Get Mystery Box with random crypto!

የስኬት ምስጢሮች

የቴሌግራም ቻናል አርማ sucesssecret — የስኬት ምስጢሮች
የቴሌግራም ቻናል አርማ sucesssecret — የስኬት ምስጢሮች
የሰርጥ አድራሻ: @sucesssecret
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.35K
የሰርጥ መግለጫ

የሁሉም ስኬት መጀመሪያ ነጥብ ያለው ፍላጉት ላይ ነው ።የመለወጥ ጠንካራ ፍላጎት ያለቻው ሰዎች አእምሮአቸውን ይጠቃሙባታል
በቻናላችን ላይ ትላልቅ የስኬት መሪህዎችን ታገኛለችሁ ሼር አድርጉ ይቀላቀሉም።
እንዲሁም በነፃ የማማከር አገልግሎትም እንሰጣለን (0972707274)። ስልጠናዎችን በኦዲዮ ፣ በቪድዮ እና በፁሁፍም ይቀርባሉ።

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-05 06:54:01 ጥበበኛዋ ትል

አንዲት ትል ከአንድ ረጅም ዛፍ ስር ሆና ወደ ላይ ስትመለከት ዛፉ በማፍራት ላይ ያለውን ፍሬዎች በመመልከቷ ከፍሬው ለመመገብ ወደ ዛፉ ላይ የመውጣትን ጉዞ ጀመረች፡፡

በእሷ ፍጥነት (ዝግመት) ዛፉን ወጥታ ያሰበችበት ለመድረስ ረዘም ያለ ጊዜ እንደሚፈጅ ከተሞክሮ ብታውቀውም በጣም የምትወደውን ዜማ እያንጎራጎረችና ወደላይ በወጣች ቁጥር በበለጠ ሁኔታ እየታያት የመጣውን የአካባቢ ገጽታ እያየች በደስታ ዳገቱን ተያያዘችው፡፡

ብዙም ሳትርቅ ከዛፉ ላይ ወደታች የምትወርድ አንዲት ምንነቷ በውል ያልታወቀ እንስሳ ቆም ብላ፣ “ወደየት ነው እንደዚህ በደስታ እየተፍለቀለቅሽ የምትሄጂው አለቻት”፡፡

ትል፣ “ዛፉ ጫፍ ላይ ያለውን ፍሬ ልበላ” አለች፡፡

እንስሳዋም፣ “እኔ ከዚያ ነው የመጣሁት፣ ፍሬዎቹ ገና አልበሰሉምና አትልፊ፡፡ ሲቀጥል ደግሞ አጉል ደስተኛነትና አዎንታዊነት አያጥቃሽ ጉዞው ቀላል እንዳይመስልሽ፣ ስለዚህ ብትመለሺ ይሻልሻል” አለቻት፡፡

ትሏም፣ ቆም ብላ እዚያ ለመድረስ የሚፈጅባትን ጊዜ ካሰላች በኋላ፣ “ችግር የለውም፣ እዚያ እስከምደርስ ድረስ ፍሬዎቹ ይበስላሉ” በማለት ጉዞዋን ቀጠለች፡፡

ያሰብከው ከፍታ ለመድረስና የለፋህበትን ፍሬ ለማግኘት . . .

1. ዓላማህን ከጊዜ ጋር አጣጥመህ እቅድ አውጣ
ከሁሉ በፊት ለመድረስ የምትፈልግበትን የዓላማ ከፍታ ወስን፡፡ ከዚያም፣ እዚያ ዓላማህ ጋር ለመድረስ የሚፈጅብህን የጊዜ ሁኔታ አስላና ሁለ-ገብ እቅድ አውጣ፡፡ ሁለ-ገብ እቅድ ማለት፣ እንደ አንተ ሁኔታ ገንዘብን፣ ትምህርትን፣ እድሜን . . . ያካተተ ሊሆን ይችላል፡፡

