Get Mystery Box with random crypto!

የስኬት ምስጢሮች

የቴሌግራም ቻናል አርማ sucesssecret — የስኬት ምስጢሮች
የቴሌግራም ቻናል አርማ sucesssecret — የስኬት ምስጢሮች
የሰርጥ አድራሻ: @sucesssecret
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.35K
የሰርጥ መግለጫ

የሁሉም ስኬት መጀመሪያ ነጥብ ያለው ፍላጉት ላይ ነው ።የመለወጥ ጠንካራ ፍላጎት ያለቻው ሰዎች አእምሮአቸውን ይጠቃሙባታል
በቻናላችን ላይ ትላልቅ የስኬት መሪህዎችን ታገኛለችሁ ሼር አድርጉ ይቀላቀሉም።
እንዲሁም በነፃ የማማከር አገልግሎትም እንሰጣለን (0972707274)። ስልጠናዎችን በኦዲዮ ፣ በቪድዮ እና በፁሁፍም ይቀርባሉ።

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-06-15 16:09:41 መቸም ቢሆን አልረፈደም! ከ65 አመቱ ወጣት የምንማረው...!

በአንድ ወቅት በአንዲት ኬንታኪ በምትባል የአሜሪካ ግዛት ውስጥ ከመንግስት በየወሩ በሚሰጠው 99$ የሚኖር ፣ ገንዝብ አልባ ፣ ትንሽ ቤት ውስጥ የሚኖር እና አሮጌ መኪና የሚነዳ ሽማግሌ ሰው ነበር ።

ይሄ ሰው ልክ 65 አመት ሲሞላው ልጅነቴንማ በዚህ መልኩ ማባከን የለብኝም በማለት ነገሮችን ለመቀየር ተነሳ ። ከዚያም ምን አገልግሎት? ለሰዎች ልስጥ ብሎ ሲያስብ ጓደኞቹ ሁሌ የሚያደንቁለት የዶሮ አሰራሩ ትዝ አለው ። ስለዚህ በህይወቱ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት ይቺ የዶሮ አሰራር ቁልፍ እንደሆነች ወሰነ!!!

ከዛም ጥርስ የነቀለባትን ኬንታኪ ትቶ ይቺኑ የምግብ አሰራር ለመሸጥ ብዙ የአሜርካ ክፍሎችን ዞረ። ለብዙ የሬስቶራንት ባለቤቶች እጅ የሚያስቆረጥም የዶሮ አሰራር እንዳለው ነገራቸው። እንደውም ከሽያጫቸው ላይ ትንሽ ፐርሰንት ከሰጡት አሰራሩን በነጻ ሊሰጣቸው ሁሉ ፈቀድ።

የሬስቶራንት ባለቤቶቹ ግን እንደሱ አላሰቡም። 1000 ግዜ አይሆንም አሉት። እሱ ግን እጅ አልሰጠም።

ዶሮ አሰራሩ በጣም የተለየች እንደሆነች አጥብቆ ያምን ነበርና። የመጀመሪያውን እሺ እስኪያገኝ ድረስ 1009 ግዜ አይሆንምን ሰማ ።

በመጨረሻ ግን ኮሎኔል ሃርትላንድ ሳንድራስ አሜርካኖች ብቻ አይደለም በአለም ያለ ሰው ሁሉ ዶሮ የሚበላበትን መንገድ ቀይሯል ።

ኬንታኪ የተጠበሰ ዶሮ መሸጫ (KFC) የተፈጠረው በዚህ መልኩ ነው ።

ከ65 አመቱ ወጣት ጋሽ ሳንድራስ የምንማረው .....

#መቼም ቢሆን አልረፈደም!
40, 50 ወይም 60 አመትም ቢሞላን መንገድ መቀየር ከፈለግን ማለት ያለብን "ልጅነቴንማ እንደዚህ አላባክነውም" ነው ።

በህይወት መዘግየት ማለት አለመድረስ አይደለም። ስለዚህ ሁሌም ጉዞህን ቀጥል!

ሁሌም ካለህበት ጀምር፤ ያለህን ተጠቀምበት፤ የምትችለውን አድርግ!

