Get Mystery Box with random crypto!

#ፀናለሁ ትመጣለች ብለዉ ተስፋ እያሰነቁኝ ስንት ጊዜ ነጋ ስንት ጊዜ መሸ ሳቅ እንደናፈቅሁኝ አ | ፍቅር 🄻🄾🅅🄴❤️


#ፀናለሁ

ትመጣለች ብለዉ ተስፋ እያሰነቁኝ
ስንት ጊዜ ነጋ ስንት ጊዜ መሸ ሳቅ እንደናፈቅሁኝ

አንቺ ግን
በናፍቆትሽ ገመድ ታስሮ 'ሚጠብቅሽ
በእንባ 'ሚታጠበው ያው ቡቡው አድናቂሽ

እንዲሉሽ ፈልገሽ
ልክ እንደመስቀል ወፍ ታይተሽ ትጠፊያለሽ

አበቦች ሲፈኩ ደምቀሽ ትመጪና ሲከስሙ ስትከስሚ
ስጠብቅሽ ውዬ ተስፋዬ ተሟጦ ጠርቼ ገጣሚ

"በል እንግዲህ ሆዴ ካለው ተላመድ
ቢያስሩበት አያጠብቅ በስባሳ ገመድ"

የሚለውን ስንኝ ከነፍሴ እንዲያዋህድ

እንድረሳሽ ብሎ ቅኔ እየዘረፈ ስንኝ ቢያሰናኝም
እንኳንስ ሊያስረሳኝ ትዝ አልሽኝ ሲገጥም

እናም እርሳኝ ካልሽኝ መርሳቱን አልችልም
ቀሰሩብኝ ብዬ ዓለሜን አልሰጥም
አስበኝ ካልሽኝ ግን አስታውሰኝ ካልሽኝ ግን እጠብቅሻለሁ ጊዜው ለ'ኔ እስኪቆም

ዓለሜን አፅድቆ የወል ሀቅ እስኪያረግ
ውጣ ቢሉኝ ገደል ውረድ ቢሉኝ 'ረግረግ
እከተልሻለሁ ዳንኤል ነኝ አልፈራም
እወድቅ ቢሆን እንጂ ከቶ አልሰበርም .


━━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━━