Get Mystery Box with random crypto!

ጋፋት ስቱዲዮ / Gafat Studio

የቴሌግራም ቻናል አርማ yenatnael_tube — ጋፋት ስቱዲዮ / Gafat Studio
የቴሌግራም ቻናል አርማ yenatnael_tube — ጋፋት ስቱዲዮ / Gafat Studio
የሰርጥ አድራሻ: @yenatnael_tube
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.85K
የሰርጥ መግለጫ

ታማኝ፣ ትኩስ፣ ወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃዎችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ!
ቸር አይለፈን 🙏
ክፉ አይንካን 🙏
🇪🇹 ኢትዮጵያ ሀገራችንን እግዚአብሔር ይጠብቅልን 🙏
ስለምትከታተሉን እናመሰግናለን!
👉ማስታወቂያ ማሰራት ለምትፈልጉ @Nati_Habesha ላይ ይፃፉልን

የቻናላችን ቤተሰብ ለመሆን ይህንን 👉 @Gafat_Studio #JOIN ያድርጉ!

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-04-26 23:32:00
ገብርኤል ማለት የአምላክ አገልጋይ ማለት ነው (ቅዱስ ገብርኤል) ለብስራት የሚላክ ከሠዎች ጋር ታላቅ ግንኙነት ያለው ተወዳጅና ፈጣን መልአክ ነው።
(ጌታችን እየሡስ ክርስቶስን) እንደምትወልድ እመቤታችንን ያበሠራት እና ለመጀመሪያ ግዜ ከሠዎች በፊት ያመሠገናት (ቅዱስ ገብርኤል ነው ሰለስቱ ደቂቅን ናቡከደነፆር በእሳት ላይ በጣላቸው ግዜ ፈጥኖ በመድረስ ከእሳት ያዳናቸው ቅዱስ ገብርኤል) ነው እንዲሁም (እየሉጣንና ቂርቆስ በፈላ ውሀ ውስጥ በተጣሉ ግዜ ውሀውን በማቀዝቀዝ ያዳናቸው ቅዱስ ገብርኤል) ነው። ቅዱስ ገብርኤል ከሚነደው እሳት ያወጣል የመለአኩ ረድኤት በረከቱ ጥበቃው አይለየን
(አሜን) [፫]

የተዋህዶ ልጆች በቴሌግራም መንፈሳዊ ትምህርቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቤተሰብ ይሁኑ!!!

ጠላትን በጋራ ከእግዚአብሔር ጋር ድል እናደርገው ዘንድ እናንተም የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉ
እምዬ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር አሜን
ኢትዮጵያ ሀገራችንንና ሀይማኖታችንን እግዚአብሔር ይጠብቅልን

Telegram Link

ቻ @YeNatnael_Tube
ና @YeNatnael_Tube
ል @YeNatnael_Tube
2.2K viewsÑäťňāêł Ŧãmïřű, 20:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-24 08:14:17 ጠ/ሚ/ር ዐቢይ መላው ጥቁር ሕዝብ ከኢትዮጵያ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዛሬ ጀምሮ ጦሩን ለመምራት ወደ ግንባር ለመሄድ መወሰናቸውንም ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ መላው ጥቁር ሕዝብ ከኢትዮጵያ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ትናንት ምሽት ባስተላለፉት መልዕክት፤ “ኢትዮጵያ አፍሪካዊ በሆነ መንገድ ከተነሣች፣ ተነሥታም ካሸነፈች፣ ከዚህ በኋላ ለማንም የማትመለስ ትሆናለች። ይሄን አፍሪካዊ መንገድ ለማደናቀፍ ሁሉንም ዓይነት የክፋት መሣሪያዎች አሰልፈዋል” ብለዋል።
“ከእንግዲህ እኔ መከላከያን በግንባር ሆኜ ለመምራት ከነገ ጅምሮ ወደ ትግሉ ሜዳ እዘምታለሁ”- ጠ/ሚ ዐቢይ
“ይህ ትግል የመላ ጥቁር ሕዝቦች ትግል ነው ያሉት” ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “ኢትዮጵያ አንበርክኮ ጥቁር ሕዝብን ለማሳፈርና አዲሱን የቅኝ ግዛት ቀንበር ለመጫን የሚደረግ ሤራ ነው” ሲሉም ገልፀዋል።

