Get Mystery Box with random crypto!

የስኬት ምስጢሮች

የቴሌግራም ቻናል አርማ sucesssecret — የስኬት ምስጢሮች
የቴሌግራም ቻናል አርማ sucesssecret — የስኬት ምስጢሮች
የሰርጥ አድራሻ: @sucesssecret
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.35K
የሰርጥ መግለጫ

የሁሉም ስኬት መጀመሪያ ነጥብ ያለው ፍላጉት ላይ ነው ።የመለወጥ ጠንካራ ፍላጎት ያለቻው ሰዎች አእምሮአቸውን ይጠቃሙባታል
በቻናላችን ላይ ትላልቅ የስኬት መሪህዎችን ታገኛለችሁ ሼር አድርጉ ይቀላቀሉም።
እንዲሁም በነፃ የማማከር አገልግሎትም እንሰጣለን (0972707274)። ስልጠናዎችን በኦዲዮ ፣ በቪድዮ እና በፁሁፍም ይቀርባሉ።

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-08 20:24:49 ካነበብኩት የወደድኩት ድንቅ እይታ

"ይህም ያልፋል"
በአንድ ወቅት ነበር አንድ ሰው የሰው ማሳ ተከራይቶ ሲአርስ አንድ መንገደኛ አይቶ ይጠይቀዋል የአንተ ማሳ ነውን?ይለዋል አይ ተከራይቸ እያመረትኩ ነው ይህም ያልፋል ይለዋል፤

በዓመቱ ይህ ገበሬ የራሱ ማሳ ኑሮት ነገር ግን በሬ ስለሌላው በአዷማ እየቆፈረ ያ ሰውዬ አየው ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ የቀደመ ጥያቄውን ጠየቀው ሰውዬውም መልሱ ይህም ያልፋል ነበር።

አሁንም በሌላ ግዜ እነዚህ ሰወች ተገናኙ ገበሬው በሬ ኑሮት አርሶ አዝምሮ አውድማ ላይ እየወቃ ያ መንገደኛ ሰውዬ መጣ አሁንም ይህም ያልፋል አለው ሰውዬውም በመልሱ ተገርሞ ሄደ።

ከጥቂት አመት በኃላ አገሪቱ ከተማ ሁና ያ ገበሬም ሆቴል ገንብቶ ተገናኙ ሰውዬውም ይህ የማነው ብሎ ጠየቀ ያ ቀድሞ የሚያውቀው የዛ ገበሬ ነበር ፌት ለፊትም እዛው ሆቴል ውስጥ ተገናኝተው ተጠያየቁ ይህም ንብረት ያልፋል ብሎ መለሰለትና ተለያዩ ፤

በአመቱ የዚያች ሀገር ሰዎች ተሰብስበው ይህ ሰው ትኁትና ታዛዥ በዚያውም ላይ ቅን ሰው ነው ስለዚህ የከተማዋ ከንቲባ ሆኖ ያገልግለን ብለው ሹመውት ተገናኙ ድሮ እንደሚለው ይህም ስልጣን ያልፋል አለው አሁንም ዛሬ ስልጣን ላይ ተቀምጦ እንዲህ ይለኛል ብሎ ተገርሞ ሄደ።

ከብዙ አመታት በኃላ ያ መንገደኛ መጥቶ የዚህች ሀገር ከንቲባ የት ሄዶ ነው ብሎ ጠየቀ ሲጠይቅ እንደ ሞተ ነገሩት ወደ መቃብሩም እንዲወስዱት ጠይቆ ወሰዱት በመቃብሩም ላይ ይህም ያልፋል የሚል ቃል ተፅፎ አገኘ እንዴ ከሞት በኃላ ደግሞ ምን አለ ብሎ ነው ይህም ያልፋል ያፃፈ ብሎ ሊቃውንትን ጠየቀ እነሡም አስረዱት ይህ ያየኀው ስጋዊ ሞት ያልፋል የማያልፋል የፈጣሪ መንግስት ብቻ ነው ብለው አስተማሩት።

