Get Mystery Box with random crypto!

ሀገር በተለያዩ ጊዜያት አደጋ ላይ በገባች ጊዜ መሪዎች ጦራቸውን ግንባር ሆነው በመምራት ወርቃማ ድ | ጋፋት ስቱዲዮ / Gafat Studio

ሀገር በተለያዩ ጊዜያት አደጋ ላይ በገባች ጊዜ መሪዎች ጦራቸውን ግንባር ሆነው በመምራት ወርቃማ ድል አስመዝግበዋል።
በአድዋ ጦርነት የአፄ ሚኒሊክን እና የእቴጌ ጣይቱን በጦር ግንባር የፈጸሙትን የአመራር ጥበብ ማንሳት ይቻላል። በአድዋ የነገስታቱን ግንባር መዝመት አነሳን እንጂ በየጊዜው የነገሱ ነገስታቶች እና የሀገር መሪዎች ጦራቸውን ግንባር ድረስ በመምራት ተዋግተዋል፤ አዋግተዋል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም (ዶክተር) ሀገሪቱ በውስጥ እና በውጭ ኀይሎች የተሰነዘረባትን የተቀናጀ ጥቃት በመቀልበስ ደማቅ ገድል እንድትጽፍ ግንባር ዘምተዋል።

ኮንስታብል ፋሲል አለልኝ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ግንባር መቀላቀል ከነበራቸው ወታደራዊ ወኔ በላይ እንዳነሳሳቸው ገልጸዋል። እንኳን ግንባር ለዘመተው ሠራዊት ለመዝመት ለተዘጋጁ ወጣቶችም ሞራል እና ወኔን ይፈጥራል። የደጀኑ ሕዝብም በግንባር ለሚዋደቀው ሠራዊት የሚያደርገውን እገዛ የበለጠ ያጠናክራል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ግንባር መዝመት የሠራዊቱን ወኔ የበለጠ እንዲነሳሳና በመንግሥት እና በሕዝብ መካከል የሚኖረውን መስተጋብር የበለጠ የሚያጠናክር ነው።

ሠራዊቱ ሀገርን ለማገልገል ከገባው ግዳጅ በላይ ወኔ ተላብሶ ለመፋለም ትልቅ ስሜት ፈጥሯል። አንድ የሀገር መሪ ግንባር ሲዘምት የደጀኑ ሕዝብም በገንዘቡ እና በስንቅ ዝግጅት ሥራ የበለጠ እገዛ እንዲያደርግ ያግዛል።

የጠቅላይ ሚንስትሩ ግንባር መቀላቀል ሠራዊቱ ግዳጁን የበለጠ እንዲወጣ ወኔ ፈጥሯል።
ታማኝ፣ ትኩስ፣ ወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃዎችን ለመከታተል እንዲሁም ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ!

አዲሱን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!!!
#Subscribe For [ Gafat Studio - ጋፋት ስቱዲዮ ] https://youtube.com/channel/UCoheB9PLWR2zx9ouBfKBrmQ
ድል ለአማራ ህዝብ
ድል ለእናት ሀገራችን
ሞት ለአሻባሪው እና ለመላው ሀገር ሻጮች

ቻ @YeNatnael_Tube
ና @YeNatnael_Tube
ል @YeNatnael_Tube

መረጃዎችን ለመለዋወጥ የቴሌግራም ግሩፑን ይቀላቀላሉ @AmharaDiscussion