Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅር 🄻🄾🅅🄴❤️

የቴሌግራም ቻናል አርማ yefkersew — ፍቅር 🄻🄾🅅🄴❤️
የቴሌግራም ቻናል አርማ yefkersew — ፍቅር 🄻🄾🅅🄴❤️
የሰርጥ አድራሻ: @yefkersew
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 143
የሰርጥ መግለጫ

ፍቅር የሌለው እግዚአብሔር አያውቅምና
እግዚአብሔር ፍቅር ነው
1ዮሀ 4:8

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-11 18:45:39 ክረምት ገባ አሉ

ያች ፀሀይ ተጋርዳ በጥቁር ደመና
ሰማይ ሲያጉረመርም በሚያስፈራ ቃና
ነጎድጓድ ሲነጉድ መብረቁም ሲባርቅ
የባህር ውሀ ሙሌት መሬት ሲያጥለቀልቅ
የምድሩ አፈር ወደ ጭቃ ሲቀየር
ሀይለኛው ንፋስ ሲያነቃንቅ አጥር
ለወራት ዘግቼ ከተቀመጥኩበት
ወጥቼ ብጠይቅ ምን ይሁን ይህ ክስተት
''ክረምት ገባ'' አሉ ቀዝቃዛው ወቅት
እውነትም አንቺዬ ክረምቱ ገብቷል
ልክ እንዳለፈው አመት በጊዜው መጥቷል
የሀገሬው ሰውም ወፋፍራም ልብስ
አድርጎ እሳት ዳር ተቀምጧል
እንስሳቶቹም ሙቀትን ፍለጋ
ዋሻቸው ከትመዋል
ለእኔ ግን እንደባለፈው አመት ልክ
እንደካቻምናው
የዘንድሮውም ክረምት ከበጋው የባሰ
የቀለጠ ሀረሩ ነው

ከሲኦል የባሰ በትዝታ ሲቃ የምሰቃይበት
ከኤርታሌው ፍም በላይ የምቃጠልበት
ከእሳት እንደተደፋ ጋዝ የምንቦገቦግበት
እልህ ከቁጭት ጋር ተደምሮ ይዞ
ልክ እንደተበላ በቁማር አስይዞ
እህህ እያልኩኝ በማያባራ እንባ
ትዝ እያለኝ ክህደትሽ በጋው እንደሚጠባ
እንዳለፈው ክረምት የዚህኛው አመት
መቃጠል ነው እንጂ ቅዝቃዜ የለበት
መቼም ፈርዶብኛል ከላይ ታዞልኛል
እሷን እያሰብክ ተቃጠል ብሎኛል
በጋው ከክረምት ጋር ተዘበራርቆብኛል
ሙቀትን ነው እንጂ ብርድን አላውቀው
እንዲህ ላደረገኝ ፍቅርሽ እድሜ ይስጠው

ግን እኮ አንዳንዴ
በበረሀ መሀል ያንዘፈዝፈኛል
በቀትሯ ፀሀይ ብርድ ብርድ ይለኛል
ቢሆንም ግን ከክረምቱ ይሻላል
በቀዝቃዛው ወራት በዝናቡ ጊዜ ትናፍቂኛለሽ
ያን ውብ የፍቅር ጊዜ ታስታውሽኛለሽ
መብረቁም ሲባርቅ ልቤ ሲደነግጥ ሳቅሽ ይታየኛል
እንደመብረቅ ብልጭታ የጥርስሽ ንፃት ይገርማል
የነጎድጎድ ድምፅ ማስፈራቱን ያህል
ያንቺም ድምፅ ይለያል
ውበት እና ለዛው እኔን ብቻ ስሙኝ አድምጡኝም ይላል
ንፋሱን ሳስበው ክህደትሽ ይመጣል
ልክ እንደሱ ፍጥነት እዚህ እዚያ ማለትሽ ያናዳል
ብቻ ምን አለፋሽ ብቸኛ ፍጡር ነኝ
በራሴ አለም ላይ እንደፈለኩ የምዋኝ
ያው እንደምታውቂው የሌሎቹ በጋ ለእኔም በጋ ነው
የሌሎቹ ክረምት ለእኔ ግን ሀሩር ነው
ምን ብዬ ላስረዳሽ ''ክረምት ገባ'' አሉ
ህመሜን ሳያውቁት ሳይገባቸው ሁሉ።


ሰላም ላንተይሁን
93 views15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 09:32:57 የአፍቃሪነት ፀጋ!
. (አኑ)