አንዳንዴ እንደ ተራራ የከበደን ሀዘን አልፎ በደስታ ይተካል ችግራችን በዝቶ ተስፋ በቆረጥንበት ወቅት ይህም እንደሚያልፍ እንገንዘብ።

ሁሌም አመስጋኝ እንሁን

ሼር
https://t.me/SucessSecret
https://t.me/SucessSecret
714 viewsMasresha, 17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 11:10:43 አንድ እውነተኛ ታሪክ ላካፍላቹህ ወደድኩ
ወክቱ ክረምት ነው ሃይለኛ ዶፍ ዝናብ እየዘነበ ነበር ታደ ሃይለኛ ዝናብ እየዘነበ አንድ ወጣት መኪናውን እየነደ ወደቤቱ ሲገባ ከመንገዱ ዳር የቆሙ አንድ አባት ነበሩ ሃይለኛው ዶፍ እየቀጠቀጣቸው ባየ ሰአት ልቡ እራራና አባት እሄሁሉ ዶፍ እንዴት ችለውታል የለበሱት ልብስም በጣም ቀጭን ነው ብርድ መቋቋም አይችልም ሲላቸው እኚ አባት እንዲህ ሲሉ መለሱለት አይ ሊጄ ለረጅም አበ
መት ከዝናቡጋር ተግባብተን ለምጄዋለሁ አሉት ።
ቆዩ ከቤት ወፈር ያለ ልብስ ብርድን ሊቋቋም የሚችል ልብስ ላምጣሎት ብሎ ወደቤቱ ገባ ተስፋ ሰጣቸው ታደ የሃብታም ነገር ብዙወዳጆች አሉት እና እቤት ሲገባ እቤት የመጡ እንግዶች ነበሩ በወሬ ይዘውት እርስት አድርጎ መሽቶ ሲነጋ ከእንቅልፉ ሲነቃ ማታ ቃል የገባላችው አባት ትዝ አሉት እና እየሮጠ ሲወጣ እኚ አባት ሞተው ያገኛቸዋል ታደ እኚ አባት ምን ብለው ደብዳቤ ፃፉለት ለረጅም አመት አይምሮዬን አሳምኜው ብርድና ዶፍን ተቋቅሜ የኖርኩ ሰው አንተ መተህ አዲት ቃል ተስፋ አድርጌ. ብርዱን መቋቋም አቅቶኝ ሞትኩኝ ብለው ነው የፃፉለት ታደ ስንቶቻችን ነን አንተ አትችልም አንተ እዲህ ነህ ተብለን ወደ ስኬት እንዳንደርስ የያዙን ቃላቶች ለቃላቶች እንጠንቀቅ ከራሳችንም አንደበት ከአፋችን በሚወጣው ቃላቶች ለሰዎች የምንናገረው ቃላቶቻችን በሙሉ ቀና መሆናቸውን ቼክ እናድርግ!!!
855 viewsMasresha, 08:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 11:07:20 በትንሽ ድንጋይ እስክትመታ አትጠብቅ!! #ይነበብ

የኮንስትራክሽን ተቆጣጣሪው ከ 6ኛ ፎቅ ላይ ሆኖ መሬት ላይ የሚስራውን ሰራተኛ ይጠራዋል፣ ስራተኛው ሊስማው አልቻለም፡፡ ስራተኛው የአሰሪውን ጥሪ ሊስማው ስላልቻለ ተቆጣጣሪው መላ ዘየደ

