Get Mystery Box with random crypto!

ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና zehabesha

የቴሌግራም ቻናል አርማ zehabesha_newes — ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና zehabesha
የቴሌግራም ቻናል አርማ zehabesha_newes — ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና zehabesha
የሰርጥ አድራሻ: @zehabesha_newes
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.06K
የሰርጥ መግለጫ

#𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨𝐩𝐢𝐚𝐧_𝐧𝐞𝐰𝐬
ዘ-ሐበሻ የኢትዮጲያና ኢትዮጲያዊነትን ሁለንተና የሚቃኝ፣ የሀገርንና የህዝብን ጉዳዮች በብዙ መንገዶች ተደራሽ የሚያደርግ፣ በርካታ ዝግጅቶችና አቀራረቦች ያሉት የሚድያ ተቋም ነው።
#𝓩𝓮𝓱𝓪𝓫𝓮𝓼𝓱𝓪_𝓸𝓯𝓯𝓲𝓬𝓲𝓪𝓵

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-08-30 14:02:40
920 views11:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 14:02:40 ዳር ላይ ያለች ትንሽ ከተማ ተያዘችም፣ ትልቅ ከተማ ተያዘም ክብራችን ተነክቷል። የቀበሌ፣ የወረዳ፣ የዞንና የክልል ከተማ ቢያዝ ከብዙ ፋይዳ አንፃር ሊታይ ይችላል። ክብር ግን የትኛም ላይ ተመሳሳይ ነው። ከራሱ ድንበር አንድ ኢንች ሲያልፍ ተወርረናል የሚል ስሜት መኖር አለበት። ትንሽ ከተማ ሲያዝ ምንም የማይመስለን፣ ትልቅ ሲያዝ እንቅልፍ የምናጣ መሆን የለብንም። ከሩቅ ያለቦታ ሲያዝ ግድ የለሽ ወደእኛ ሲቀርብ የምንሰጋ መሆን የለብንም።

ህወሓት ወያኔ የራሱን አልፎ ከመጣ ቆይቷል። አሁን የራሳችን ከተማ የምንቆጥርበት አካሄድ መቆም አለበት። ከወረረው እስካልወጣ ድረስ የትም ይሁን የት ህመሙ እኩል መሆን አለበት። የራሳችን ከተማ እየተወረረ ዛሬ ከዚህ ደርሷል፣ ነገ ከዚህ ይደርሳል እያልን መቁጠር ለውጥ አያመጣም። ከየትኛውም እንዲወጣ የሚያስችል ስራ መስራት አለብን።

የትም ደረሰ፣ የት እንደምናሸንፈው ደግሞ ጥርጥር የለውም። ባለፈው ገና ከራያ ጀምሮ ባለው ከህዝባችን ከፍተኛ ትግል ገጥሞታል። በየመንደሩ ሲያልፍ በጀግናው ህዝባችንና ሰራዊቱ በርካታ ኃይሉን እያጣ ነው ሸዋና ጎንደር ድረስ የደረሰው።

ሸዋ ደርሶ ተመትቶ ተመልሷል። ከደብረታቦር ቅርብ ርቀት ደርሶ ተመትቷል። ከደባርቅ ቅርብ ርቀት ደርሶ ተመትቷል። ተስፋ በቁረጡት ሳይሆን ተስፋ ባልቆረጡት ተሸንፏል። ወገናቸውን በጎነተሉት ሳይሆን በቻሉት ከወገናቸው ጋር በቆሙት አቅም ተመትቷል። ባቅማሙት ሳይሆን በቆረጡት ተመትቷል። ሰራዊቱ ሸሸ ብለው ባራገቡት ሳይሆን ያለበት ድረስ ሄደን እንገጥዋለን ባሉ ክንደ ብርቱዎች ተመትቷል። ከቻልን አሁን ባለበት አስቁመን ወደመጣበት ለመሸኘት መስራት ነው። ባይቻል ደግሞ የትም ይግባ የት መሸነፉ እንደማይቀር አምነን መስራት አለብን። ደብረብርሃን ይድረስ ጎንደር፣ ላሊበላ ይድረስ ደጀን እንደምናሸንፈው ሳንጠራጠር መስራት አለብን።

እነሱ ዋሻ ገብተው ወጥተዋል። መቀሌም ይሁን አዲግራት ሲያዝባቸው ሰራዊቱ ሸሸ ብለው ብዙ አጀንዳ አላደረጉትም። ሲይዙ እንጅ ሲያዝባቸው ከተማ አልቆጠሩም። ከማን ጋር እንደገጠምን ማወቅ አለብን። የራስን ከተማ መቁጠር መቆም አለበት።

ባለፈውም ዘንድሮም መወረር አልነበረብንም። ግን ሆኗል። በሆነ ጉዳይ ጉንጭ ማልፋት የለብንም። ባለፈው እንዳደረገው ዘንድሮም ከራያ ጀምሮ ሕዝባችን የቻለውን እያደረገ ነው። ትልቅ መስዋዕትነት እየከፈለ ነው። ወደፊት ሲያልፍ አጨብጭቦ አያሳልፈው፣ ባገኘው አጋጣሚ እየገጠመው ኃይሉን እያጣ ነው የሚያልፈው። የትም ይድረስ የት ተመትቶ ይመለሳል።

ባለፈውም ብለናል። ሆኗልም። እንዳትጠራጠሩ እናሸንፋለን!
921 views11:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 13:50:53 ሰልጥን፣
መክት፣
አጥቃ፣
አንክት፣ ለሃገርህ ድል ለኢትዮጵያውያን
903 views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 13:50:52 ቀይ መለዮ ልዩ ኮማንዶ.... ደርብ!
903 views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 12:22:26
ወያኔ ዛሬ ያወጣው መግለጫ ነው።

