Get Mystery Box with random crypto!

➲ ኢትዮጵያ ሀገሬ እግዜር የባረከሽ ፣ የቅኔዎች አድባር ስምሽ ይጣፍጣል ፣ ልክ እንደ ወለላማር | ፍቅር 🄻🄾🅅🄴❤️

➲ ኢትዮጵያ ሀገሬ

እግዜር የባረከሽ ፣ የቅኔዎች አድባር
ስምሽ ይጣፍጣል ፣ ልክ እንደ ወለላማር

የፍጥረት አውድማ ፣ የመኖር ሚስጥሬ
አንቺ ብቻ እኮ ነሽ ፣ ኢትዮጵያ ሀገሬ።

ባለብዙ ምስጢር ፣ በስመገናና
ታሪክሽ ተፅፏል ፣ በደማቅ ብራና

ትውልድሽም ሳይቀር ፣ በጥበብ ታንጿል
ሰንደቅሽን አስሮ ፣ ዘመቻ ጀመሯል።

የቃልኪዳን ምድር፣ ለነፃነት ቋሚ
ወትሮም ከጥንት ነሽ ፣ አንደኛ ቀዳሚ።

አምሳለ ገነት ሆይ ፣ ውዲቷ እናቴ
እስቲ ልመርቅሽ ፣ እኔም በአንደበቴ

እዮብን አይተሽው ፣ ከልብሽ ተፅናኚ
እንባሽን አብስሽ፣ ተስፋሽን ጠግኚ

በሄድሽበት ሁሉ ፣ ፈጣሪ ይከተልሽ
ከስንፍና ይልቅ ፣ ልቦናውን ይስጥሽ

መልክሽም ይታደስ ፣ እንደ አደይ አበባ
ፈፅሞ አይንካሽ ፣ የውድቀት ገለባ

ወታደሮችሽም ፣ መንገዱ ይቅናቸው
እንክርዳዱ ቀርቶ፣ ስንዴው ይግጠማቸው።

ቤዛዊት ታፈሰ