እናም የሰራትኛውን ሃሳብ ልማግገኘት ሲል ተቆጣጣሪው ከላይ ብር ጣለለት ብሩም ከሰራተኛው እግር ስር አረፈ፣ ሰራተኛው ብሩን አንስቶ ወደ ኪሱ አሰገብቶ ስራውን ቀጠለ በድጋሜ የሰራተኛውን ሃሳብ ለማግኘት ተቆጣጣሪው መጀመሪያ ከጣለው ብር በላይ ሌላ ብር ጨምሮ ጣለለት፣ የቀን ሰራተኛውም ልከ እንደ መጀመሪያው ብሩን አንስቶ ወደ ኪሱ አስገብቶ ስራውን ቀጠለ፡፡

በመጨረሻ ሌላ መላ ዘየደ ብር በመጣል የሰራተኛውን ሀሳብ ማግኘት ስላልቻለ የሰራተኛውን ሃሳብ ለማግኘት አነስ ያለ ድንጋይ አነሳና ወደ ሰራተኛው ወረወረው፣ ድንጋዩም የሰራተኛውን ጭንቅላት አገኝው በዚህ ሰዓት ነበር ሰራተኛው ወደ ላይ የተመለከተው እና ከተቆጣጣሪው ጋር መነጋግር የጀመረው፡፡

ይሄ ታሪክ ከእኛ ህይወት ጋር ይመሳሰላል ፈጣሪ ከኛ ጋር መገናኘት ይፈልጋል ነገር ግን እኛ በጣም በ አለማዊ ስራ ራሳችንን ጠምደናል ከዛ ፈጣሪ ትንሽ ስጦታ ይሰጠናል እኛም ስራችንን እንቀጥላለን ከየት እንዳገኘነው ቀጥ ብለን ለማየት ጊዜ የለንም፡፡

በድጋሜ ፈጣሪ ከመጀመሪያው የተሸለ ስጦታን ይሰጠናል አሁንም ልክ እንደ መጀመሪያው ስጦታውን ወስደን ምስጋናም ለፈጣሪ ሳናቀርብ እድልኞች ነን ብቻ ብለን ስራችንን እንቀጥላልን ከየት እና ከማን እንዳገኘነው ቀና ብለን ለማየት አንሞክርም፡፡

እናም በትንሽ ድንጋይ ስንመታ፣ ማለት ትንሽ ችግር ቢጤ ስታገኘን ወደ ላይ ማየት እና መጮህ ከዚያም ከፈጣሪ ጋር መነጋገር እንጀምራለን፡፡ ስለዚህ ምንግዜም በህይወታችን ስጦታን ስናገኝ በፍጥነት ፈጣሪን ማመስገን አለብን በጭራሽ በትንሽ ድንጋይ እስክንመታ መጠበቅ የለብንም ሁሌም ቢሆን ከፈጣሪ ጋር እንገናኝ፡፡

#እግዚአብሔር ፍቅር ነው
#እግዚአብሔር መልካም ነው
#እግዚአብሔር የልብን መሻት ይፈፅማል
#ግን እስኪ ልክ እደ ሰራተኛው ድንጋይ እስኪጣልብን አንጠብቅ

ሼርርርር
ምርጥ መጣጥፎች
908 viewsMasresha, 08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 22:51:27
ብዙችዎች ምን እየሰራህ ነው የሚልጥያቄ ያላችሁ ጓደኞቼ እነሆ በዚህ ፕሮግራም በሰዓቱ ተገኙ እና እዩ! የዊዝደም ቲም NBO(New Business Orientation)
22 # በሆሊዳይ ሆቴል
እሑድ ሐምሌ24, ጠዋት2:30ጀምሮ!

ቲኬቱን ቀድሞ ይያዙ ውስን ቦታ ነው የለን

ለበለጠ መረጀ 0972707274
820 viewsMasresha, edited  19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 22:44:16
እንኳን ደስ አላችሁ
#በዊዝደም ቲም የተዘጋጀ የፊታችን እሁድ ሀምሌ/24/2014 ድንቅ የNBO ስልጠና በሆሊደይ ሆቴል ከጥዋቱ 2:30-11:00 ጀምሮ ያካሄዳል። በእለቱ ልክ እንደ ሀበሻ በሰዓቱ በመገኘት አእምሮውን ይመግቡ።"በጥበብ መስረት ብልህነት ነው'' ዊዝደም ቲም

ቲኬቱን ቀድሞ ይያዙ ውስን ቦታ ነው የለን
639 viewsMasresha, edited  19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 21:56:10 #ከፈሰሰ_አይታፈስ..