እኔ ከንቱ አፍቃሪ
ያፈቀርኳት ሁሉ ሸሽታኝ ትሄዳለች
ስትወደኝ የኖረች
አፈቀርኩሽ ስላት ጥላኝ ትጠፋለች
ያፈቀርኳቸው ሁሉ
ፍቅሬን ከመቀበል ሸሽተው ይሄዳሉ!
አሁን ለምሳሌ
ከአመታት በፊት
ፍቅር ማላቅ እኔ አንዲት ልጅ አፍቅሬ
ማፍቀሬን ሳልነግራት
ፍቅሬን በልቤ ላይ በድብቅ ቀብሬ
እየኖርን ሳለ
ከአይኖቿ የሚነበብ መውደዷ ነበረ
እንደምትወደኝ
በሴትነት ቋንቋ ትንግረኝ ነበረ
ይሁሉ ቢሆንም
ማፍቀሬን ስነግራት መውደዴን ሳበስራት
በፊት ማታውቀውን
አንዳች አይነት ጉራ አንዳች አይነት ኩራት
በራሷ ላይ ቀርፃ
ወደድኩሽ መባሏን ከጀግንነት ቆጥራ
በየካፍቴሪያው
ጠየቀኝ እያለች እኔን ታማኛለች ከሰው ተቀጣጥራ!
...
ቀጣዩ ህይወቴ ላይ
ማፍቀርን ጠልቼ ፣ ማፈቀርን ፈርቼ
ዳግም ላላፈቅር
ደግሜ ላልጠይቅ ምዬ ተገዝቼ
ጥቂት እንደቆየሁ
ከአንዲት ቆንጆ ሴት ጋር የያዘኝን ፍቅር
እስከ-ዘላለሙ
በዝምታዬ ውስጥ ልቤ ላይ ስቀብር
የቀበርኩት ፍቅሬ
እንደ ሲዖል እሳት እያንገበገበኝ
እቆያለሁ እንጂ
ፍቅሬን መናገሬ
ካፈቀርኳት ይልቅ
የማፍቀሬን ሀሜት አፏ ላይ ነው የማገኝ!
ይህ ሁሉ ባስብም
ያፈቀርኳት ቆንጆ ላግኝህ ስትለኝ
ባገኘችኝ ቦታ
ወደድኩህ እያለች የትም ስትስመኝ
ከማሳምም አልፋ
የሴትነት ክብሯን ለአንድ እኔ ስትሰጠኝ
አፈቀርኩህ ብላ
በፍቅር አምላኳ ምላ ስትነግረኝ
የቀበርኩት ፍቅሬ
በፍቅሯ ተረ'ቶ ማፍቀሬን ስነግራት
በፊት ያሌለባት
አንዳች አይነት ጉራ አንዳች አይነት ኩራት
በራሷ ላይ ፈጥራ
ላግኝህ እንዳላለች ነይ ላግኝሽ ስላት
ናፍቀሽኛል ስላት
እኔን ማግኘት ጠልታ
በየካፍቴሪያው በየሬስቶራንቱ ከማንም ተቃጥራ
ጠየቀኝ እያለች
እኔን ታማኛለች
የሳመኝን ከንፈር ለሀሜት ቀይራ!
.........
ይኸው ዛሬም ደግሞ
ሌላ ሴት አፍቅሬ ማፍቀሬን ልናገር
መልካም ሆነ መጥፎ
'እውነቱን ተናግሮ የመሸበት ማደር"
ከሚል ተረት ጋራ እኔኑ አሳምኜ
ማፍቀሬን አምኜ
አፈቀርኩሽ ብዬ ፍቅሬን እንዳወራሁ
በየካፍቴሪያው
በየሬስቶራንቱ
እንደ ምግብ ትዕዛዝ የራሴን ስም ሰማሁ!

ነግራቸው ነው እንደ
107 views06:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 23:36:18 ታሪክ ነው;

ማንም ሊያደበዝዘው የማይችል! በዘመን ውክብያ የማይጨልም!

መነሻችሁ ሐቅ ነበር! መስዋትነታችሁ እውነታ ነበረው! ትግላችሁ መራር ነበር!

ታሪክ ነው;

በቧልተኛ የማይደበዝዝ! በተሸናፊ ልሳን የማይቆሽሽ! በአድርባይ ልቡና የማይገመት!

ጀግኖች ናችሁ! ዓላማ ያነገባችሁ! ነፍስ የገበራችሁ! ትልቅ ናችሁ ትንሽ የማይነቀንቃችሁ!

ታሪክ ነው;

ተራራ አደለም ርኩስ መንፈስንም ታንቀጠቅጣላችሁ! ጅምራችሁ ሁሉ መልካም ነበር!

ታሪክ ነው;

እኔና ቤቴ ለዚህ ግዙፉ ለሆነው የታሪክ ሰነዳችሁ ዝቅ ብለን እጅ እንነሳለን!