መልካም ቀን!
625 viewsMasresha, 13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 06:26:28
ቶማስ ኤዲሰን ብዙ ተሳስቶ አምፖልን ፈጠረ። ስለስህተቶቹ ሲያወራ ግን እንዲህ ይላል 'እኔ ብዙ ስለሞከርኩ ደስተኛ ነኝ ምክንያቱም ሁሌም ስሞክር ወይ ልክ ነኝ ወይ ደግሞ ተምሬበታለው' ይለናል። ያለፉ ስህተቶቻችንን ለከፍታችን መጠቀም አለብን፤ ሰሞኑን ካጋጠመኝ ችግር ምን ተማርኩበት እንበል። ሁለቴ መውደቅ የሚፈልግ የለም መቼም...አሸናፊ ማለት የማይወድቅ አይደለም፤ ቢወድቅም መልሶ የሚነሳ ነው። የሆነ ነገር አልሳካ ሲለን እስኪ ምንድነው ያጎደልኩት ብለን ጊዜ ወስደን ማሰብ አለብን። ከስህተት በላይ ምን አስተማሪ ነገር አለ? እንደውም ምርጥ አርጌ ደግሜ እንድሰራው እድል ተሰቶኛል ማለት አለብን።

መልካም ቀን!
እፁብ ድንቅ ቀን ይሁንልን!
#ወደዱት፡ ለሌሎችም #ሼር በማድረግ አካፍሉ፡፡
https://t.me/SucessSecret
https://t.me/SucessSecre
740 viewsMasresha Debele, edited  03:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 22:20:11
የህይወት ውሳኔያችንን
አቅጣጫ ምናስይዝበት የቡድን ጊዜ ፕሮግራም
በ Helzer tower 3rd flr
ስልጠናዎች እና አማራጮች
የህይወት ተሞክሮ
ግብዣውን ይያዙ ለሚወዷቸው እድል ይስጡ!
የፊታችን እሁድ ሰኔ 5 /2014
ከሰዓት 8:00 ጀምሮ
ቀድመው ቡክ ያድርጉ!
"ስኬት የሚገባው ለሚያምኑ ነው"
"ዊዝደም ቲም"

ለበለጠ መረጀ 0972707274
680 viewsMasresha, edited  19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 06:36:04 ዓላማህን ያወክ ጊዜ . . .

በልጅነትህ ገና መራመድ ስትጀምርና ተደናቅፈህ ስትወድቅ አብዛኛዎቹ ሰዎች፣ “እኔን” ብለው ሊደግፉህ የሞክራሉ፡፡ አድገህ የዓላማና የአቋም ሰው ከሆንክ በኋላ ግን ተደናቅፈህ ስትወድቅ አብዛኛዎቹ ሰዎች፣ “ምን ያደናቅፈዋል፣ እያየ አይሄም” ይሉሃል፡፡ በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት የመብሰልህ፣ የዓላማ ሰው የመሆንህን ጉዳይ ነው፡፡

ሁል ጊዜ ግን እንደ ልጅ አይዞህ ባይና ደጋፊ ብቻ ስትጠብቅ መኖር አትችልም - አያዛልቅህምና! ዓላማህን አውቀህና ወገብህን ታጥቀህ ወደፊት መራመድ አስፈላጊ ነው፡፡ የሕይወትህን ዓላማ ያወክ ጊዜ ሁለት ነገሮች መለየት ትጀምራለህ . . .

1. ለአንተ ግድ የሚለውን ደጋፊህንና ለአንተ ግድ የሌለውን ሰው ትለያለህ

ካለምንም ዓላማ ወዲህና ወዲያ ስትል የኖርክባቸውን ጊዜያት ብታስታውስ ብዙም የሚቃወምህ ሰውና የሚጋፋህ እንቅፋት እንዳልነበረ ታስተውላለህ ብዬ እገምታለሁ፡፡ ልክ ዓላማህን ማወቅ ስትጀምር፣ ወደ አንድ አቅጣጫ ለመጓዝ ስትቆርጥና የአቋምና የእርምጃ ሰው ስትሆን የሚቃወሙህና በአንተ ላይ ሃሳብን የሚያበዙ ሰዎች ብቅ ብቅ ማለት ይጀምራሉ፡፡ አይግረምህ፤ መንገድህን ቀጥል፡፡ ምንም ዓላማውን የማያውቅን ሰውና ምንም እንቅስቃሴ የማያረግን ሰው ማንም ሰው አይነካውም፡፡