አንዲት ወጣት ሴት ለጉዞ ኤርፖርት ዉስጥ ተቀምጣለች። በመንገደኞች የመጠበቂያ ክፍል የምትሄድበትን አዉሮፕላን ትጠብቃለች። አዉሮፕላኑ እንደሚዘገይ ባወቀች ጊዜ ኤርፖርት ዉስጥ ካሉት ሱቆች ኩኪስና መፅሐፍ ገዛች። መጠበቂያ ወንበር ላይ ተደላድላ ተቀምጣ ማንበብ ጀመረች። አጠገቧ እንዲሁ አንድ ሰዉ መፅሔት ያነባል። በሁለት ወንበሮች የጋራ መደገፊያ ላይ ኩኪስ ተቀምጧል። በንባቧ መካከል መተከዣ ሁኗታል። ታድያ ከኩኪሱ አንድ ስትወስድ አጠገቧ የተቀመጠዉ ሰዉዬ አንድ አነሳ። ገረማት።
ሳያስፈቅዳት እንኳ መዉሰዱ አስደነቃት።
ግን ዝም አለች። ቀጥላ እርሷ አንድ ስትወስድ እርሱም ሌላ ወሰደ። አሁን ተበሳጨች። ድፍረቱ አናደዳት። በዚህ አላበቃም፣ እስከ መጨረሻዉ ቀጠለ።
ቅጥል አለች። ግን ንቃ ተወችዉ። በአካባቢዉ ያሉ ሰዎችን አትኩሮት መሳብ አልፈለገችም። ለዚህ ብቻ አይደለም በኩኪስ ምክኒያት ለሚነሳ ረብሻ ሰበብ መሆን አልወደደችም።

እንዲህ...እንዲህ እያለ የመጨረሻዉ አንዲት ኩኪስ ቀረች። ይህ የተረገመ ሰዉ ምን ያደርግ ይሆን? ስትል አሰበችና በቀስታ ማየት ጀመረች። ከዚያም ሰዉየዉ ኩኪሷን ሁለት ቦታ ከፈላትና ግማሹን ወሰደ። ለድፍረቱ ጥግ አጣችለት። ከልክ ያለፈ ስራዓት የለሽ እንደሆነ ደመደመች።

አዉሮፕላን ዉስጥ እንደገባች መነፀር ለማዉጣት ቦርሰዋን ስትከፍት አይኗን ማመን አልቻለችም። ያልተከፈተ የታሸገዉ ኩኪሷ ቦርሰዋ ዉስጥ አለ።
በጣም አፈረች። ተሸማቀቀች። ለካ የእርሷን ኩኪስ ቦርሰዋ ዉስጥ ረስታዉ የሰዉየዉን ነበር ስትበላ የቆዬችዉ።
ከሁሉም በላይ ያፀፀታት ሰዉዬዉ እስከ መጨረሻዉ አንዲት ኩኪስ ድረስ ያካፍላት የነበረዉ ምንም ሳይቆጣና ሳይመረር በደስታ መሆኑ ነበር።

የራሱን ኩኪስ እየተካፈለች ሰዉየዉ ላይ ስትበሳጭበት በመቆየቷ እጅግ አፈረች።
አሁን ይቅርታ ለመጠየቅ እንኳ ጊዜዉ አልፏል። እርሱም በሌላ አዉሮፕላን ወደ ሀገሩ አቅንቷል። እርሱን የማግኘት አንድ ተጨማሪ እድል እንኳ የላትም። ብዙ ተመኘች። ማመስገን፣ ይቅርታ መጠየቅ።
ጉዳዩን ማብራራት...ፈለገች ግን ሁሉም እርሷ ጋ ቀሩ...አልፏል።

