Get Mystery Box with random crypto!

እጅግ የተከበርከው የአማራ ክልል ሕዝብ ሆይ! በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል ሀገርን ማፍረስ ዋነ | ጋፋት ስቱዲዮ / Gafat Studio

እጅግ የተከበርከው የአማራ ክልል ሕዝብ ሆይ! በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል ሀገርን ማፍረስ ዋነኛ ቀዳሚ ዓላማ አድርጎ ይህንኑ ፍላጎቱን ለማስጠበቅ በአይነቱ የተለየ፣ በተሳሳተ ትርክትና የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ የተጠለፈ ሕዝባዊ አሰላለፍ በመፍጠር መጠነ ሰፊ ወረራ መፈፀሙና እየፈፀመ መሆኑ ይታወቃል።
እድሜያቸው ከ12 እስከ 65 ዓመት የሚደርሱ ወንድና ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞችና ነፍሰ ጡሮች፣ ካህናትና ሸኮች ሳይቀር እያስገደደ በማሰማራት ወደ አማራና አጎራባች የአፋር ክልሎች አዝምቷል።

በዚህ ወረራ ወደር የሌለው ጭካኔ በመላበስ አማራን እስከወዲያኛው አንገት ለማስደፋት በየደረሰበት አካባቢ ሴቶችን በመድፈር፣ ንጹሐንን በመረሸን፣ መሰረተ ልማቶችን በማውደም፣ የመንግሥትና የግለሰብ ሀብቶችን በመዝረፍ፣ የቤት እንስሳትን በጥይት በመግደል ሕዝብን እያሸበረ ከቀየው እንዲሰደድ በማድረግ ላይ ይገኛል።

የትግራይ ወራሪ ኃይል ሀገርን የማፍረስና አማራን እንደ ሕዝብ የማጥፋት ዘመቻው ከመደበኛ ወታደራዊ አደረጃጀት በተጨማሪ በሕዝባዊ ማዕበል መቀልበስና መደምሰስ እንዳለበት ግድ የሚል ሁኔታ ስለተፈጠረ ሀገራዊ የመንግሥት ጥሪ መተላለፉ ይታወቃል።

ይህ ሀገራዊ የመንግሥት ጥሪ እንደተጠበቀ ሆኖ በአማራ ክልል ደረጃ ፈጣንና የተደራጀ ሁሉ አቀፍ ሕዝባዊ ዘመቻ ማካሄድ ጊዜ የማይሰጠው እጅግ አጣዳፊ ጉዳይ ሆኗል። ስለሆነም እድሜውና አካላዊ ብቃቱ የፈቀደለት የክልላችን ሀገር ወዳድ ዜጋ ሁሉ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 23/2014 ዓ.ም ድረስ ማንኛውንም መሳርያና ስንቅ በመያዝ ወደ ወረዳ ማዕከላት የክተት ጥሪውን ተቀብሎ እንዲገባ የክልሉ መንግሥት ታላቅ የሕልውና ዘመቻ ጥሪ አቅርቦልሃል።

ሁሉ አቀፍ የሕልውና ዘመቻውን የተደራጀ አመራር፣ በሕዝባዊ ማዕበል ተመስርቶ በእልህና በወኔ ለማከናወን የሚያስችል ዝርዝር ማስፈፀሚያ መመርያ በየአካባቢው ይደርስሃል።

የዚህ ክተት ዘመቻ ዋነኛ ኃይላችን ለመስዋእትነት የተዘጋጀ ሕዝባችን መሆኑን የክልላችን መንግሥት ያምናል። በመሆኑም አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኃይል የከፋ ምኞት ማምከን ብሎም የገባበት ገብቶ ለመደምሰስ የቀረበውን የጀግንነት ጥሪ በመቀበል ኢትዮጵያን ለማዳን እንዲሁም የአማራ ክልልን ሕዝብ ከውርደት ለመታደግ እንድንዘምት የክልሉ መንግሥት ጥሪውን በድጋሜ ያስተላልፋል።

ህልውናችንን በትግላችን እናረጋግጣለን! እናሸንፋለን

ክተት
መክት
አንክት

ታማኝ፣ ትኩስ፣ ወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃዎችን ለመከታተል እንዲሁም ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ!

ድል ለአማራ ህዝብ
ድል ለእናት ሀገራችን
ሞት ለአሻባሪው እና ለመላው ሀገር ሻጮች

ቻ @YeNatnael_Tube
ና @YeNatnael_Tube
ል @YeNatnael_Tube

መረጃዎችን ለመለዋወጥ የቴሌግራም ግሩፑን ይቀላቀላሉ @AmharaDiscussion