ጥቁር ሕዝቦች የራሳችን ታሪክ፣ ባህል፣ ማንነትና ክብር እንዳይኖረን ሆን ተብሎ የሚደረግ አንገት የማስደፋት ትግል ነው፤ ይህ በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተ ዘመቻ፣ ኢትዮጵያን በማንበርከክ ጥቁር ሕዝቦች የነጻነትና የአሸናፊነት አርአያ እንዳያገኙ የተከፈተ ዘመቻ መሆኑንም ገልፀዋል።
“ለጥቁር ሕዝብ ክብርና ልዕልና ስትሉ፣ በፓን አፍሪካ መንፈስ፣ ሁላችሁም ጥቁር ሕዝቦች፣ ከኢትዮጵያ ጋር እንድትቆሙ ጥሪ አቀርብላችኋለሁ” ብለዋል።
በኢትዮጵያ ላይ የተደቀነውን የሕልውና አደጋ ለመመከት አመራሩ ከፊት ተሰልፎ ሚናውን እንደሚወጣ የብልጽግና ፓርቲ ገለፀ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልእክታቸው አክለውም፤ ኢትዮጵያ መከራ ማለፍ ነባር ችሎታዋ እንደሆነ የገለጹ ሲሆን፤ አሁን ሀገሪቱ የገጠማትን መከራም “እናልፈዋለን፤ኢትዮጵያም ማሸነፏ አይቀርም፤ አሁን ኢትዮጵያን ለመታደግ የመጨረሻውን ፍልሚያ የምናደርግበት ጊዜ ላይ ነን” ብለዋል።
ጊዜው ሀገርን በመሥዋዕትነት መምራት የሚያስፈልግበት ጊዜ እንደሆነ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከእንግዲህ ”እኔ መከላከያን በግንባር ሆኜ ለመምራት ከነገ ጀምሮ ወደ ትግሉ ሜዳ እዘምታለሁ” ሲሉ በትናንትና ምሽት መልዕክታቸው ገልጸዋል።
በዚህም ታሪክ ከሚያደንቃቸው የኢትዮጵያ ልጆች አንዱ ለመሆን “የምታስቡ ሁሉ ለሀገራችሁ ስትሉ ዛሬውኑ ተነሡ፤ ግንባር ላይ እንገናኝ” ም ብለዋል።

ታማኝ፣ ትኩስ፣ ወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃዎችን ለመከታተል እንዲሁም ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ!

ድል ለአማራ ህዝብ
ድል ለእናት ሀገራችን
ሞት ለአሻባሪው እና ለመላው ሀገር ሻጮች

ቻ @YeNatnael_Tube
ና @YeNatnael_Tube
ል @YeNatnael_Tube

መረጃዎችን ለመለዋወጥ የቴሌግራም ግሩፑን ይቀላቀላሉ @AmharaDiscussion
6.6K viewsÑäťňāêł Ŧãmïřű, 05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-24 08:14:08
4.8K viewsÑäťňāêł Ŧãmïřű, 05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-23 19:51:05 ሀገር በተለያዩ ጊዜያት አደጋ ላይ በገባች ጊዜ መሪዎች ጦራቸውን ግንባር ሆነው በመምራት ወርቃማ ድል አስመዝግበዋል።
በአድዋ ጦርነት የአፄ ሚኒሊክን እና የእቴጌ ጣይቱን በጦር ግንባር የፈጸሙትን የአመራር ጥበብ ማንሳት ይቻላል። በአድዋ የነገስታቱን ግንባር መዝመት አነሳን እንጂ በየጊዜው የነገሱ ነገስታቶች እና የሀገር መሪዎች ጦራቸውን ግንባር ድረስ በመምራት ተዋግተዋል፤ አዋግተዋል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም (ዶክተር) ሀገሪቱ በውስጥ እና በውጭ ኀይሎች የተሰነዘረባትን የተቀናጀ ጥቃት በመቀልበስ ደማቅ ገድል እንድትጽፍ ግንባር ዘምተዋል።