2. ጠንካራ ጎንህንና ደካማ ጎንህን ትለያለህ

ከባድ ነገርን ለማንሳት ሙከራ እስክታደርግ ድረስ ምን ያህል ነገር ማንሳት እንደምትችል አታውቀውም፡፡ ረጅም ርቀት ለመጓዝ እንስካልሞከርክ ድረስ ምን ያህል ርቀት መጓዝ እንደምትችል አይገለጥልህም፡፡ አንድን የሞያ መስመር መከታተል እስከምትጀምር ድረስ ምን አይነት የእውቀት ዘርፍ እንደሚገለጥልህ አታውቀውም፡፡ ልክ በአንድ ዓላማ አቅጣጫ መራመድ ስትጀምር ብርቱ ጎንህና ደካማ ጎንህ ለራስህው መታየት ይጀምራሉ፡፡ ማድረግ የምትችለውንና የማትችለውን፣ የሚቀልህንና የሚከብድህን ነገር መለየት ትጀምራህ፡፡

የሕይወትህ ዓላማ ምንድን ነው?

(ዶ/ር ኢዮብ ማሞ)
እፁብ ድንቅ ቀን ይሁንልን!
#ወደዱት፡ ለሌሎችም #ሼር በማድረግ አካፍሉ፡፡
https://t.me/SucessSecret
https://t.me/SucessSecret
721 viewsMasresha Debele, edited  03:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 06:35:19
546 viewsMasresha Debele, 03:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 08:51:22 8ኛ. ተመሳሳይ ስህተት ደጋግሞ መሥራት

“እብደት ማለት ተመሳሳይ ነገር ደጋግመው እያደረጉ የተለየ ውጤት መጠበቅ ነው” የሚል አባባል አለ። የአእምሮ ጽናት ያለው ሰው የተሳሳተውን ነገር ተቀብሎ እና አርሞ ለመጓዝ ፈቃደኛ ብቻ ሳይሆን ቀዳሚ ነው።

9ኛ. በሌሎች ሰዎች ስኬት መቆጨት

በሌሎች ሰዎች ስኬት የእውነት መደሰት ጠንካራ ባህሪን ይጠይቃል። የአእምሮ ጽናት ያላቸው ሰዎች ይህንን ጠንካራ ባህሪ የተጎናጸፉ ናቸው። ሌሎች ሲሳካላቸው ቅናት ጠቅ አያደርጋቸውም። ያም ሆኖ “ይህ ሰው እንዴት ሆኖ ነው እዚህ ስኬት ላይ የደረሰው?” ብለው በመጠየቅ ለራሳቸው ትምህርት ይቀስማሉ። “አቋራጭ” ሳያሻቸው በራሳቸው ስኬትን ለማግኘት ይተጋሉ።

10ኛ. ሳይሳካላቸው ሲቀር ተስፋ መቁረጥ

እያንዳንዷ ውድቀት የመሻሻል እድል አብራ ይዛ ትመጣለች። በዓለም ታሪክ ታላላቅ የሚባሉ የቢዝነስ ጀማሪዎች እንኳን፣ በተለይ መጀመሪያ አካባቢ አንድን ነገር አቃንተው ከሠሩበት ያበላሹበት ጊዜ እንደሚበዛ ለመናገር አያፍሩም። የአእምሮ ጽናት ያላቸው ሰዎች ወደሚፈልጉት ግብ የሚያቀርባቸው ይሁን እንጂ፣ አሥሬ እየወደቁ አሥሬ አቧራቸውን አራግፈው ለመነሣት ፈቃደኛ ናቸው።

11ኛ. ብቻቸውን መሆን መፍራት

የአእምሮ ጽናት ያላቸው ሰዎች ለብቻቸው ጊዜ ማሳለፍ አያሸብራቸውም፤ እንደውም ይናፍቁታል። የብቻ ጊዜያቸውን ለማሰላሰል፣ ለማቀድ እና ውጤታማነታቸው ላይ ለመሥራት ይጠቀሙታል። ከዚህም በላይ፣ ደስታቸው ሙሉ በሙሉ በሌሎች አብሮነት ላይ የተደገፈ አይደለም። ከሌሎች ጋር አብረው በመሆን ደስ እንደሚላቸው ሁሉ፣ ብቻቸውን ሆነውም ደስታን ማጣጣም ይችላሉ።


