Get Mystery Box with random crypto!

የምናብ ምስጢር (imagination) ሕልምን የማሳካት ምስጢር እንዲህ ይላል… ‘‘የሰው ልጅ ሕል | የስኬት ምስጢሮች

የምናብ ምስጢር (imagination)

ሕልምን የማሳካት ምስጢር እንዲህ ይላል… ‘‘የሰው ልጅ ሕልሙን በአዕምሮው በግልጽ ሲያስብ እና እንደሚያሳካው በልቡ ሲያምን፣ መከፈል ያለበትን መስዋዕትነት በመክፈል፣ ሕልሙን ማሳካት ይችላል!’’

ይህንን ምስጢር በትክክል የተረዱ ሰዎች፣ ምናባቸውን ድንቅ በሆነ መንገድ በመጠቀም ተዓምር እየሰሩ ነው። አሁን በአካባቢያችን የምናያቸው ድንቅ የሆኑ ግኝቶች በሙሉ የተፈጠሩት ምናባቸውን በድንቅ ሁኔታ በተጠቀሙ ሰዎች ነው። አውሮፕላን፣ መኪና፣ ቴሌቪዥን፣ ስልክ፣ ኮምፕዩተር፣ እስክርቢቶና አሁን የለበስከው ልብስ ጭምር፣ የሆነ ጊዜ ላይ በአንድ ሰው ምናብ ውስጥ የተፈጠሩ የድንቅ ምናባዊ ምጥቀት ውጤቶች ናቸው።

ትልቁን ሕልምህንና የሕልምህን ድንቅ ሕይወት በምናብህ በተደጋጋሚ ስትመለከተው፣ ሕልምህን እንደምታሳካው በልብህ ታምናለህ። ሕልምህን እንደምታሳካው በልብህ ስታምን ደግሞ፣ መከፈል ያለበትን መስዋዕትነት በመክፈል፣ ሕልምህን እውን ታደርገዋለህ።

ፈጣሪ ምናብህን በመጠቀም፣ ትልቁን ሕልምህን አስቀድመህ በማየት፣ ልታሳካበት የምትችልበትን ልዩ የአዕምሮ መሣሪያ ሰጥቶሀል። ምናብህን በመጠቀም፣ ሕይወትህንና የቤተሰብህን ሕይወት ብቻ ሳይሆን፣ አገርህንና ዓለምን የሚቀይር ትልቅ ሕልም አልም። መከፈል ያለበትን መስዋዕትነት በመክፈል፣ ትልቁን ሕልምህን እውን በማድረግ እና የተሻለች ዓለም በመፍጠር፣ ፈጣሪህን አመስግን።

መልካም ቀን!