ኮንስታብል ፋሲል አለልኝ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ግንባር መቀላቀል ከነበራቸው ወታደራዊ ወኔ በላይ እንዳነሳሳቸው ገልጸዋል። እንኳን ግንባር ለዘመተው ሠራዊት ለመዝመት ለተዘጋጁ ወጣቶችም ሞራል እና ወኔን ይፈጥራል። የደጀኑ ሕዝብም በግንባር ለሚዋደቀው ሠራዊት የሚያደርገውን እገዛ የበለጠ ያጠናክራል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ግንባር መዝመት የሠራዊቱን ወኔ የበለጠ እንዲነሳሳና በመንግሥት እና በሕዝብ መካከል የሚኖረውን መስተጋብር የበለጠ የሚያጠናክር ነው።

ሠራዊቱ ሀገርን ለማገልገል ከገባው ግዳጅ በላይ ወኔ ተላብሶ ለመፋለም ትልቅ ስሜት ፈጥሯል። አንድ የሀገር መሪ ግንባር ሲዘምት የደጀኑ ሕዝብም በገንዘቡ እና በስንቅ ዝግጅት ሥራ የበለጠ እገዛ እንዲያደርግ ያግዛል።

የጠቅላይ ሚንስትሩ ግንባር መቀላቀል ሠራዊቱ ግዳጁን የበለጠ እንዲወጣ ወኔ ፈጥሯል።
ታማኝ፣ ትኩስ፣ ወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃዎችን ለመከታተል እንዲሁም ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ!

አዲሱን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!!!
#Subscribe For [ Gafat Studio - ጋፋት ስቱዲዮ ] https://youtube.com/channel/UCoheB9PLWR2zx9ouBfKBrmQ
ድል ለአማራ ህዝብ
ድል ለእናት ሀገራችን
ሞት ለአሻባሪው እና ለመላው ሀገር ሻጮች

ቻ @YeNatnael_Tube
ና @YeNatnael_Tube
ል @YeNatnael_Tube

መረጃዎችን ለመለዋወጥ የቴሌግራም ግሩፑን ይቀላቀላሉ @AmharaDiscussion
5.3K viewsÑäťňāêł Ŧãmïřű, 16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-03 09:23:39 ኢትዮጵያ የጀግኖች ሀገር ናት፡፡ ልባም ልጆችዋ አጥር ሆነው የጋረዷት፣ ዋጋ ከፍለው ያደመቋት፣ ተቆጥሮ በማያልቅ መሥዋዕትነት ታፍራና ተከብራ የኖረች ሀገር ናት፡፡ የሩቁ ቢዘነጋን እንኳን፣ አምና ጥቅምት 24 ግፍ የተፈጸመባቸው ጀግኖቻችን ታሪክ ፈጽሞ የሚረሳ አይደለም፡፡ እያንዳንዳችን የጀግኖቹ ዕዳ አለብን፡፡ ዛሬ የቆምነው ለእኛ ሲሉ የግፍ ጽዋን በተጎነጩ ጀግኖቻችን አጥንት ላይ ነው፡፡ እነዚያ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጆች “ከወገኔ በፊት እኔ ልቅደም” ብለው ደማቸውን ለአፈር፣ ሥጋቸውን ለአሞራ ባይሰጡ ኖሮ የዛሬው ቀን ዛሬን ባልመሰለ ነበር፡፡

የሰሜን ዕዝ ሠራዊት የተደራጀው ከአንድ አካባቢ አልነበረም፡፡ አማራና ኦሮሞው፣ ሲዳማና ወላይታው፣ አፋርና ጋምቤላው፣ ጉራጌና ሐድያው ከሁሉም ብሔር ተውጣጥቶ ሀገር እንዲጠብቅ የተደራጀ ሠራዊት ነበር፡፡ ሀገሬን ብሎ ለሃያ ዓመታት ከቤቱና ካሳደገው ቀዬ ተነጥሎ ዱር እያደረ ድንበር ሲጠብቅ ኖሯል፡፡ ሠራዊቱ ለትግራይ ክልልና ለሕዝቡ ከደግነት ውጭ ክፉ ሆኖ አያውቅም። ጠላት ሲመጣ የሚመክት፣ አዝመራ ሲደርስ የሚያጭድ፣ በማኅበረሰባዊ ተግባራት ላይ የሚካፈል ነበር። በደምና በላቡ ለከፈለው ደግነት በምላሹ ከሽብር ቡድኑ ሕወሐት የተቀበለው ክህደት ነው።

