Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅር 🄻🄾🅅🄴❤️

የቴሌግራም ቻናል አርማ yefkersew — ፍቅር 🄻🄾🅅🄴❤️
የቴሌግራም ቻናል አርማ yefkersew — ፍቅር 🄻🄾🅅🄴❤️
የሰርጥ አድራሻ: @yefkersew
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 143
የሰርጥ መግለጫ

ፍቅር የሌለው እግዚአብሔር አያውቅምና
እግዚአብሔር ፍቅር ነው
1ዮሀ 4:8

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-05 21:11:12
➲ ኢትዮጵያ ሀገሬ

እግዜር የባረከሽ ፣ የቅኔዎች አድባር
ስምሽ ይጣፍጣል ፣ ልክ እንደ ወለላማር

የፍጥረት አውድማ ፣ የመኖር ሚስጥሬ
አንቺ ብቻ እኮ ነሽ ፣ ኢትዮጵያ ሀገሬ።

ባለብዙ ምስጢር ፣ በስመገናና
ታሪክሽ ተፅፏል ፣ በደማቅ ብራና

ትውልድሽም ሳይቀር ፣ በጥበብ ታንጿል
ሰንደቅሽን አስሮ ፣ ዘመቻ ጀመሯል።

የቃልኪዳን ምድር፣ ለነፃነት ቋሚ
ወትሮም ከጥንት ነሽ ፣ አንደኛ ቀዳሚ።

አምሳለ ገነት ሆይ ፣ ውዲቷ እናቴ
እስቲ ልመርቅሽ ፣ እኔም በአንደበቴ

እዮብን አይተሽው ፣ ከልብሽ ተፅናኚ
እንባሽን አብስሽ፣ ተስፋሽን ጠግኚ

በሄድሽበት ሁሉ ፣ ፈጣሪ ይከተልሽ
ከስንፍና ይልቅ ፣ ልቦናውን ይስጥሽ

መልክሽም ይታደስ ፣ እንደ አደይ አበባ
ፈፅሞ አይንካሽ ፣ የውድቀት ገለባ

ወታደሮችሽም ፣ መንገዱ ይቅናቸው
እንክርዳዱ ቀርቶ፣ ስንዴው ይግጠማቸው።

ቤዛዊት ታፈሰ
36 views18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 21:32:26
#ፀናለሁ

ትመጣለች ብለዉ ተስፋ እያሰነቁኝ
ስንት ጊዜ ነጋ ስንት ጊዜ መሸ ሳቅ እንደናፈቅሁኝ

አንቺ ግን
በናፍቆትሽ ገመድ ታስሮ 'ሚጠብቅሽ
በእንባ 'ሚታጠበው ያው ቡቡው አድናቂሽ

እንዲሉሽ ፈልገሽ
ልክ እንደመስቀል ወፍ ታይተሽ ትጠፊያለሽ

አበቦች ሲፈኩ ደምቀሽ ትመጪና ሲከስሙ ስትከስሚ
ስጠብቅሽ ውዬ ተስፋዬ ተሟጦ ጠርቼ ገጣሚ

"በል እንግዲህ ሆዴ ካለው ተላመድ
ቢያስሩበት አያጠብቅ በስባሳ ገመድ"

የሚለውን ስንኝ ከነፍሴ እንዲያዋህድ

እንድረሳሽ ብሎ ቅኔ እየዘረፈ ስንኝ ቢያሰናኝም
እንኳንስ ሊያስረሳኝ ትዝ አልሽኝ ሲገጥም

እናም እርሳኝ ካልሽኝ መርሳቱን አልችልም
ቀሰሩብኝ ብዬ ዓለሜን አልሰጥም
አስበኝ ካልሽኝ ግን አስታውሰኝ ካልሽኝ ግን እጠብቅሻለሁ ጊዜው ለ'ኔ እስኪቆም

ዓለሜን አፅድቆ የወል ሀቅ እስኪያረግ
ውጣ ቢሉኝ ገደል ውረድ ቢሉኝ 'ረግረግ
እከተልሻለሁ ዳንኤል ነኝ አልፈራም
እወድቅ ቢሆን እንጂ ከቶ አልሰበርም .


