Get Mystery Box with random crypto!

ስኬት ማለት በሕይወታችን ልናሳካ የምናስበውን ጠቃሚ ግብ ወደ ተጨባጭ ውጤት የምንቀይርበት፣ በንፅፅ | የስኬት ምስጢሮች

ስኬት ማለት በሕይወታችን ልናሳካ የምናስበውን ጠቃሚ ግብ ወደ ተጨባጭ ውጤት የምንቀይርበት፣ በንፅፅር የሚመዘን እና ከደረጃ ደረጃ መሸጋገርን የሚያመላክት የሕይወት መንገድ ነው፡፡
ለስኬት ብዙ ዋጋ ይከፈላል ከነዚህም ውስጥ ሁለትና ሶስት ስራዎችን ደራርቦ መስራት ፣ተከታታይነት ባለው መልኩ ትምህርትና ስልጠናዎችን መውሰድ እና በባህር ላይ አቆርጦ ሕይወትን ለአደጋ በሚያጋልጥ ሁኔታ ከሀገር መውጣትን የመሰሉ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ሁለንተናዊ ስኬት ማለት ደግሞ አንድ ሰው በጤና፣በእዉቀት ፣በገንዘብ ፣ በማህበራዊ ግንኙነት፣በመንፈሳዊ ሕይወት እና በግለሰናዊ ስብዕና የተገነባ ማንነት ሲኖረው ነው ስለዚህ ስኬት በገንዘብ ብቻ እንደማይመዘን አውቀን ሁለንተናዊ ስኬትን ለማግኘት ትኩረት ሰጥተን ልንሰራ ይገባናል ፡፡ከራሳችን አልፈን ለሌሎች መትረፍ እና ማገልገል መቻል ትልቁ የስኬት ማሳያ ነው ሀብት፣እውቀት፣ዝናና ኃይል ለሌሎች ጥቅም እስካልዋለ ድረስ ብቻውን ስኬት ሊሆን አይችልም በእጃችን የገባው ብዙ ለሌሎች ጥቅም ያወጣነው ግን ጥቂት ከሆነ ከስኬት እርቀናል እኛ የደረስንበት ደረጃና ያገኘነው መልካም ነገር በሰዎች በኩል መሆኑን መዘንጋት የለብንም ፡፡
በመጨረሻም የስኬት መርሆችን ጠንቅቀን ማወቅና መረዳት ፣ የተደራጀና በፅሁፍ የሰፈረ ራዕይ ፣ ህልም ፣ ግብ እና ዝርዝር እቅድ ማውጣት፣አውንታዊ አመለካከቶችን መገንባት፣ ስኬታማ የሆኑ ሰዎችን ግለ ታሪክ ማጥናትና የሕይወት ልምዶቻቸዉን መቅሰም፣የተለያዩ መጻህፍትን ማንበብ፣በጊዜዊ ሽንፈቶች ሳንበገር ደጋግመን መሞከር እና ሳንሰለች ስኬትን የሙጥኝ ብለን መያዝ ለስኬት ትልቅ ድርሻ አለው፡፡

መልካም ቀን!
እፁብ ድንቅ ቀን ይሁንልን!
#ወደዱት፡ ለሌሎችም #ሼር በማድረግ አካፍሉ፡፡
https://t.me/SucessSecret
https://t.me/SucessSecre