Get Mystery Box with random crypto!

ከሰሞኑ በአየርና በምድር ከፍተኛ ድብደባ የደረሰበት ወንበዴ ቡድን በሌሊት ከደሴ አካባቢ ለማምለጥ | ጋፋት ስቱዲዮ / Gafat Studio

ከሰሞኑ በአየርና በምድር ከፍተኛ ድብደባ የደረሰበት ወንበዴ ቡድን በሌሊት ከደሴ አካባቢ ለማምለጥ ሞክሯል። ቁስለኛውን እና አስከሬኑን አንጠባጥቦ የሄደው ይኸው ወራሪ ቡድን ከኩታበር ማዶ ሆኖ ለመዋጋት እየተፍጨረጨረ ነው። በአሁኑ ሰዓት ከኩታበር ወዲህ እየዋጉ ያሉት በምላስ ብቻ ነው። ምላሳቸውም ከድቷቸው መንተባተብ ጀምረዋል። ቃል አቀባያቸው ወገቡን ይዞ ስድብ ጀምሯል። በዚህ አያያዙ በቅርቡ በኦራል ተንጠላጥሎ መጥቶ እጅ እንደሚሰጥ ይጠበቃል። እጁን ካልሰጠ እግሩን ጨምሮ የሚያጣ ይሆናል....!

ወደ ኩታበር ሲሸሽ የነበረው ቡድን ላይ ተቆርጠው የቀሩ ቁስለኞች አቅጣጫ ጠፍቷቸው ወደ ጦሳ እና ቦሩ ገደል ለገደል እየዋጀጁ ተኩስ ለመክፈት ሞክረው ነበር። ለምሳሌ ዛሬ ረፋዱ ላይ ወደ 50 የሚጠጉ የሚዋጅጁ ወራሪዎች በሩጋ በኩል ተኩስ ከፍተው ነበር። ጠዋት ላይ 50 ወራሪዎች ነበሩ በአሁኑ ሰዓት ግን 50 አስከሬን ሆነዋል። የተራበው እና የቆሰለው ወራሪ ወደ ትግራይ የሚያስኬደው መንገድ በየት በኩል ነው እያለ ይጠይቃል። መሳሪያውን ጥሎ የሚፈረጥጠው አያሌ ነው። በፍርጠጣ ላይ የሚገኘውን ወራሪ የአካባቢው ምሊሻ እና አርሶ አደር በሚገባው ቋንቋ መሬት ይዘው እያናገሩት ነው።

ደሴ ከኢትዮጵያ ህዝባዊ ሰራዊት በተጨማሪ በጀግና ልጆቿ ጥንቅቅ ብላ እየተጠበቀች ትገኛለች። በነገራችን ላይ ወራሪው ቡድን ከባድ መሳሪያ ወደተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ተኩሶ ነበር። ሁሉም ኮብል ስቶን ከመፈንቀል ውጭ እዚህ ግባ የሚባል ጥፋት አላጠፉም። በተለይ የተወሰኑት ከባድ መሳሪያዎች ግለሰቦችን ለማጥቃት የተተኮሱ ነበሩ።

ጋሻው መርሻ


ክተት
መክት
አንክት

ታማኝ፣ ትኩስ፣ ወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃዎችን ለመከታተል እንዲሁም ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ!

ድል ለአማራ ህዝብ
ድል ለእናት ሀገራችን
ሞት ለአሻባሪው እና ለመላው ሀገር ሻጮች

ቻ @YeNatnael_Tube
ና @YeNatnael_Tube
ል @YeNatnael_Tube

መረጃዎችን ለመለዋወጥ የቴሌግራም ግሩፑን ይቀላቀላሉ @AmharaDiscussion