━━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━━
45 views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 10:55:31
አንድ ሊቅ ተጠየቀ :- ማነው ብልህ . . . ? ቢሉት - ከእያንዳንዱ ሰው ሊማር የሚችል

ማነው ጠንካራ ሰው ? ስሜቱን የሚቆጣጠር ,
ማነው ሀብታም ቢሉት . . . በቃኝን የሚያውቅ ,
ማነው የተከበረ ሰው . . . ሰውን የሚያከብር ,
ማነው ቶሎ ነገር የሚገባው ? ቢሉት . . . በትዕግስት ሰውን የሚያደምጥ ሰው።

በዓሉ ግርማ~ ሀዲስ

ድንቅ ሊቅ ድንቅ እይታ።
85 views07:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 10:55:08 አባታችንን ሆይ የሚለው ፀሎት ለይ

የዕለት እንጀራችንን ስጠን ዛሬ ብለን ነው የምንፀልየው።

ብቻክን እኮ ነህ ግን የዕለት እንጀራዬን ስጠኝ አይደለም የምትለው......የዕለት እንጀራችንን ስጠን ነው የምትለው።

ስለዚህ የምንፀልየው ፀሎት.......አብረን ከሌሎች ጋር እንደምንበላ ቃል እየገባን ነው ማለት ነው።

እና የዕለት እንጀራችንን ስጠን ብለህ አንተ ብቻህን የምትበላ ከሆነ.....ወንድምህ ወድቆ ተርቦ እያየህ ዝም የምትለው ከሆነ.....ለጋራ የተቀበልከውን ምግብ ለብቻህ ይዘኸዋል ማለት ነው።

ስለዚህ አባታችን ሆይ በጣም ለመፅዋትም የሚያስገድድ ፀሎት ነው ማለት ነው።

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

ሀሳቡ ግልፅ ነው ስለዚህ ወገን እንንቃ እላለው

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
@yefkersew
76 views07:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 20:04:49 ባለህ ተደሰት

የሆነ እድሜ ስንደርስ ‘እርፍ እንላለን’ የሚል የተሳሳተ ሃሳብ ብዙዎቻችን ልብ ዉስጥ አለ ፡፡

ለምሳሌ “ልክ ሚስት አግብቼ እንትን መስሪያ ቤት ስገባ እርፍ እላለሁ፣ እንዲህ ሳደርግ እርፍ እላለሁ፡ ጭንቀቴ ይጠፋል ወዘተ...” እንላለን፡፡

አንድ ቀላል እዉነት አለ...በየትኛዉም እድሜ ላይ ብንሆን ሁሉን ነገር ማቅለል አይደለም ማሰብ እራሱ ይከብደናል፡፡

‘ይሄ ከተከናወነልኝ ደስተኛ እሆናለሁ’ ብለን መስፈርት ከሰጠን ደስተኛ የመሆን እድላችን ከጊዜ ወደጊዜ እየጠበበ ይሄዳል! ዛሬን፡ አሁን፡ እቺን ሰአት ባለን ነገር ደስታ እንፍጠርበት፡፡

ነገ እቅዶቻችን ሁሉ ቢሳኩ እንኳን ልክ ለመደሰት እቅድ ስንነድፍ ሌላ ሃሳብ፣ ሌላ ማነቆ፣ ሌላ ችግር እንፈጥራለን፡፡

ስለዚህ ዛሬን በጭንቀት ከመኖር የምንችለዉን በማድረግ፣ ከአቅማችን በላይ የሆነዉን ደግሞ ይለፍ ብለን በማሳለፍ ለራሳችን ዋጋ መስጠት!
87 views17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 21:01:48 የእድሜ_ባለፀጋው_ተጠየቁ!
ለመሆኑ እስካሁን ባሳለፉት እድሜ ምን ተማሩ?