2. የሰዎችን ሃሳብ አመዛዝን
ሁል ጊዜ ከፍ ያለ እቅድ ስታወጣና መንቀሳቀስ ስትጀምር ተቃራኒውን የሚነግሩህ ሰዎች እንደሚያጋጥሙህ አትርሳ፡፡ አንዳንዶች ለአንተ አስበው በቅንነት፣ ሌሎቹ ደግሞ በአንተ ላይ አስበው በምቀኝነት፡፡ በጭፍንነት ከሰማሃቸው ውጤቱ ያው ስለሆነ ሁለቱንም ቢሆን በጥንቃቄ ማስተናገድ አስፈላጊ ነው፡፡

3. በጉዞው ተደሰት
ወደ ዓላማህ በአንተ አቅምና ፍጥነት ስትጓዝ ፍጻሜው ላይ የመድረስን ደስታ እስከምታገኝ አትደበር፡፡ የጉዞ ደስታ የሚባልም ነገር እንዳለ አስብ፡፡ የመድረስ ደስታ ዓላማህ ላይ እስከምትደርስ ድረስ ያስጠብቅሃል፡፡ የጉዞው ደስታ ደግሞ አሁኑኑ በመደሰት ለጉዞው ጉልበትን ይሰጥሃል፡፡

በማንኛውም ጉዞህ ውስጥ “የምታዜመውን ዜማ” ፈልግ፣ የምትስቅበትን ምክንያት ፍጠር፣ ዙሪያህን እየቃኘህ ተደሰት፡፡ ጉዞው የፍጻሜውን ያህል አስፈላጊ ነውና፡፡

ያሰብከው ደረጃ መድረስህና ፍሬህን መብላትህ አይቀርምና፣ በፍጹም እንዳትቆም!!!

አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ልማድ፣ አዲስ ውጤት!

መልካም ቀን!

እፁብ ድንቅ ቀን ይሁንልን!
#ወደዱት፡ ለሌሎችም #ሼር በማድረግ አካፍሉ፡፡
https://t.me/SucessSecret
https://t.me/SucessSecre
320 viewsMasresha Debele, edited  03:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 06:53:41
250 viewsMasresha Debele, 03:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 08:02:03 ለመፍረድ_አንቸኩል !
ዶክተሩ ስልክ ይደወልለትና እየሮጠ ወደ ሆስፒታል ይሄዳል፡፡ሆስፒታል ከደረሰ ቦሀላ ልብሱን በፍጥነት ቀያይሮ ወደ ኦፕራሲዮን ክፍል እየተጣደፈ ሲሄድ መግቢያ በሩ ላይ ቆሞ ይጠብቀው የነበረ የታማሚው ልጅ አባት "እንዴት እዚህ ለመድረስ ይህን ሁሉ ሰአት ይፈጅብሀል ዶክተር? የሰው ህይወት ግድ አይሰጥህም?በጣም ዘገየህ" ሲለው ዶክተሩም በፈገግታ " ይቅርታ ሆስፒታል ጊቢ ውስጥ አልነበርኩም፤ስልክ ከተደወለልኝ ቦሀላ ግን አቅሜ በፈቀደ መጠን በፍጥነት ለመድረስ ሞክሬያለው፤ ተረጋጋ አለው:: "ተረጋጋ ትለኛለህ? ታሞ ሊሞት እያጣጣረ ያለውኮ የኔ ልጅ ነው፤እንዴት ተረጋጋ ትለኛለህ? ያንተ ልጅ ቢሆን እንደዚህ ትላለህ? አንተ በመዘግየትህ ልጄ ሊሞትብኝ ነው ትንሽ አታስብም?'' ብሎ ሲጮህበት ዶክተሩ አሁንም ፈገግ እያለ፦ ዶክተር የሰውን ልጅ ህይወት ሊያረዝምም ሊያሳጥርም አይችልም፤አፈር ነንና ወደ አፈር መመለሳችን አይቀርም፤አሁን ተረጋጋ እኔም ስራዬን ልስራበት" ብሎ ወደ ሰርጀሪ ክፍል ገብቶ ለተወሰኑ ሰአታት የህፃኑን ቀዶ ጥገና ካከናወነ ቦሃላ ወደ ውጭ
ወጥቶ በፈገግታ የልጁን አባት "እንኳን ደስ አለህ!! ልጅህ ሰርጀሪ ከተደረገለት ቦሀላ በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛል፤ከዚህ ቦሀላ የሚያስፈልግህ ነገር ካለ ነርሷ ትረዳሀለች " ብሎት እየሮጠ ከሆስፒታሉ ወጣ ሰውዬው በሰማው መልካም ዜና ቢደሰትም የዶ/ሩ ሁኔታ ግራ ስለገባው ነርሷን "ዶ/ሩ ምን ሆኖ ነው እንዲህ የተዋከበው?'' ብሎ ሲጠይቃት " ዶ/ሩ ትላንትና ልጁ በመኪና አደጋ ሞቶበት ቀብር ላይ ነበር፤ያንተ ልጅ ህመም አደገኛ ስለነበር እንዲያክመው ደውለን ጠርተነው ነው፤ አሁን ያንተን ልጅ ካዳነ ቦሀላ የልጁ ቀብር ላይ ለመድረስ ነው እየሮጠ ያለው!" ስትለው ሰውዬው ድርቅ ብሎ ቀረ!! የሰው ልጅ በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንደሆነ ሳታውቅ አትፍረድ!!!
መልካም ቀን!
እፁብ ድንቅ ቀን ይሁንልን!
#ወደዱት፡ ለሌሎችም #ሼር በማድረግ አካፍሉ፡፡
https://t.me/SucessSecret
https://t.me/SucessSecre
310 viewsMasresha Debele, 05:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 08:00:38
296 viewsMasresha Debele, 05:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 20:45:09
ፍላጎትዎን ማሳካት እና መኖር ይሻሉ?