ኢትዮጵያን ለመውረር የመጡ ጠላቶች እንደ ሽብር ቡድኑ ዋነኛ የጦር ቤዛችንን በመደብደብ አልጀመሩም፡፡ ዋና ዋና መኮንኖችን በመግደልና ከባድ መሣሪያዎቻችንን ዘርፈው አልተነሡም። የጦርነት ቅዱስ ባይኖርም ለጭካኔም ልክ አለው። በሽብር ቡድኑ ልክ ኢትዮጵያ ላይ የጨከነ የለም፡፡ ጥቅምት 24 ሠራዊቱ ላይ የክህደት ጥቃት ሲፈጸም የሞቱት እነዚያ ጀግኖች ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ እንደመሆናቸው የተፈጸመባቸው ግፍ በኢትዮጵያ ላይ የተፈጸመ ግፍ ነው።

የሽብር ቡድኑ በሰሜን ዕዝ ላይ የፈጸመው ጥቃት መሣሪያ ለመዝረፍ ብቻ የተደረገ ተራ ጥቃት አልነበረም፡፡ በተንኮል የተቀመመና በክፋት የሞላ መሆኑ የተለየ ያደርገዋል፡፡ የገዛ ጓዶቹን አስኮብልሎ በተኛበት ከመግደል ባለፈ ከሬሳው ላይ ልብሱን ገፍፎ የአውሬ ቀለብ እንዲሆን እርቃኑን ሜዳ ላይ ጥሎታል። ይኼን ሲያደርግ የሽብር ቡድኑ ዓላማ ሁለት ነው፡፡ አንደኛ ሠራዊቱ በሐፍረት በትር እየተቀጣ ሞራሉ እንዲላሽቅና የአቅመ ቢስነት ስሜት እንዲሰማው፡፡ ሁለተኛ ሠራዊቱ እርስ በእርስ እንዳይተማመንና “ክፉና ደጉን አብሮ ከተካፈሉኝ ጓዶቼ እንደዚህ ዓይነት ነውር ዛሬ ከተፈጸመብኝ ነገስ?” ብሎ እንዲጠራጠር ለማድረግ ታስቦ ነበር፡፡ ዳሩ ግን ሠራዊቱ እንደተጠበቀው አልሆነም፡፡

የወንድሞቹ ደም በከንቱ መፍሰስ ያንገበገበው ሠራዊት በፍጥነት ራሱን አደራጅቶ በሦስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ የሽብር ቡድኑ ያደራጀውን ኃይል ወደ በርሃ እንዲበተን ማድረግ ችሏል፡፡ የቡድኑን ቁንጮ አመራሮች አብዛኞቹን ይዞ ለሕግ አስረክቧል፡፡ የተፈጸመበትን ክህደት በበቀል ሒሳብ ሳይሆን የሕግ ማስከበር መርሕን በተከተለ መንገድ ሲያከናውን ነበር፡፡ በጦርነት ውስጥ ለመርሕ መገዛት ቀላል አይደለም፡፡ ሠራዊታችን ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ከሽብር ቡድኑ ጋር አያሌ ውጊያዎችን ሲያደርግ ብዙ ዋጋ ከፍሏል፡፡ በየጦር ውሎው በጀግንነት እየተዋጋ ለእናት ሀገሩ ተሠውቷል፡፡ ለሀገርና ለወገን ያለውን አጋርነት በንግግር ሳይሆን በተግባር አሳይቷል፡፡ አሁንም በዱር በገደሉ እየተዋደቀ ነው፡፡

ዛሬ ሽብር ቡድኑ የተሰጠውን የጥሞና ጊዜ እንድ እድል ከመጠቀም ይልቅ እንደ ድል ወሰደው። በአማራና በአፋር ክልል በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የግፍ በትሩን ቀጥሎበታል፡፡ የጥፋት አጋሩ ሸኔም በኦሮሚያ ክልል ወለጋ አካባቢ ልዩ ልዩ አደጋዎችን እየጣለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያንን ረፍት እየነሣ ነው፡፡ ሌሎችም የጥፋት ኃይሎች ከውስጥም ከውጭም ወኪሎቻቸውን አስተባብረው በሙሉ ዐቅማቸው ኢትዮጵያ ላይ መዝመታቸውን ገፍተውበታል፡፡