አራት የማይጠገኑ ነገሮች አሰበች፦

ድንጋይ ከተወረወረ በኃላ
ቃላት ከተናገርናቸዉ በኃላ
ድርጊቶች ካመለጡን በኃላ
ጊዜ ካለፈ በኃላ

ከፈሰሰ...አይታፈስ።

እንደዚች ሴት የህይወት ቦርሳችንን እንክፈተዉ።
እስካሁን ስንበላዉ የነበረዉ የሌሎች መሆኑን፣ የምንበሳጨዉም ትክክለኛ ባልሆነ ነገር መሆኑ ይገባናል።
የእኛ እንደታሸገ ነዉ፣ የሰዎቹን ግን ጨርሰናል። እኛ ከትርፋችን የማንሰጣቸዉ ሰዎች እነርሱ ግን አንዱን ለሁለት ቆርሰዉ አካፍለዉናል።
የብዙዎች መልካምነት የሚታወቀን ካጠገባችን ከሄዱ በኃላ ነዉ። ብዙ ባሎች የሚስታቸዉን ደግነት ያወቁት ስትሞት ነዉ። ብዙ ሚስቶች ባላቸዉን ያመሰገኑት ሲሞት ነዉ። ነገር ግን ቁጭቱ ሃይለኛ ነዉ። እንደዉም እኛ ኢትዮጵያዉያን ሰዉ ካልሞተ እና ለቆ ካልሄደ አናመሰግንም። ይህ ሀገራችንን የጎዳ ክፉ ባህላችን ነዉ። እንደዉም እንደ ሀገር ስናስብ ሙት አንግሶች ነን ማለት ይቻላል።
ለማንኛውም አስተዉሉ ዛሬ የምንበሳጨዉና የምንቆጣዉ ምን አልባት ባለማዎቅ ሊሆን ይችላልና በኃላ እንዳናፍር አስቀድመን እንጠንቀቅ።

ሁለት ሰዎች ተጣልተዉ አንደኛዉ ዶክተሩን “አንተ መሃይም” እያለ ሊመታዉ ይጋበዛል። አለቃ ገብረ ሀና ደረሱና ለማስታረቅ ቀኝ እና ግራ አስቀምጠዉ ሲዳኙ አንድ ሰዉ ሲያልፍ አይቷቸዉ አለቃ ገብረ ሀና ምን እያደረጉ ነዉ? ቢላቸዉ፦ “ስድብ ቦታ ተለዋዉጦ ቦታ ቦታዉ እየመለስኩ ነዉ”አሉ ይባላል።

ዛሬም ወቀሳ ቦታ ተለዋዉጧል፣
ምስጋናም ያለ ቦታዉ ይነጉዳል።

አንድ ቀን ሁሉም ወደ ቦታዉ ይመለሳል።
አምባሳደር ሚዲያ
እፁብ ድንቅ ሚሽት ይሁንልን!
#ወደዱት፡ ለሌሎችም #ሼር በማድረግ አካፍሉ፡፡
https://t.me/SucessSecret
https://t.me/SucessSecre
617 viewsMasresha, edited  18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 11:04:29 ቅን አሳቢ የሆኑ ሰዎች ይኼንን አስተሳሰባቸውን ከማጠናከርም በላይ ከመመረዝና ከመበከል በቻሉት መጠን ይጠብቁታል።
638 viewsMasresha, 08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 06:16:09
በሕይወታችን አብዛኛዎቹ ነገሮች ልክ እንደጽንስ ናቸው፡፡ ጽንስ ገና እንደተፈጠረ ወይም የመወለጃው ወቅት ሳይደርስ አይወለድም፣ ቢወለድም ወይ ጎዶሎ ሆኖ ይኖራል ወይም ደግሞ ካለጊዜው ስለተወለደ ካለጊዜው ይሞታል፡፡