ታሪክ ነው;
77 views20:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 23:36:08
74 views20:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 19:59:45 ስትኖር

ጤናህን ጠብቅ

ጤናህ የመጀመሪያዉና ወሳኙ ነገር መሆኑን ተረዳ

የራስህን ልክ እወቅ

የራስህንም ሆነ የሰዎችን ልክ ማወቅ በጣም ያስፈልጋል፡፡ አንድ ሰዉ መናገር ካልፈለገ እንዲናር አታስገድደዉ...መሄድ ካልፈለገ 'ለምን አልሄድክም?' ብለህ አትነዛነዝ፡፡

ለራስህ ክብር ስጥ

ሰዎች የምትፈልገዉንና ያልፈለከዉን ነገር ረግጠዉ ሊገቡ ሲሞክሩ አስቁማቸዉ ማንም ይሁኑ ምን በራስህ ላይ እንዲረማመዱ አትፍቀድ ።

ለራስህ እዉነተኛ ሁን

ሰዎችን ለማስደሰት ብለህ ተራራ አትዉጣ ድንጋይ አትቆፍር፡፡ ሰዎች በራሳቸዉ የማይረካ አይነት ባህሪ ሊያንፀባርቁ ስለሚችሉ ጊዜህን አታጥፋ ።

እራስህን ቻል

የራስህን ችግር በራስህ ፍታ፣ ቤትህን አፅዳ፣ ወጪህን በራስህ ሸፍን ብቻህን የምትኖር ከሆነ ምግብ ስራ፡፡ ‘ሚስት ቢኖረኝ እኮ...’የሚለዉን የስንፍና ምልክት አትጠቀም፡፡ ስለሚስት ሳይሆን እራስህን እንዴት ማሻሻል እንዳለብህ ተረዳ ።

ከሰዎች ጋር እንዴት መግባባት እንዳለብህ እወቅ

ሃሳብህን በተረጋጋና ስርአት ባለዉ መንገድ ተናገር ፣ ሰዎች ሲያወሩም ማዳመጥን ተማር

እድሎችን ተጠቀም

በወቅቱ ያልተጠቀምክበትን እድል መቼም ልትጠቀምበት አትችልምና ደፈር ብለህ ሃላፊነቶችን ዉሰድ

መዉደድን ተማር

ፍቅር መስጠትንና መቀበልን ተማር ፣ ይህ ልምድ ህይወት እንዳይሰለችህና ለሰዎች የማሰብ ባህሪን ታዳብርበታለህ ።

የሰነፍ አንደኛ አትሁን

በምትሰራዉ ስራ ይብዛም ይነስም ያለህን አቅም አሟጠህ ተጠቀምና ፍሬ አፍራ፡፡ ለራስህ ህይወት ሃላፊነቱን የሚወስደዉ ቤተሰብ፣ ጓደኛ፣ መንግስት፣ ሀገር ምናምን እያልክ ዉስጥህ የተቀጣጠለዉን ሃይል አታጥፋዉ፡፡ ዛሬን ተነስተህ ድከም...ነገ ታርፋለህ

ገንዘብን እወቅ

ገንዘብን እንዴት መቆጣጠር እንዳለብህ ከህይወትህ ልምድ፣ ካጋፈጡህ ችግሮች እንዲሁም ከተለያዩ ሰዎች ተረዳ ።

ተዝናና

ያለህን ጊዜ በሙሉ በስራና በትምህርት ብቻ ካዋልከዉ አንድ ቀን ምንም ደስ የምትሰኝበትን ትዉስታ ስላላሳለፍክ ይቆጭሃል፡፡ በመጠኑና በልኩ ተዝናና፣ አሪፍ ጊዜ ከቤተሰቦችህ፣ከጓደኞችህ ወዘተ ይኑርህ፡፡ ነገ ለልጆችህ እንዲህ ነበር ብለህ የምታወራዉን አሪፍ ትዝታ ቅረፅ ።
@t.me/yefkersew
74 views16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 15:45:35 እንዲሁ ስከተልሽ