ሠራዊታችን ብቻውን ተጋፍጦ የድል ዜና እንዲያበስረን መጠበቅም ሞኝነት ነው፡፡ ጠላቶቻችን ተባብረው የደቀኑብን አደጋ ሁላችንም ተባብረን ካልመከትነው ድል የማይታሰብ ነው፡፡ የጠላቶቻችን ኅብረት ለፕሮፓጋንዳ የተፈበረከ ጉዳይ አይደለም፡፡ እውነት ነው፡፡ እነዚህ ኃይሎች ዓላማቸው ግልጽ ነው፡፡ ብረት ያነሡት ሀገር ለማፍረስ እንጂ ሀገር ለመገንባት አይደለም፡፡ የኢትዮጵያን ስም በክፉ የሚያብጠለጥሉ፣ ነገ የሊቢያና የሶርያን እጣ ሊያስታቅፉን እንዲመቻቸው የፈጠሩት ዘዴ መሆኑን ልናውቅ ይገባል፡፡ ጠላቶቻችን በዚህ ደረጃ ሲተባበሩብን እኛ አንድ የማንሆንበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ የወንድምና የእኅቶቹ ጥቃት የሚያንገበግበው ሁሉ ጣት ከመጠቆም ወጥቶ ሀገር የማዳን ፍላጎቱን በተግባር መግለጥ አለበት፡፡

ወደፊት ታሪክ ፍርዱን ይሰጣል፡፡ ፈሪውም በፈሪነቱ፣ ሴረኛውም በሴረኛነቱ እንደየግብሩ ይመዘገባል፡፡ የሽብር ቡድኑን ትውልድ በክህደት ሲያስታውሳቸው እንደሚኖር ግልጽ ነው፡፡ በተቃራኒው በግፍ የተሠውት የሰሜን ዕዝ አባላትን ጨምሮ ለሀገር የሚዋደቁ ጀግኖች ስማቸው በወርቅ ይጻፋል፡፡

ክብር ኢትዮጵያን ሲሉ ለተሠዉ ጀግኖቻችን!!

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ታማኝ፣ ትኩስ፣ ወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃዎችን ለመከታተል እንዲሁም ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ!

ድል ለአማራ ህዝብ
ድል ለእናት ሀገራችን
ሞት ለአሻባሪው እና ለመላው ሀገር ሻጮች

ቻ @YeNatnael_Tube
ና @YeNatnael_Tube
ል @YeNatnael_Tube

መረጃዎችን ለመለዋወጥ የቴሌግራም ግሩፑን ይቀላቀላሉ @AmharaDiscussion
6.2K viewsÑäťňāêł Ŧãmïřű, 06:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-03 09:22:19
4.5K viewsÑäťňāêł Ŧãmïřű, 06:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-30 21:10:59 እጅግ የተከበርከው የአማራ ክልል ሕዝብ ሆይ! በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል ሀገርን ማፍረስ ዋነኛ ቀዳሚ ዓላማ አድርጎ ይህንኑ ፍላጎቱን ለማስጠበቅ በአይነቱ የተለየ፣ በተሳሳተ ትርክትና የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ የተጠለፈ ሕዝባዊ አሰላለፍ በመፍጠር መጠነ ሰፊ ወረራ መፈፀሙና እየፈፀመ መሆኑ ይታወቃል።
እድሜያቸው ከ12 እስከ 65 ዓመት የሚደርሱ ወንድና ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞችና ነፍሰ ጡሮች፣ ካህናትና ሸኮች ሳይቀር እያስገደደ በማሰማራት ወደ አማራና አጎራባች የአፋር ክልሎች አዝምቷል።

በዚህ ወረራ ወደር የሌለው ጭካኔ በመላበስ አማራን እስከወዲያኛው አንገት ለማስደፋት በየደረሰበት አካባቢ ሴቶችን በመድፈር፣ ንጹሐንን በመረሸን፣ መሰረተ ልማቶችን በማውደም፣ የመንግሥትና የግለሰብ ሀብቶችን በመዝረፍ፣ የቤት እንስሳትን በጥይት በመግደል ሕዝብን እያሸበረ ከቀየው እንዲሰደድ በማድረግ ላይ ይገኛል።