ሁሉም ሠው የራሴ የሚለው ሊደርስበት፣ ሊያሳካው የሚፈልገው ከመሞቱ በፊት ባደርገው ብሎ በውስጡ የሚይዘው ህልም አለው።

ለአብዛኛዎቻችን ግን ይህ ህልም ከሀሳብ እና ከምኞት አልፎ አያውቅም። በየዕለቱ ስለህልማችን ማሰብ እንዳለብን አንረዳም ፤ ወይም ህልማችን በጣም ትልቅ እና የማይደረስበት አድርገን በማሰብ ትኩረት አንሰጠውም።

ትልቅ እና ከአቅማችን በላይ የመሠለንን ህልማችንን በገሃዱ አለም ዕውን ለማድረግ ከሀሳብ እና ከምኞት ከፍ ማድረግ ይሻል ፤ ከዚያም መሬት አውርደን አጭር በሆነችው ህይወታችን ህልምና ግባችን ላይ ተንተርሰን፤ ወደ የየዕለት አጫጭር እርምጃዎች የመቀየር ልምምድን ይጠቃል።

ህልማችንን ከተግባር ጋር የምናገናኝባቸውን ጠንካራ ስልቶች ቀላል በሆነ መንገድ መማር ለምትፈልጉ። ውስብስብ የነበረውን ህልማችንን አቅልሎና አጥርቶ መንገዳችንን ግልፅ እንድሆንላችሁ ወይም እንድያግችሁ።

ስልጠና ለመካፈልበዚህ
@masredeb
ቴሌግራም ሊንክ መግኛት ትችላላችሁ ።
329 viewsMasresha Debele, 17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 12:27:59 የምናብ ምስጢር (imagination)

ሕልምን የማሳካት ምስጢር እንዲህ ይላል… ‘‘የሰው ልጅ ሕልሙን በአዕምሮው በግልጽ ሲያስብ እና እንደሚያሳካው በልቡ ሲያምን፣ መከፈል ያለበትን መስዋዕትነት በመክፈል፣ ሕልሙን ማሳካት ይችላል!’’

