Get Mystery Box with random crypto!

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥቦች በግፍ ህይወታቸው | ዘ-ሀበሻ-የዕለቱ-ዜና zehabesha

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥቦች

በግፍ ህይወታቸውን ላጡ ለተገደሉ ንፁሀን ዜጎች የሚሰማኝን ጥልቅ ኃዘን መግለፅ እፈልጋለሁ፤ ባልሰሩት ወንጀል በማይመለከታቸው ጉዳይ ባልተገባ መንገድ ህይወታቸውን ከሚቀጥፉ ገዳዮች አጥፊ ስብስቦች በእጅጉ ዜጎቻችንን ህይወታቸውን መታደግ ባመቻላችን ጥልቅ ሃዘን ይሰማናል፤

የንጹሀንን ደም በከንቱ የሚያፈሱ የትኛውንም ስብስብ ለማጥፋት በጀመርነው እንቀጥላለን፤ የጥፋት ሃይሎች ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን መግፋት ማጎሳቆል ይችሉ እንደሆነ እንጂ ከዋናው ዓላማ አያሰናክሉንም፤ መንግስት 24 ሰአት የዜጎቹን ህይወት ለመታደግ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋል፤

በሚፈጠሩ ችግሮች ሁሉ ህይወታቸውን የሚገብሩ የጸታ አካላት እንዳሉ ማወቅ ያስፈልጋል፤ ይሄንን ዋጋ የሚከፍለው የተለየ ጥቅም አግኝቶ ክፍያ ተሰጥቶት አይደለም፣ በማይመች ሁኔታ ውስጥ ሆነው ነው የጸጥታ ሃይሎቻችን ዋጋ እየከፈሉ ያሉት፤ ለእነሱ ክብር መስጠት ይገባል፤

ሽብር የዓለም ሁሉ ፈተና ነው፤ በኢትዮጵ ውስጥ ብቻ የሚፈጸም አድርገን ማሰብ የለብንም፤ ሽብር መልኩ ብዙ ነው፤ በዓለም ላይ እንድ አሜሪካ ጠንካራ የደህንነት ተቋመ ያለው አገር የለም፤ ነገር ግን ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተገድለውባታል፤

አሸባሪዎችን ከዘር ጋር ብቻ ማያያዝ ተገቢ አይደለም፤ የአልሸባብ አብዛኛው ታጣቂ ሶማሌ ነው፤ በቡድኑ የሚገደለውም ሶማሌ ነው፤ ተጨማሪ ይዘን እንመለሳለን