እሳቸውም መለሱ!

"ይህች ዓለም የአበዳሪ እና የተበዳሪ መነታረኪያ መድረክ መሆኗን፤ መልካም የሠራ የብድሩን መልስ ከፈጣሪው ሳይሆን መልካም ከዋለለት አካል የሚጠብቅባት ዓለም እንደሆነች ተረዳሁ!"

"በዳይ ዘግይቶም ቢሆን የእጁን እንደሚያገኝ፣ ተበዳይም የበዳይን መጨረሻ በአይኔ ካላየሁ ብሎ ሲያለቅስ እድሜውን እንደሚፈጅ ተረዳሁ!"

"በለሊት የተወነጨፈች ቀስት ኢላማዋን እንደማትስትም ተማርኩ!"

"ህይወታችን እኛ ከዝንጋቴ ሳንወጣ በየትኛውም ቅፅበት ሊቋጭ እንደሚችል ተገነዘብኩ!"

"መልካም ንግግር፣ ፈገግታ የተሞላ ገፅታ፣ ችሮታ የማይለየው እጅ ካሉን ሃብቶች ሁሉ የላቁ ድልቦች እንደሆኑ ተማርኩ!"

ሰናይ ጊዜ!
@yefkersew
101 views18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 21:01:27
89 views18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 20:34:21 ​​​​​​​​​​​​​​​​​​◈ ━━━⸙ ፍቅሬን በግጥM ⸙━━━━◈


አረ እግዜር በናትህ ፥ በጭንቅ አማላጇ
ባጠቡህ ጡጦቿ ፥ ባጎረሰህ እጇ
ወይ ህፃን ሆነህ ና ፥ ወይ ሙሴን ስደደው
የማንም ወጠጤ፤
የቃል ኪዳን ምድሯን ፥ ክብሯን አወረደው
ዳዊትን ላክልን ፥ ወይ ደግሞ ወንጭፉን
ጎልያዶች በዝተው፤
የሚመካከሩት ፥ መች እንደሚያጠፉን
እባክህ እግዜር ና፤
ወይ ሎጥን ፍጠረው ፥ ከመካከላችን
ዝም ያልህ እንደሆን፤
ነበር መሆኑ ነው ፥ ምድር ላይ ስማችን።

እኔን ባይ
138 views17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 18:52:37
122 views15:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 18:50:18 መፍራት ስትጀምሩ መኖር ታቆማላችሁ!

• ፈራችሁም አልፈራችሁም መኖራችሁ ካልቀረ፣ ገና ለገና እሞታለሁ በሚልፍ ፍርሃት ታስራችሁ ከምትኖሩ ቀና ብላችሁ ብትኖሩ ይመረጣል፡፡

• ፈራችሁም አልፈራችሁም መነገዳችሁ ካልቀረ፣ ገና ለገና እከስራለሁ በሚል በፍርሃት ታስራችሁ ከምትነግዱ በአዎንታዊነት ተነቃቅታችሁ በትነግዱ ይሻላል፡፡

• ፈራችሁም አልፈራችሁም መማራችሁ ካልቀረ፣ ገና ለገና ፈተና እወድቃለሁ በሚል ፍርሃት ታስራችሁ ከምትማሩ እችለዋለሁ በሚል እምነትና ትጋት ብትማሩ የላቀ ነው፡፡

• ፈራችሁም አልፈራችሁም አንድን ሰው ማፍቀራችሁ ካልቀረ፣ ገና ለገና ይገፉኛል በሚል ፍርሃት ታስራችሁ ከምታፈቅሩ ጤናማ በራስ መተማመን ይዛችሁ ብታፈቅሩ እጅግ ተመራጭ ነው፡፡

መፍራት ስትጀምሩ መኖር ታቆማላችሁ! ቀና ብላችሁ መኖር ስትጀምሩ ደግሞ መፍራት ታቆማላችሁ!

ቀና ብላች ኑሩ እንጂ አትፍሩ!

ዶ/ር እዮብ ማሞ
106 views15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