ጽንስ በጽንስነት ዘመኑ በቂ ጊዜን ካሳለፈ በኋላ እውነተኛውን አለም ለመቋቋም የሚችልበት ደረጃ ሲደርስ ነው መወለድ ያለበት፡፡ ጊዜው ሲደርስ ደግሞ እኛ ሳንገፋው ራሱ ገፍቶ መምጣቱ አይቀርም፡፡

ብዙ ነገራችን የሚበላሽብን ካለጊዜው ለመውለድ ስለምንሞክር ነው፡፡ ጓደኛን እንይዛለን፣ ጓደኝነቱ ፍቅርን ጸንሶ፣ ጽንሱ ደግሞ ጊዜውን ወስዶ በተፈሯዊው መንገድ እንዲወለድ ጊዜ አንሰጠውም፡፡ ስለዚህም እናጣድፈዋለን፣ ቶሎ እንዲፈጠር እንፈልጋለን፣ እንወልደዋለን፡፡ የተፈጥሮን ሂደት ተከትሎ አድጎ እንዲወለድ ጊዜን ከመስጠት ይልቅ አዋክበን ወደመኖር ልናመጣው እናግለበልበዋለን፡፡ ከዚያም ካለጊዜው የተወለደን አንካሳ፣ ሰባራና ጤናቢስ ነገር ይዘን መላው ይጠፋብናል፡፡

ያለን ማሕበራዊ ግንኙነት፣ ስራ፣ ንግድም ሆነ ሌሎች ነገሮቻችን የዚህ መርህ ተገዢ ናቸው፡፡ አንድን ነገር ከጀመርን በኋላ ነገሩ ተፈጥሯዊውን ሂደት እስኪጨርስ መታገስ አስፈላጊ ነው፡፡

ይህንን የተፈጥሮ ሂደት መከተል እውነተኛውን ከውሸተኛው ሕይወት ያለውን ከሌለው የምንለይበት ብቸኛ መንገድ ነው፡፡


በምድር ላይ የምናደርጋቸው መልካም ነገሮች ሁሉ በሰማይ ላይ የዘላለም ደመወዝ ሆነው ይከፈሉናል፡፡ ሁሌም ቢሆን ከክፋት ይልቅ በጎ በጎውን ነገር እናስብ መልካምነት ለራስ ነው፡፡

መልካም ቀን!
እፁብ ድንቅ ቀን ይሁንልን!
#ወደዱት፡ ለሌሎችም #ሼር በማድረግ አካፍሉ፡፡
https://t.me/SucessSecret
https://t.me/SucessSecre
707 viewsMasresha Debele, edited  03:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 08:47:54
Formal education will make you a living; self-education will make you a fortune. Jim Rohn
ራስን ማስተማር፣ራስ ላይ መስራት ሁለንተናዊ እድገትና ሀብት እንድታመጣ ትልቁን ድርሻ ይወስዳል። ለዚህ ደግሞ የበርካቶች ህይወት ላይ በጎ የሆነ ለውጥ እንዲያመጡ እያደረገ ያለው ቅንመድረክ የግል ስብዕና ማበልፀጊያ ስልጠና ፕሮግራም ትክክለኛው ቦታ ነው። ቅዳሜ ጠዋት ቀጠሮዎ ከቅንመድረክ ጋር ይሁን። ሁላቹም ተጋብዛችኋል። በፍፁም እንዳያመልጦ!
ለበለጠ መረጀ በዚህ ስልክ
ይደውሉ 0972707274
128 viewsMasresha, edited  05:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 08:03:57 በዜሮ የተባዛው አገልግሎት!