ይህንን ምስጢር በትክክል የተረዱ ሰዎች፣ ምናባቸውን ድንቅ በሆነ መንገድ በመጠቀም ተዓምር እየሰሩ ነው። አሁን በአካባቢያችን የምናያቸው ድንቅ የሆኑ ግኝቶች በሙሉ የተፈጠሩት ምናባቸውን በድንቅ ሁኔታ በተጠቀሙ ሰዎች ነው። አውሮፕላን፣ መኪና፣ ቴሌቪዥን፣ ስልክ፣ ኮምፕዩተር፣ እስክርቢቶና አሁን የለበስከው ልብስ ጭምር፣ የሆነ ጊዜ ላይ በአንድ ሰው ምናብ ውስጥ የተፈጠሩ የድንቅ ምናባዊ ምጥቀት ውጤቶች ናቸው።

ትልቁን ሕልምህንና የሕልምህን ድንቅ ሕይወት በምናብህ በተደጋጋሚ ስትመለከተው፣ ሕልምህን እንደምታሳካው በልብህ ታምናለህ። ሕልምህን እንደምታሳካው በልብህ ስታምን ደግሞ፣ መከፈል ያለበትን መስዋዕትነት በመክፈል፣ ሕልምህን እውን ታደርገዋለህ።

ፈጣሪ ምናብህን በመጠቀም፣ ትልቁን ሕልምህን አስቀድመህ በማየት፣ ልታሳካበት የምትችልበትን ልዩ የአዕምሮ መሣሪያ ሰጥቶሀል። ምናብህን በመጠቀም፣ ሕይወትህንና የቤተሰብህን ሕይወት ብቻ ሳይሆን፣ አገርህንና ዓለምን የሚቀይር ትልቅ ሕልም አልም። መከፈል ያለበትን መስዋዕትነት በመክፈል፣ ትልቁን ሕልምህን እውን በማድረግ እና የተሻለች ዓለም በመፍጠር፣ ፈጣሪህን አመስግን።

መልካም ቀን!
366 viewsMasresha Debele, 09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 11:14:40
መንገድ ወይም ምክንያት!

አንድን ነገር በእርግጥም ለማድረግና ለማከናወን ከወሰናችሁና ከቆረጣችሁ በዚህም በዚያም ብላችሁ መንገድ ትፈልጋላችሁ፡፡ አንድን ነገር ለማከናወን ቁርጠኝነቱ፣ ፍላጎቱና መነሳሳቱ ከሌላችሁ ግን ያንን ነገር ላለማድረግ ከዚህም ከዚያም ብላችሁ ምክንያት ትፈልጋላችሁ፡፡

ከመልካም ዓላማችሁና እቅዳችሁ አንጻር ምክንያታችሁ ይድከምና መንገድ የማፈላለጋችሁ ትጋት ይቀጥል፡፡

ወስኑ! ቁረጡ! አቋም ያዙ! “የትኛውም እንቅፋት አያቆመኝም” ብላችሁ ለራሳችሁ ንገሩት! መንገዱ እስከሚገኝ ተራመዱ፣ ፈልጉት፣ ማግኘታች አይቀርም!