የትግራይ ወራሪ ኃይል ሀገርን የማፍረስና አማራን እንደ ሕዝብ የማጥፋት ዘመቻው ከመደበኛ ወታደራዊ አደረጃጀት በተጨማሪ በሕዝባዊ ማዕበል መቀልበስና መደምሰስ እንዳለበት ግድ የሚል ሁኔታ ስለተፈጠረ ሀገራዊ የመንግሥት ጥሪ መተላለፉ ይታወቃል።

ይህ ሀገራዊ የመንግሥት ጥሪ እንደተጠበቀ ሆኖ በአማራ ክልል ደረጃ ፈጣንና የተደራጀ ሁሉ አቀፍ ሕዝባዊ ዘመቻ ማካሄድ ጊዜ የማይሰጠው እጅግ አጣዳፊ ጉዳይ ሆኗል። ስለሆነም እድሜውና አካላዊ ብቃቱ የፈቀደለት የክልላችን ሀገር ወዳድ ዜጋ ሁሉ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 23/2014 ዓ.ም ድረስ ማንኛውንም መሳርያና ስንቅ በመያዝ ወደ ወረዳ ማዕከላት የክተት ጥሪውን ተቀብሎ እንዲገባ የክልሉ መንግሥት ታላቅ የሕልውና ዘመቻ ጥሪ አቅርቦልሃል።

ሁሉ አቀፍ የሕልውና ዘመቻውን የተደራጀ አመራር፣ በሕዝባዊ ማዕበል ተመስርቶ በእልህና በወኔ ለማከናወን የሚያስችል ዝርዝር ማስፈፀሚያ መመርያ በየአካባቢው ይደርስሃል።

የዚህ ክተት ዘመቻ ዋነኛ ኃይላችን ለመስዋእትነት የተዘጋጀ ሕዝባችን መሆኑን የክልላችን መንግሥት ያምናል። በመሆኑም አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኃይል የከፋ ምኞት ማምከን ብሎም የገባበት ገብቶ ለመደምሰስ የቀረበውን የጀግንነት ጥሪ በመቀበል ኢትዮጵያን ለማዳን እንዲሁም የአማራ ክልልን ሕዝብ ከውርደት ለመታደግ እንድንዘምት የክልሉ መንግሥት ጥሪውን በድጋሜ ያስተላልፋል።

ህልውናችንን በትግላችን እናረጋግጣለን! እናሸንፋለን

ክተት
መክት
አንክት

ታማኝ፣ ትኩስ፣ ወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃዎችን ለመከታተል እንዲሁም ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ!

ድል ለአማራ ህዝብ
ድል ለእናት ሀገራችን
ሞት ለአሻባሪው እና ለመላው ሀገር ሻጮች

ቻ @YeNatnael_Tube
ና @YeNatnael_Tube
ል @YeNatnael_Tube

መረጃዎችን ለመለዋወጥ የቴሌግራም ግሩፑን ይቀላቀላሉ @AmharaDiscussion
6.6K viewsÑäťňāêł Ŧãmïřű, 18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-29 23:55:35 ከሰሞኑ በአየርና በምድር ከፍተኛ ድብደባ የደረሰበት ወንበዴ ቡድን በሌሊት ከደሴ አካባቢ ለማምለጥ ሞክሯል። ቁስለኛውን እና አስከሬኑን አንጠባጥቦ የሄደው ይኸው ወራሪ ቡድን ከኩታበር ማዶ ሆኖ ለመዋጋት እየተፍጨረጨረ ነው። በአሁኑ ሰዓት ከኩታበር ወዲህ እየዋጉ ያሉት በምላስ ብቻ ነው። ምላሳቸውም ከድቷቸው መንተባተብ ጀምረዋል። ቃል አቀባያቸው ወገቡን ይዞ ስድብ ጀምሯል። በዚህ አያያዙ በቅርቡ በኦራል ተንጠላጥሎ መጥቶ እጅ እንደሚሰጥ ይጠበቃል። እጁን ካልሰጠ እግሩን ጨምሮ የሚያጣ ይሆናል....!

