንድነት መመከት አለበት ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ቱሉ ገለፁ፡፡

ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ ባንዳዎቹ በአፈቀላጤዎቻቸው በአንድ በኩል “ጦርነቱ አንተን አይመለከትም” እያሉ ይገዘታሉ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሂሳብ እናወራርደለን፣ ኢትዮጵያን ለማፍራስ ሲኦልም ቢሆን እንገባለን እንደሚሉ ጠቁመዋል።

“ከአማራ ህዝብ ጋር ፀብ የለንም እያሉ የአማራን ሴቶችና ሕጻናት ይደፍራሉ፣ ንብረቶቻቸውን ይዘርፋሉ፣ በአደባባይ ያዋርዳሉ፣ መሰረተ ልማቶቻቸውን ያወደማሉ” ነው ያሉት።

በተመሳሳይ የአፋር ህዝብ እየታገለም፣ ንብረቱ እየወደመበትም፣ ራሱ እየተራበም ቢሆን ለትግራይ ወንድሞቹ ሰብአዊ እርደታ ሳይስተጓጓል እንዲቀርብ እያደረገ ከቀዬው እንዲፈናቀል፣ የዘር ፍጅት እንዲደርስበት ማድረጋቸውን አስደርተዋል።

ኦሮሞው፣ ሶማሌው፣ ጉሙዙ ወዘተ ወዳጆቻችንና አጋሮቻችን ናቸው እያሉ ከቅጥረኛ ሽብርተኞችና ታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር ተቀናጅተው እርስ በርስ እንዲፋጁ፣ መሰረተ-ልማቶቻቸው እንድወደም፣ ሃብት ንብረታቸው እንዲዘረፍ ያደርጋሉ ብለዋል፡፡

ለመሆኑ ይህ እኩይ ድርጊታቸው የቅድስና ስራ ነው እንዴ? ሲሉ የጠየቁት ሚኒስትሩ፥ ሰብአዊ እርዳታን እንደመሳሪያ ተጠቅመው በኋላ ቀር የጦርነት ስልት የትግራይን ህጻናት፣ አዛውንቶችና ሴቶችን ሲማግዱ ምነው የኢትዮጵያ ወጣት ወደ ጦርነት አትግባ ብለው የራራው አንጀታቸው ለትግራይ ሲሆን ምነው ጠነከረ? ሲሉም ጠይቀዋል።

የህወሓት መሪዎች እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል እንዳለችው እንስሳ ምቾት እና ድሎታቸው አይጓደል እንጂ የትግራይ ህዝብ እና ወጣት እንደአቧራ ቢቦኑ፣ እንደጉም ቢተኑ፣ እንደ ቅጠል ቢረግፉ ለቅፅበትም ያህል አይገዳቸውም ብለዋል።

አሸባሪው ህወሓት ለትግራይ ህዝብ የሚያመጣው አንዳችም ተስፋ እንደሌለ ሚኒስተሩ ተናግረዋል።

በትግራይ ህዝብ ስም ተለምኖ የመጣን የዕርዳታ ስንዴ እና ነዳጅ በመስረቅ ለጦርነት መጠቀም የኖረበት የቡድኑ አስነዋሪ ገፅታ እንደሆነ በማወቅ የትግራይ ወጣት ቡድኑን በማውገዝ ሞት እና ስደት እንዲቆም የጋራ ድምፁን ሊያሰማ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል፡፡

ህዝባችን ሆይ ንቃ ያሉት ሚኒስትሩ፥ ሀገር በጦርነት ውስጥ ሆና ገለልተኛ ነኝ ብሎ መቀመጥ ከአንድ ሀገር ወዳድ ዜጋ እንደማይጠበቅ አመልክተዋል፡፡

ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሚችለው አቅም ኢትዮጵያ ላይ የተከፈተውን ፈርጀ ብዙ ጦርነት መመከት በማለት፥ በጦር ግንባር፤ በደጀንነት፤ በሳይበር ውጊያ እና በሌሎችም መንገዶች ኢትዮጵያ ላይ የተከፈተውን ጦርነት ለመመከት በጋራ መቆም የህልውና ግዴታ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

“ሀገር ሁሉም ነገር ናት! ሀገር መኖሪያ ናት፤ ሀገር እኛነታችን የተገነባባት እሴት ናት፤ ሀገር አብሮ በሚኖር በምንወደው በምናከብረው ህዝብ ትገለጻለች፤ ሀገር የልጅ ልጆቻችን የሚረከቧት የትናንት ታሪካችን፤ የዛሬ ሀብታችን እና የነገ ተስፋችን ናት” ብለዋል።

እኛነታችንን የቀረፀች፣ መኖሪያችን የሆነች እና የነገ ተስፋችንን የሰነቀች ሀገራችን እንድትጠፋ በተለያዩ መስኮች ጦርነት ተከፍቶባታል ያሉት ዶክተር ለገሰ፥ እኛነታችን የሆነችው ኢትዮጵያችን እንደ ጠላት ፍላጎት እንዳትጠፋ ሁላችንም ከመንግስት ጎን በመሆን የምንችለውን ሁሉ ማድረግ አለብን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሠራዊታችን ጀግንነት መገለጫው፤ ድል መዳረሻው፤ ህዝባዊነት ስንቁ የሆነ የኢትዮጵያ ጀግና፤ ፅኑ ዘብ መሆኑንም ገልፀዋል።

በማንኛውም ጊዜ እና ሁኔታ ለመከላከያ ሰራዊታችን ያለንን ክብር ያለስስት ማሳየት አለብን ያሉት ሚኒስትሩ፥ ከምንም በላይ ውድ የሆነውን ህይወቱን ለሚሰጠን ጀግናው ሰራዊታችን ደጀንነታችንን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ልናሳየው ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ሰራዊታችን የሀገሩን ረሀቧን እየተራበ፤ ጥሟን እየተጠማ፤ መከራዋን እየተሸከመ ኢትዮጵያን እየጠበቀ ያለ ብሔራዊ ክብራችን እና ሀብታችን ነው ብለዋል፡፡
699 views16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:10:08
ለአሸባሪው ህወሓት ሊተላለፍ የነበረ ከ1 ሚሊዮን በላይ ብር ተያዘ

ከስሃላ ወረዳ ወደ በየዳ ወረዳ በቅብብሎሽ ለሽብርተኛው ህወሓት ሊደርስ የነበረ 1 ሚሊዮን 253 ሺህ ብር መያዙን የተከዜ ክፍለ ጦር 3ኛ ሻለቃ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ጀጃው ፈረደ ገልጸዋል።

አሸባሪው ቡድን ሰርጎ ገቦችን በማዘጋጀት ገንዘብ እና ቁሳቁስ እንዲሻገርለት ቢፈልግም በአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና በኅብረተሰቡ ጥብቅ ክትትል ዕቅዱ ከሽፏል ብለዋል።

ቡድኑ ሊጠቀምበት የነበረ 600 ሊትር አረቂ፣ 10 ጣቃ አቡጀዲ፣ 15 ሺህ 9 የሶላር መብራት እና ከአምስት ኩንታል በላይ ጨው እና መሰል ቁሳቁስ ከእነተጠርጣሪዎቹ መያዙን የአማራ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።
 
649 views16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:10:07
ሰበር መረጃ ከወሎ ፋኖ
******
በጀኔራል ሀሰን ከረሙ ፣ ሻለቃ ሞገስ ከበደ ፣ ሻለቃ ደምሌ አራጋው ፣ ምስጋን ደስየ ፣ የወርቄው በላይ እያሱ እና ሙሃመድ ጎብየ ጥምረት የሚመራው የወሎ ፋኖ በትላንትናው እለት በአላ ውሃ ፣ ጎብየ እና ወርቄ አፋፍ ላይ ከክቡር መከላከያ ሰራዊት ኮማንዶው ጎንለጎን በመሆን የሚከተሉትን ድሎች አስመዝግቧል።