መግለጫው ለኢትዮጵያና ለኤርትራ ህዝብ የተላለፈ ጥሪ ሲሆን የመግለጫው አንኳር ይዘት ባጭሩ .......
"የኢትዮጵያና የኤርትራ ጦሮች በጋራ ትግራይን ለመውረር ዝግጅት መጨረሳቸውን ተረድቻለሁ ፤ በመሆኑም እኛ ከኢትዮጵያና ከኤርትራ ህዝብ ጋር ጠብ የለንም፤ጠባችን ከአቢይ እና ከአማራ ጋር ብቻ መሆኑን ተረድታችሁ ይሄንን እኩይ የጥፋት ድግስ እንድታወግዙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን" ይላል ።

https://t.me/zehabesha_newes
963 views09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 11:40:14 ወልድያ ኔትወርክና መብራት ከመጥፋቱ ውጭ! የወገን ጦር ባለበት ነው:: ህዝብ ድጋፍ ለጥምር ጦሩ ማድረግ አለበት!
https://t.me/zehabesha_newes
954 viewsedited  08:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 11:40:14 በጣም በርካታ ሰው ነው የሚደውልልኝ። ስልኩን ለማቃለል ያክል ይሄን ልበል። ወልዲያ ከተከፈተባት የተቀናጀ ሽብር በቀር እስካሁን በወገን እጅ እንዳለች ናት። የወገን ሀይል አዳሩን በቃሊም፣ በጎብየ፣ በአላ ሲዋጋ ነው ያደረው። አሁንም ወጥሮ ይዟል። ሽብር ፈጣሪወች ግን ደሴ ገብተዋል። አንዳንድ የብልጽግና አመራሮች፣ ፋኖወች፣ ጋዜጠኛ አይሏቸው አክቲቪስቶች የሽብር ፈጠራው ዋና ተዋናይ ናቸው። በተለይ ደግሞ የመከላከያን ሬንጀር ለብሰው የሚጓዙ ተከዳን፣ አለቃችን ጠፋን የሚሉ የጁንታው ሰርጎ ገቦች ዋና የሽብር ፈጠራው ተዋናይ ናቸው። ከትናንት ማታ ጀምሮ እየደወላችሁ ስለ ወልዲያ የምትጠይቁኝ ሰወች የነገርናችሁን ካላመናችሁ አትደውሉ። ጦርነት ነው፣ ሁኔታወች ይለዋወጣሉ አሁን ያለው ሁኔታ ይህን ይመስላል። ያወራሁት ነገር ከሠዐታት በኋላ ሊቀየር ይችላል። ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደሮች ትልቅ ሥራ እጃችሁ ላይ ወድቋል። በተለይ የተቀናጀ የፀጥታና ደህንነት ሥራው ፈታኝ ነው ትኩረት ስጡት።

Via Brook Abegaz
https://t.me/zehabesha_newes
987 viewsedited  08:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 10:45:39 ወልድያ
አሁን ስልክ ደውዬ ነበር መብራት አለ፣ስልክ ይሰራል። ህዝቡ ዛሬ ማክሰኞ ገበያ ስለሆነ ወደ ገበያ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው። የከባድ መሳሪያ ተኩስ ይሰማናል።
ተደናግጦ የወጣ ህዝብ ግን ብዙ ነው ብለውኛል።
ጥምር ጦሩ በሁሉም ቦታ እየተዋደቀ ነው። ይሄ አሁን መሬት ላይ ያለ መረጃ ነው።
977 views07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 10:45:23 ከተማ አስተዳደሩ ሕዝቡ ለጥምር ጦሩ እያደረገ ላለው የምግብ ዝግጅትና አቅርቦ ምስጋናውን አቅርቧል።
የከተማውን ሕዝብ አርአያነት በዙሪያው ያለው ሕዝብም በመጋራት የሎጅስቲክ አቅርቦቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አቅርቧል።
ወልድያ ከተማ ኮሙኒኬሽን
ነሐሴ 24 ቀን 2014 ዓ.ም
ወልድያ ከተማ ኮሙኒኬሽን
962 views07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 20:11:20
በቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ የቢሮ ኃላፊ የባንክ አካውንት፤ 8.4 ሚሊዮን ብር ገቢ ተደርጎ እንደነበር ፖሊስ አስታወቀ

ከኮንዶሚኒየም ዕጣ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ በእስር ላይ ለሚገኙት የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቢሮ ኃላፊ፤ 8.4 ሚሊዮን ብር በባንክ አካውንታቸው ገቢ እንደተደረገላቸው የፌደራል ፖሊስ ገለጸ። በዶ/ር ሙሉቀን ሀብቱ ስም ከተከፈቱ አራት የባንክ አካውንቶች፤ 6.4 ሚሊዮን ብሩ ወጪ መደረጉንም አስታውቋል።

የፌደራል ፖሊስ ይህን የገለጸው “በስልጣን አላግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል” ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በሚገኙት ዶ/ር ሙሉቀን ላይ ተጨማሪ ምርመራ ለማከናወን ዛሬ ሰኞ ለፍርድ ቤት ጥያቄ ባቀረበበት ወቅት ነው። ፖሊስ በተጠርጣሪው ስም በተከፈቱ የባንክ አካውንቶች የተደረጉ ዝውውሮችን መረጃ ያገኘው ከፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት መስሪያ ቤት መሆኑን የጊዜ ቀጠሮ መዝገቡን እየተመለከተ ለሚገኘው ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታውቋል።

ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2022/7897/
1.2K views17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