Get Mystery Box with random crypto!

እውነተኛ ስኬት በህይወት ስንኖር ሁላችንም ስኬት የምትባለውን ጽዋ መቅመስ እንሻለን፡፡ ወደ እውነታ | የስኬት ምስጢሮች

እውነተኛ ስኬት
በህይወት ስንኖር ሁላችንም ስኬት የምትባለውን ጽዋ መቅመስ እንሻለን፡፡ ወደ እውነታው ስንመጣ ደግሞ ስኬት የጥቂቶች ብቻ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ለምን?

በትምህርቶቻችን ስኬት ሂደት እንደሆነ እናስተምራለን፡፡ ይህ የማይካድ እውነት ነው፡፡ ይህን ሂደት በቁርጠኝነት ያለማቋረጥ የሚሄዱ ናቸው እውነተኛውን የስኬት ጽዋ የሚጎነጬት፡፡ እንደ ሊቃውንት ኮንሰልተንሲ ዛሬ ላይ በዚህ ሂደት ውስጥ እያለፍን እያደግን ዛሬ ላይ ከራሳችን አልፈን ለሺዎች መቶ ሺዎችና ሚሊየኖች መለወጥ ምክንያት እየሆንን እንገኛለን፡፡እንቀጥላለንም

አንተስ? አንቺስ?

አንድ በዚህ እውነተኛ ስኬት ሂደት ውስጥ ያለፈ ድንቅ አፍሪካዊ ወጣት ታሪክ ላጋራችሁ

በቅጽል ስሙ ጥቁሩ ዳይመንድ ይሉታል ሴኔጋላዊው የእግር ኳስ ኮከብ ሳዲዮ ማኔ፡፡ ውልደቱ ባምባሊ በሚባል የሴኔጋል መንደር ውስጥ ሲሆን ፕሮፌሽናል እግር ኳስን በ19 ዓመቱ ሜትዝ(Metz)በሚባል ክለብ ሲጀምር ከትንሽ ቆይታ በኋላም የአውስትራሊያውን ሬድ ቡል ሳልዝበርግን ተቀላቅሏል፡፡

እንዲህ እንዲያ እያለ ማኔ በየክለቡ በሚያሳየው ድንቅ አቋምና ችሎታ የስኬት ሂደቱን በቁርጠኝነት በማለፉ ዛሬ ላይ የዓለማችን ታላቅ ከሆነው ክለብ ሊቨርፑል ላይ በሚገርም ክፍያ ምርጥ ብቃቱን እያሳየ እየተጫወተ ይገኛል፡፡

ሳዲዮ ማኔ በዓመት 10。2 ሚሊየን ዶላር(510,000,000 ሚሊዮን ብር) ወደ ካዝናው ያስገባል፡፡ ምንም እንኳ ገቢው የትየለሌ ቢሆንም ማኔ ብዙ ጊዜ ግን ቀለል ያለና ውድ የሚባሉ ቁሶችን የማይጠቀም ሰው ነው፡፡

በአንድ ወቅት አድናቂዎቹ የተሰነጣጠቀ ስልክ ይዞት ባዩ ጊዜ ለምን ብለው ጥያቄ ሰነዘሩ፡፡ ማኔም እንዲህ ነበር ያላቸው .....

ለምን አስር ፈራሪ መኪና፣ 20 የዓልማዝ ሰዓቶች፣ እና ሁለት ዘመናዊ ጀቶችን እፈልጋለሁ? በረሃብ ተሰቃይቻለሁ፣ በባዶ እግሬ ኳስ ተጫውቻለሁ በድህነቴ ምክንያትም አልተማርኩም፡፡

አሁን ግን ሰዎችን መርዳት እችላለሁ፡፡ ትምህርት ቤት ገንብቼ ለታዳጊ የሃገሬ ተስፈኛ ልጆች ደርሻለሁ፡፡ በከፋ ድህነት ውስጥ ለሚኖሩ የሴኔጋል ገጠራማ የሴኔጋል ዜጎች በየወሩ 70 ዩሮ እለግሳለሁ፡፡

ሳዲዮ ንግግሩን ሲቋጩም እኔ የቅንጦት መኪናዎችን፣ የቅንጦት ቤቶችን እና ውድ ውድ ነገሮችን ማሳየትና መጎረር አያስፈልገኝም ይላል፡፡

ይህ ነው እውነተኛ ስኬት፡፡ ከታች የጀመረና ጫፍ ላይ በሂደት የደረሰ በትክክለኛ ሂደት ተፈትኖ ያለፈና ውጤትን ያፈራ፡፡ ለብዙዎችም የተረፈ ስኬት።
ወደዚህ ምድር የመጣነው ለራሳችን ለመኖር ብቻ አይደለም። የመጣነው ከኛ አልፈን የሌሎችን ህይወት የተሻለ ለማድረግ ነው። ለለውጥ።

ንቃ።ራስህ ላይ ስራ።

ለዓላማችን ውጥረን እንስራ እንሞክር ቁርጠኛ እንሁን ተስፋም አንቁረጥ በፍፁም አናቁም። ይሄን ስናደርግ ፈጣሪም ይረዳናል፡፡ ፈጣሪ ሁላችንንም ለንደዚህ አይነት እውነተኛ ስኬት ያብቃን፡፡

የተሻለ ልምድ የተሻለ ውጤት
ይምጡ ይማሩ፡፡ ይደጉ፡፡
በአካልም በኦንላየን መሰልጠን ይችላሉ፡፡

አድራሻ
0972707274