እውነት

እግዜሩን አላውቀው
ከደጁ አልቀርበው
እንደሰው ሄጄ መሬቱን አልስመው
ወይ ፀሎት አላደርስ
ቅዳሴ አላስቀድስ
አባቴ ሆይ ማረኝ ብዬ እኔ አላለቅስ
ዳዊቱን ስደግም መች እኔ እገኛለሁ
ማህሌት ሰአታቱን በእንቅልፍ አልፋለሁ
እንዲህ እንዲህ እያልሁ እርሱን ረስቼ
መጠጥ ጭፈራ ቤት ተስቤ ገብቼ
አንድ ቀን አየሁሽ ከቅዱሱ ስፍራ
ነጠላን ጣል አ'ርገሽ ከምዕመናን ጋራ
አምላኬ ተመስገን
በደሌንም ማረኝ ስትይ ሰማሁሽ
ቀልቤን ገዛሽና እንዲሁ ተከተልኩሽ
አንቺ ካለሽበት
በደመነብስ ስቀርብ ራሴን አየሁት
ለእልፍ አእላፍ ዘመን ደርሶ የማያውቀውን
ከእግዜሩ ግቢ እግሬን አገኘሁት

ስብሀት ለአብ ለወልድ ለመንፈስቅዱስ ብዬ ተሳለምኩኝ
አንቺ እንዳደረግሺው
ከበሩ ሰግጄ መሬቱንም ሳምኩኝ
ካጠገብሽ ሆኜ ስብከቱን ሰማሁኝ
ስትወጪውም ከኋላሽ ተከትዬሽ ወጣሁ
ስምሽን ጠይቄ እንደምንም ተግባባሁ
ምስጋና ለፍቅርሽ
ቀና ብዬ አምላክን የ'ኔ አድርጋት አልሁት
ደግሜ ደግሜ ደግሜ ጠየቅሁት
እሱም አልጨከነ እንደኔ አይደለም
ለፀሎት ጥያቄ ምላሽ አልነፈገም
ወድጄሽ ነውና
አንቺን ፍለጋ እግርሽን ስከተል
አትጠፊም እና ቤተ ክርስቲያን ስውል
አጠገብሽ ቆሜ
ውዳሴን ከፍቼ ስቡህኒ ብለው
ዳዊትን ደግሜ
አምላኬ ሆይ ማረኝ ብዬ ብማፀነው
የ'ኔ እንዲያደርግሽ ማህሌቱን ብቆም
ፍቅርን ፍለጋ
ልብሽ አሸፍቶኝ ገዳማቱን ብዞር
በፀሎት በስግደት በፆም ውዬ ባድር
ንስሀ ገብቼ በይቅርታ ወደቅኩ
ከረሳሁት ጌታ በሂደት ተታረቅኩ
ለካ በምክንያት ነው አንቺን ያስወደደኝ
ባ'ንቺ ተማርኬ ከቤቱ እንድገኝ
ልብሽ አሸፍቶኝ እንዲሁ ስከተልሽ
ከተጣላሁት ቤት
ከአባቴ እርስት ዞሬ ገባሁልሽ።
69 views12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-05 16:22:10
68 views13:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-05 16:19:05 (ኢትዮጵያዬ)
''''''''''''''''''''''''''
ጋራ ላይ ሰቅለውሽ
አባቶች አያቶች በብርቱ ትከሻ
በምን ጉልበታችን
ወጥተን እንመርምረው ልክሽን ስንሻ..?
ዘመን እየገፋ
ቁልቁል የሰደደን ድንክዬ ልጆችሽ
እንዴት እንመልከት
ጋራውን አሻግረን ሲናፍቀን መልክሽ...?

አደራ እናት አለም
አንዴም ሳንገናኝ አንዴም ሳንተያይ
ምፅአት እንዳይመጣ
ዘም'በል በይልን
ቀን ፈቅዶ ከማማው
አፋፍ እስክንወጣ !
66 views13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-05 16:14:39 01) ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትወደቅ ማለት አይደለም
ወድቀህ መነሳትን ልመድ ማለት እንጂ!

02) ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም
ሌሎችን ለመስማትም ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ!

03) ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም
በሰዎች ሃቅ ላይ አትለፍ ማለት እንጂ!

04) አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም
ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ!

05) ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም
በሆድ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!

06) ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም
ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ እንጂ!

07) ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም
ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ!

08) ስራህን ወደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት
አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ወደድ
ማለት እንጂ!

09) ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም
ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ!

10) ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም
ምንም ቁም ነገር ሰትሳራ አትሙት ማለት እንጂ!

11) ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም
ልብህን ጊዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈህ ለመስጠት ዝግጁ
ሁን ማለት እንጂ!

12) እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነት ተናገር ማለት
አይደለም ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት እንጂ!

13) አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትጋጭም ማለት አይደለም
ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ!

14) ኩራተኛ አትሁን ማለት አትዘንጥ ማለት አይደለም
ሌሎችን አትናቅ ማለት እንጂ!

15) ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሸልክ ነህ ማለት አይደለም
አምሮብሃል ማለት እንጂ!

16) አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም
ብልህ ሁን ማለት እንጂ
68 views13:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