Get Mystery Box with random crypto!

ጠ/ሚ/ር ዐቢይ መላው ጥቁር ሕዝብ ከኢትዮጵያ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዛሬ | ጋፋት ስቱዲዮ / Gafat Studio

ጠ/ሚ/ር ዐቢይ መላው ጥቁር ሕዝብ ከኢትዮጵያ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዛሬ ጀምሮ ጦሩን ለመምራት ወደ ግንባር ለመሄድ መወሰናቸውንም ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ መላው ጥቁር ሕዝብ ከኢትዮጵያ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ትናንት ምሽት ባስተላለፉት መልዕክት፤ “ኢትዮጵያ አፍሪካዊ በሆነ መንገድ ከተነሣች፣ ተነሥታም ካሸነፈች፣ ከዚህ በኋላ ለማንም የማትመለስ ትሆናለች። ይሄን አፍሪካዊ መንገድ ለማደናቀፍ ሁሉንም ዓይነት የክፋት መሣሪያዎች አሰልፈዋል” ብለዋል።
“ከእንግዲህ እኔ መከላከያን በግንባር ሆኜ ለመምራት ከነገ ጅምሮ ወደ ትግሉ ሜዳ እዘምታለሁ”- ጠ/ሚ ዐቢይ
“ይህ ትግል የመላ ጥቁር ሕዝቦች ትግል ነው ያሉት” ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “ኢትዮጵያ አንበርክኮ ጥቁር ሕዝብን ለማሳፈርና አዲሱን የቅኝ ግዛት ቀንበር ለመጫን የሚደረግ ሤራ ነው” ሲሉም ገልፀዋል።

ጥቁር ሕዝቦች የራሳችን ታሪክ፣ ባህል፣ ማንነትና ክብር እንዳይኖረን ሆን ተብሎ የሚደረግ አንገት የማስደፋት ትግል ነው፤ ይህ በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተ ዘመቻ፣ ኢትዮጵያን በማንበርከክ ጥቁር ሕዝቦች የነጻነትና የአሸናፊነት አርአያ እንዳያገኙ የተከፈተ ዘመቻ መሆኑንም ገልፀዋል።
“ለጥቁር ሕዝብ ክብርና ልዕልና ስትሉ፣ በፓን አፍሪካ መንፈስ፣ ሁላችሁም ጥቁር ሕዝቦች፣ ከኢትዮጵያ ጋር እንድትቆሙ ጥሪ አቀርብላችኋለሁ” ብለዋል።
በኢትዮጵያ ላይ የተደቀነውን የሕልውና አደጋ ለመመከት አመራሩ ከፊት ተሰልፎ ሚናውን እንደሚወጣ የብልጽግና ፓርቲ ገለፀ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልእክታቸው አክለውም፤ ኢትዮጵያ መከራ ማለፍ ነባር ችሎታዋ እንደሆነ የገለጹ ሲሆን፤ አሁን ሀገሪቱ የገጠማትን መከራም “እናልፈዋለን፤ኢትዮጵያም ማሸነፏ አይቀርም፤ አሁን ኢትዮጵያን ለመታደግ የመጨረሻውን ፍልሚያ የምናደርግበት ጊዜ ላይ ነን” ብለዋል።
ጊዜው ሀገርን በመሥዋዕትነት መምራት የሚያስፈልግበት ጊዜ እንደሆነ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከእንግዲህ ”እኔ መከላከያን በግንባር ሆኜ ለመምራት ከነገ ጀምሮ ወደ ትግሉ ሜዳ እዘምታለሁ” ሲሉ በትናንትና ምሽት መልዕክታቸው ገልጸዋል።
በዚህም ታሪክ ከሚያደንቃቸው የኢትዮጵያ ልጆች አንዱ ለመሆን “የምታስቡ ሁሉ ለሀገራችሁ ስትሉ ዛሬውኑ ተነሡ፤ ግንባር ላይ እንገናኝ” ም ብለዋል።

ታማኝ፣ ትኩስ፣ ወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃዎችን ለመከታተል እንዲሁም ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ!

ድል ለአማራ ህዝብ
ድል ለእናት ሀገራችን
ሞት ለአሻባሪው እና ለመላው ሀገር ሻጮች

ቻ @YeNatnael_Tube
ና @YeNatnael_Tube
ል @YeNatnael_Tube

መረጃዎችን ለመለዋወጥ የቴሌግራም ግሩፑን ይቀላቀላሉ @AmharaDiscussion