መልካም ቀን!
እፁብ ድንቅ ቀን ይሁንልን!
#ወደዱት፡ ለሌሎችም #ሼር በማድረግ አካፍሉ፡፡
https://t.me/SucessSecret
https://t.me/SucessSecre
585 viewsMasresha Debele, edited  08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 06:19:53
ስኬት ማለት በሕይወታችን ልናሳካ የምናስበውን ጠቃሚ ግብ ወደ ተጨባጭ ውጤት የምንቀይርበት፣ በንፅፅር የሚመዘን እና ከደረጃ ደረጃ መሸጋገርን የሚያመላክት የሕይወት መንገድ ነው፡፡
ለስኬት ብዙ ዋጋ ይከፈላል ከነዚህም ውስጥ ሁለትና ሶስት ስራዎችን ደራርቦ መስራት ፣ተከታታይነት ባለው መልኩ ትምህርትና ስልጠናዎችን መውሰድ እና በባህር ላይ አቆርጦ ሕይወትን ለአደጋ በሚያጋልጥ ሁኔታ ከሀገር መውጣትን የመሰሉ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ሁለንተናዊ ስኬት ማለት ደግሞ አንድ ሰው በጤና፣በእዉቀት ፣በገንዘብ ፣ በማህበራዊ ግንኙነት፣በመንፈሳዊ ሕይወት እና በግለሰናዊ ስብዕና የተገነባ ማንነት ሲኖረው ነው ስለዚህ ስኬት በገንዘብ ብቻ እንደማይመዘን አውቀን ሁለንተናዊ ስኬትን ለማግኘት ትኩረት ሰጥተን ልንሰራ ይገባናል ፡፡ከራሳችን አልፈን ለሌሎች መትረፍ እና ማገልገል መቻል ትልቁ የስኬት ማሳያ ነው ሀብት፣እውቀት፣ዝናና ኃይል ለሌሎች ጥቅም እስካልዋለ ድረስ ብቻውን ስኬት ሊሆን አይችልም በእጃችን የገባው ብዙ ለሌሎች ጥቅም ያወጣነው ግን ጥቂት ከሆነ ከስኬት እርቀናል እኛ የደረስንበት ደረጃና ያገኘነው መልካም ነገር በሰዎች በኩል መሆኑን መዘንጋት የለብንም ፡፡
በመጨረሻም የስኬት መርሆችን ጠንቅቀን ማወቅና መረዳት ፣ የተደራጀና በፅሁፍ የሰፈረ ራዕይ ፣ ህልም ፣ ግብ እና ዝርዝር እቅድ ማውጣት፣አውንታዊ አመለካከቶችን መገንባት፣ ስኬታማ የሆኑ ሰዎችን ግለ ታሪክ ማጥናትና የሕይወት ልምዶቻቸዉን መቅሰም፣የተለያዩ መጻህፍትን ማንበብ፣በጊዜዊ ሽንፈቶች ሳንበገር ደጋግመን መሞከር እና ሳንሰለች ስኬትን የሙጥኝ ብለን መያዝ ለስኬት ትልቅ ድርሻ አለው፡፡

መልካም ቀን!
እፁብ ድንቅ ቀን ይሁንልን!
#ወደዱት፡ ለሌሎችም #ሼር በማድረግ አካፍሉ፡፡
https://t.me/SucessSecret
https://t.me/SucessSecre
793 viewsMasresha Debele, edited  03:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 08:25:32 እውነተኛ ስኬት
በህይወት ስንኖር ሁላችንም ስኬት የምትባለውን ጽዋ መቅመስ እንሻለን፡፡ ወደ እውነታው ስንመጣ ደግሞ ስኬት የጥቂቶች ብቻ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ለምን?

በትምህርቶቻችን ስኬት ሂደት እንደሆነ እናስተምራለን፡፡ ይህ የማይካድ እውነት ነው፡፡ ይህን ሂደት በቁርጠኝነት ያለማቋረጥ የሚሄዱ ናቸው እውነተኛውን የስኬት ጽዋ የሚጎነጬት፡፡ እንደ ሊቃውንት ኮንሰልተንሲ ዛሬ ላይ በዚህ ሂደት ውስጥ እያለፍን እያደግን ዛሬ ላይ ከራሳችን አልፈን ለሺዎች መቶ ሺዎችና ሚሊየኖች መለወጥ ምክንያት እየሆንን እንገኛለን፡፡እንቀጥላለንም

አንተስ? አንቺስ?

