Get Mystery Box with random crypto!

​​​​​​​​​​​​​​​​​​◈ ━━━⸙ ፍቅሬን በግጥM ⸙━━━━◈ አረ እግዜር በናትህ ፥ በጭን | ፍቅር 🄻🄾🅅🄴❤️

​​​​​​​​​​​​​​​​​​◈ ━━━⸙ ፍቅሬን በግጥM ⸙━━━━◈


አረ እግዜር በናትህ ፥ በጭንቅ አማላጇ
ባጠቡህ ጡጦቿ ፥ ባጎረሰህ እጇ
ወይ ህፃን ሆነህ ና ፥ ወይ ሙሴን ስደደው
የማንም ወጠጤ፤
የቃል ኪዳን ምድሯን ፥ ክብሯን አወረደው
ዳዊትን ላክልን ፥ ወይ ደግሞ ወንጭፉን
ጎልያዶች በዝተው፤
የሚመካከሩት ፥ መች እንደሚያጠፉን
እባክህ እግዜር ና፤
ወይ ሎጥን ፍጠረው ፥ ከመካከላችን
ዝም ያልህ እንደሆን፤
ነበር መሆኑ ነው ፥ ምድር ላይ ስማችን።

እኔን ባይ