ወደ ኩታበር ሲሸሽ የነበረው ቡድን ላይ ተቆርጠው የቀሩ ቁስለኞች አቅጣጫ ጠፍቷቸው ወደ ጦሳ እና ቦሩ ገደል ለገደል እየዋጀጁ ተኩስ ለመክፈት ሞክረው ነበር። ለምሳሌ ዛሬ ረፋዱ ላይ ወደ 50 የሚጠጉ የሚዋጅጁ ወራሪዎች በሩጋ በኩል ተኩስ ከፍተው ነበር። ጠዋት ላይ 50 ወራሪዎች ነበሩ በአሁኑ ሰዓት ግን 50 አስከሬን ሆነዋል። የተራበው እና የቆሰለው ወራሪ ወደ ትግራይ የሚያስኬደው መንገድ በየት በኩል ነው እያለ ይጠይቃል። መሳሪያውን ጥሎ የሚፈረጥጠው አያሌ ነው። በፍርጠጣ ላይ የሚገኘውን ወራሪ የአካባቢው ምሊሻ እና አርሶ አደር በሚገባው ቋንቋ መሬት ይዘው እያናገሩት ነው።

ደሴ ከኢትዮጵያ ህዝባዊ ሰራዊት በተጨማሪ በጀግና ልጆቿ ጥንቅቅ ብላ እየተጠበቀች ትገኛለች። በነገራችን ላይ ወራሪው ቡድን ከባድ መሳሪያ ወደተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ተኩሶ ነበር። ሁሉም ኮብል ስቶን ከመፈንቀል ውጭ እዚህ ግባ የሚባል ጥፋት አላጠፉም። በተለይ የተወሰኑት ከባድ መሳሪያዎች ግለሰቦችን ለማጥቃት የተተኮሱ ነበሩ።

ጋሻው መርሻ


ክተት
መክት
አንክት

ታማኝ፣ ትኩስ፣ ወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃዎችን ለመከታተል እንዲሁም ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ!

ድል ለአማራ ህዝብ
ድል ለእናት ሀገራችን
ሞት ለአሻባሪው እና ለመላው ሀገር ሻጮች

ቻ @YeNatnael_Tube
ና @YeNatnael_Tube
ል @YeNatnael_Tube

መረጃዎችን ለመለዋወጥ የቴሌግራም ግሩፑን ይቀላቀላሉ @AmharaDiscussion
4.9K viewsÑäťňāêł Ŧãmïřű, 20:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-29 23:30:29 ከመሼ ከወገልጤና ወደ ኩታበር አቅጣጫ የአሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን ታጣቂ በሰባት ሸልቶ ተጭኖ ሲጓጓዝ ጎሽ ሜዳ ዝቅ ብሎ እና ግሸን መገንጠያ ላይ በጀግናው ሰራዊታችን ድባቅ ተመቷል።

የቴሌግራም ግሩፑን ተቀላቅለው መረጃዎችን ይለዋወጡ @AmharaDiscussion
4.5K viewsÑäťňāêł Ŧãmïřű, edited  20:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-29 21:11:03
ከደሴ ህዝብ ደም ላለመቃባት ብለን ወደ ኋላ ተመለስን ሲል አሸባሪ ህወሓት ዛሬ በሰበር ዜና ገልፃል።

አሸባሪው ትህነግ አፋር ክልል ላይ በደንብ ሲገረፍም “ወደ ሃላ የተመለስኩት ከዓፋር ህዝብ ጋር ደም ላለመቃባት ብዬ
ነው” ብሎ እንደነበር ይታወሳል።

የአሸባሪው ትህነግ ቡድን በአየር ሃይላችን ተመተው የተገደሉበት ከፍተኛ አመራሮቹ ሞራሉ ተነክቶ በከፍተኛ ድንጋጤ ላይ ነው የሚገኘው።

ቻ @YeNatnael_Tube
ና @YeNatnael_Tube
ል @YeNatnael_Tube

መረጃዎችን ለመለዋወጥ የቴሌግራም ግሩፑን ይቀላቀላሉ @AmharaDiscussion
4.5K viewsÑäťňāêł Ŧãmïřű, 18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