አንድ በዚህ እውነተኛ ስኬት ሂደት ውስጥ ያለፈ ድንቅ አፍሪካዊ ወጣት ታሪክ ላጋራችሁ

በቅጽል ስሙ ጥቁሩ ዳይመንድ ይሉታል ሴኔጋላዊው የእግር ኳስ ኮከብ ሳዲዮ ማኔ፡፡ ውልደቱ ባምባሊ በሚባል የሴኔጋል መንደር ውስጥ ሲሆን ፕሮፌሽናል እግር ኳስን በ19 ዓመቱ ሜትዝ(Metz)በሚባል ክለብ ሲጀምር ከትንሽ ቆይታ በኋላም የአውስትራሊያውን ሬድ ቡል ሳልዝበርግን ተቀላቅሏል፡፡

እንዲህ እንዲያ እያለ ማኔ በየክለቡ በሚያሳየው ድንቅ አቋምና ችሎታ የስኬት ሂደቱን በቁርጠኝነት በማለፉ ዛሬ ላይ የዓለማችን ታላቅ ከሆነው ክለብ ሊቨርፑል ላይ በሚገርም ክፍያ ምርጥ ብቃቱን እያሳየ እየተጫወተ ይገኛል፡፡

ሳዲዮ ማኔ በዓመት 10。2 ሚሊየን ዶላር(510,000,000 ሚሊዮን ብር) ወደ ካዝናው ያስገባል፡፡ ምንም እንኳ ገቢው የትየለሌ ቢሆንም ማኔ ብዙ ጊዜ ግን ቀለል ያለና ውድ የሚባሉ ቁሶችን የማይጠቀም ሰው ነው፡፡

በአንድ ወቅት አድናቂዎቹ የተሰነጣጠቀ ስልክ ይዞት ባዩ ጊዜ ለምን ብለው ጥያቄ ሰነዘሩ፡፡ ማኔም እንዲህ ነበር ያላቸው .....

ለምን አስር ፈራሪ መኪና፣ 20 የዓልማዝ ሰዓቶች፣ እና ሁለት ዘመናዊ ጀቶችን እፈልጋለሁ? በረሃብ ተሰቃይቻለሁ፣ በባዶ እግሬ ኳስ ተጫውቻለሁ በድህነቴ ምክንያትም አልተማርኩም፡፡

አሁን ግን ሰዎችን መርዳት እችላለሁ፡፡ ትምህርት ቤት ገንብቼ ለታዳጊ የሃገሬ ተስፈኛ ልጆች ደርሻለሁ፡፡ በከፋ ድህነት ውስጥ ለሚኖሩ የሴኔጋል ገጠራማ የሴኔጋል ዜጎች በየወሩ 70 ዩሮ እለግሳለሁ፡፡

ሳዲዮ ንግግሩን ሲቋጩም እኔ የቅንጦት መኪናዎችን፣ የቅንጦት ቤቶችን እና ውድ ውድ ነገሮችን ማሳየትና መጎረር አያስፈልገኝም ይላል፡፡

ይህ ነው እውነተኛ ስኬት፡፡ ከታች የጀመረና ጫፍ ላይ በሂደት የደረሰ በትክክለኛ ሂደት ተፈትኖ ያለፈና ውጤትን ያፈራ፡፡ ለብዙዎችም የተረፈ ስኬት።
ወደዚህ ምድር የመጣነው ለራሳችን ለመኖር ብቻ አይደለም። የመጣነው ከኛ አልፈን የሌሎችን ህይወት የተሻለ ለማድረግ ነው። ለለውጥ።

ንቃ።ራስህ ላይ ስራ።

ለዓላማችን ውጥረን እንስራ እንሞክር ቁርጠኛ እንሁን ተስፋም አንቁረጥ በፍፁም አናቁም። ይሄን ስናደርግ ፈጣሪም ይረዳናል፡፡ ፈጣሪ ሁላችንንም ለንደዚህ አይነት እውነተኛ ስኬት ያብቃን፡፡

የተሻለ ልምድ የተሻለ ውጤት
ይምጡ ይማሩ፡፡ ይደጉ፡፡
በአካልም በኦንላየን መሰልጠን ይችላሉ፡፡

አድራሻ
0972707274
752 viewsMasresha Debele, 05:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 08:24:12
559 viewsMasresha Debele, 05:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