አንድ ንጉስ አስር አመት ሙሉ በታማኝነት ያገለገለው አገልጋዩ እንዲት ስህተት ስለሰራ ብቻ ቅጣትን አስተላለፈበት፡፡ በንጉሱ ሕግ መሰረት ማንኛውም ስህተት የሰራ አገልጋይ በኃይለኛነታቸውና በተናካሽነታቸው የታወቁት የንጉሱ ውሾች ወደሚኖሩበት ግቢ ለቅጣት ታልፎ ይሰጣል፡፡

ይህንን የንጉሱን ውሳኔ የሰማው ታማኝ አገልጋይ በሁኔታው በጣም አዘነ፡፡ እሱን ያሳዘነው የተላለፈው ቅጣት ሳይሆን፣ ለአስር አመታት ካለምንም ስህተት አገልግሎ፣ አንዲት ስህተት ብቻ ስለተገኘችበት የንጉሱ መጨከን ነው፡፡

ይህ አገልጋይ ቁጭ ብሎ፣ “ይህንን ቅጣት አስቀረሁትም፣ አላስቀረሁት ንጉሱ ግን ይህንን ጥሩ ያልሆነ ልምምድ የሚያቆምበትን አንዲት ትምህርት ባስተምረው ደስ ይለኛል” ብሎ አሰበና አንድ ብልሃት መጣለት፡፡

ንጉሱንም፣ “ቅጣቱን እቀበላለሁ፣ ቅጣቱ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ግን አስር ቀን ይሰጠኝና ከዚያ በኋላ በፈቃዴ ለቅጣቱ እመጣለሁ” ብሎ ጠየቀው፡፡ ንጉሱም ፈቀደለት፡፡

በእነዚህ አስር ቀናት ለውሾቹ የሚሆንን ምግብ አዘጋጅቶ እነሱ ያሉበት ግቢ በመሄድና ቀስ ብሎ በመቅረብ እያበላቸው፣ እየተንከባከባቸውና እያሻሻቸው በሚገባ ካገለገላቸው በኋላ በአስረኛው ቀን ወደ ንጉሱ መጣ፡፡ ፍርዱ አልቀረለትም ነበረና ወደውሾቹ ግቢ እንዲጣል ትዝዛዝ ተላለፈበትና ተጣለ፡፡ ውሾቹ ለአስር ቀን የተንከባከባቸውንና ያገለገላቸውን ይህንን ሰው ምንም ነገር አላደረጉትም ነበር፡፡

ንጉሱም ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተ ሁኔታ በመሆኑ ተገርሞ አስጠራውና የተፈጠረውን ጠየቀው፡፡ አገልጋዮም፣ “ንጉስ ሆይ፣ እርሶን አስር አመት በታማኝነት አገልግዬ አንዲት ጥፋት ስለተገኘብኝ ብቻ ያ ሁሉ ታማኝነቴና አገልግሎቴ ተረሳና ምህረትም አላገኘሁም፡፡ እነዚህ ውሾች ግን ለአስር ቀናት ብቻ ስላገለገልኳቸው ምንም እንኳን ጥፋተኛ ሆኜ ለእነሱ ታልፌ ብሰጥም ያንን አገልግሎቴን ባለመርሳት ምንም አላደረጉኝም” አለው ይባላል፡፡

ንጉሱ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ይህንን ባህሪውን ለማረም ክፍት ወደመሆን እንደመጣ ይነገራል፡፡

ሰዎች ያሳዩንን የብዙ ዓመታት ታማኝነትና አገልግሎት በአንዲት ስህተት ምክንያት በዜሮ አናባዛው፡፡ ይቅርታን እንልመድ! ለሰዎች ሁለተኛ እድልን መስጠትን እንልመድ! ውለታ ቢሶች አንሁን!

መልካም ቀን!
እፁብ ድንቅ ቀን ይሁንልን!
#ወደዱት፡ ለሌሎችም #ሼር በማድረግ አካፍሉ፡፡
https://t.me/SucessSecret
https://t.me/SucessSecre
236 viewsMasresha Debele, edited  05:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