Get Mystery Box with random crypto!

የእድሜ_ባለፀጋው_ተጠየቁ! ለመሆኑ እስካሁን ባሳለፉት እድሜ ምን ተማሩ? እሳቸውም መለሱ! ' | ፍቅር 🄻🄾🅅🄴❤️

የእድሜ_ባለፀጋው_ተጠየቁ!
ለመሆኑ እስካሁን ባሳለፉት እድሜ ምን ተማሩ?

እሳቸውም መለሱ!

"ይህች ዓለም የአበዳሪ እና የተበዳሪ መነታረኪያ መድረክ መሆኗን፤ መልካም የሠራ የብድሩን መልስ ከፈጣሪው ሳይሆን መልካም ከዋለለት አካል የሚጠብቅባት ዓለም እንደሆነች ተረዳሁ!"

"በዳይ ዘግይቶም ቢሆን የእጁን እንደሚያገኝ፣ ተበዳይም የበዳይን መጨረሻ በአይኔ ካላየሁ ብሎ ሲያለቅስ እድሜውን እንደሚፈጅ ተረዳሁ!"

"በለሊት የተወነጨፈች ቀስት ኢላማዋን እንደማትስትም ተማርኩ!"

"ህይወታችን እኛ ከዝንጋቴ ሳንወጣ በየትኛውም ቅፅበት ሊቋጭ እንደሚችል ተገነዘብኩ!"

"መልካም ንግግር፣ ፈገግታ የተሞላ ገፅታ፣ ችሮታ የማይለየው እጅ ካሉን ሃብቶች ሁሉ የላቁ ድልቦች እንደሆኑ ተማርኩ!"

ሰናይ ጊዜ!
@yefkersew