4 ብሬን ማርኳል
20 ክላሽንኮቭ ማርኳል
ከ40 በላይ ቦንቦችን ማርኳል
ብዛት ያላቸው ተተኳሽ የድሽቃ ሽልሽል ፣ የብሬን ፣ የስናይፐር ፣ እና ከክላሽ ጥይቆችን ማርኳል
በአንድ ግንባር ብቻ ከ105 ጁንታ አርግፏል
ብዛት ያላቸው ምርኮኞችን ለሰራዊቱ አስረክቧል

አዳሜ ፈርሶ ደሴ ገብቶ ሲያድር እንደ አይን ብሌሉ የሚሳሳላትን የየጁዋን ፈርጥ ወልድያ ከተማን ከልዩ ሃይሉ ፣ ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር በመሆን ለጠላት እሳት በመሆን ሲገርፈው አድሯል።

ዛሬም ሌላ የድል ውሏቸውን ማታ የማቀርብ ይሆናል

ኑ ከወሎ ፋኖ ጎን እንቁም
645 views16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:10:07
ደጀኑ ወልዲያ

ስለ ወልዲያ ሕዝብ ደግነትና ደጀንነት በኩራት እንድናገር ከሚያደርጉኝ ምክንያቶች አንዱ በጋሸና ግንባር ተሰልፎ የነበረ ወታደርን በተመለከተ የሰማሁት ታሪክ ነው። ያኔ ወልዲያ በጨለማ ውስጥ በነበረበችበት ጊዜ ወታደሩ ሁሉ ቀን ከሌት ያንን ደግና ጀግና ሕዝብ ለመታደግ ዕድል የሚያገኝበትን ቀን ይመኝ ነበር። የወልዲያን ሕዝብ እንግዳ ተቀባይነት የቀመሰው ሁሉም ወታደር "መቼ ነው ወልዲያን ነጻ እንድናወጣ ትዕዛዝ የሚሰጥን" እያለ ይጠይቅ ነበር። በሌላ ግንባር ያለው ሃይል ወደ ወልዲያ ሲቃረብ ከተማዋን ነጻ የማውጣት ዕድል ባለማግኘቱ የሚ'ቆጨው ወታደር ብዙ ነበር። ለወልዲያ ሕዝብ ብንሞትለት ያንሰዋል፣ ዘር ሳይለይ ሁሉንም ልጁ አድርጎ ተንከባክቦናል ይላሉ። በእርግጥ መከላከያው ወደ ወልዲያ ተመልሶ ሲገባ ቃለ-ምልልስ የተደረገለት ሰው እንባ እየተናነቀው ምንም የለን በባዶ እጅ እንዴት እንቀባላችሁ ብሎ የተናገረበት ድምጸት የነገሩን ሃቅነት የሚያረጋግጥ ነው።

ምን ለማለት ነው?

እርግጥ ነው። ኑሮ ተወዷል። እርግጥ ነው። ብዙ ሰው የሚያስተባብረው መሪ አጥቶ ተቸግሯል። እርግጥ ነው። ያልተጠበቀው የወያኔ ወረራ በርካታ ሰዎችን አስደናግጧል። ይሁንና ከመላው ኢትዮጵያ ተሰባስቦ በወሎ - ራያና የጁ ምድር አዲስ ታሪክ እየጻፈ ያለውን የሀገር መከላከያውን ልዩ ሃይላችንና ፋኖውን መደገፍ ያስፈልጋል። አሁን በሉ ተጠራሩና ያስለመዳችሁትን አድርጉ!
ወገን ተጠራራ! ደጀን ሁን!!
629 views16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:10:07
627 views16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:10:06
627 views16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