12ኛ. የይገባኛል ስሜት

ከተማሩት ትምህርት ወይም ካለፉበት የተለያየ የዝግጅት ሂደት የተነሣ፣ እንዲህ ያለ ሥራ፣ ኑሮ፣ ሕይወት ወዘተ ሊኖረኝ ይገባል ብለው የሚያምኑ ብዙ ሰዎች አሉ። እንዲህ ከማለት አልፈው፣ ያለምንም ተጨማሪ ጥረት እንዲህ ያሉ ነገሮች የኔ ሊሆኑ ይገባል የማለት አባዜ ግን አይጠቅምም። የአእምሮ ጽናት ያላቸው ሰዎች እነዚህኑ ነገሮች (አንዳንዴ እንደውም በይበልጥ) ቢፍልጉም፣ ነገሮቹን ለማግኘት ጠንክረው መሥራት እንዳለባቸው ይገነዘባሉ።

13ኛ. ፈጣን ውጤትን መፈለግ

ክብደት መቀነስ ይሁን፣ አዲስ ቢዝነስ መጀመር ይሁን ወይም ሌላ የሕይወት ጉዞ፣ የአእምሮ ጽናት ያላቸው ሰዎች በአንድ ጀንበር የስኬት ማማ ላይ የሚደረስበት እንዳልሆነ በሚገባ ያውቃሉ። ከቀን ቀን የመትጋት፣ ከቀን ቀን የማሻሻል ቁርጠኝነት አላቸው።
625 viewsMasresha, 05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 20:36:43 Channel photo updated
17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 06:25:22 2ኛ. ስለራሳቸው የሚሰማቸው ስሜት በሌሎች እንዲወሰን መፍቀድ

አንዳንዴ ሌሎች ሰዎች በንግግር ወይም በአካኋናቸው የበታችነት እንዲሰማን ወይም በአጠቃላይ ስለራሳችን ያለን ስሜት ቀና እንዳይሆን ሊያደርጉን ይችላሉ። የአእምሮ ጽናት ያላቸው ሰዎች ግን እንዲህ ላለ ነገር በጄ አይሉም። ስሜታቸውንም ሆነ ድርጊታቸውን ራሳቸው ይዘውሩታል እንጂ ሌሎች እንዲጠመዝዙት አይፈቅዱም። የብርታታቸው አንዱ ምንጭ ለሚገጥማቸው ነገር የሚሰጡትን ምላሽ በራሳቸው ለመምረጥ ያላቸው አቅም ነው።

3ኛ. ለውጥን መሸሽ

የአእምሮ ጽናት ያላቸው ሰዎች ለውጥ ሲመጣ “ግባ በሞቴ” የሚሉ ናቸው። የሚፈሩት ነገር ለውጥን ሳይሆን ባሉበት መርገጥን ነው። ለውጥ እና አንዳንዴም የማያስተማምን የሚመስል ሁኔታ እንዲህ ያሉ ሰዎችን የበለጠ ለመትጋት ያነሣሣቸዋል።

4ኛ. ከቁጥጥራቸው ውጪ የሆኑ ነገሮች ላይ ጊዜ ማጥፋት

የአእምሮ ጽናት ያላቸው ሰዎች ስለመንገድ መጨናነቅ፣ ስለጠፋባቸው እቃ፣ ወይም ስለሌሎች ሰዎች እምብዛም ሲያማርሩ አይሰሙም። ለምን ቢባል፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ከእነርሱ ቁጥጥር ውጪ ናቸው። አጉል ነገር ሲገጥማቸው ከማማረር ይልቅ መቆጣጠር የሚችሉት ነገር ላይ ያተኩራሉ፤ ያም ለዚያ ነገር እነርሱ የሚሰጡት ምላሽ ነው።


5ኛ. ሌሎችን ለማስደሰት መጨነቅ

ሰው ለማስደሰት ሲሉ ራሳቸውን ውጥንቅጥ ውስጥ የሚከቱ ሰዎች ታውቁ ይሆን? አሊያም በተገላቢጦሽ ሌሎችን “ለማብሸቅ” ሲሉ አሳራቸውን የሚያዩስ? ሁለቱም በጎ አይደሉም። የአእምሮ ጽናት ያለው ሰው ለሁሉም መልካም እና ፍትሃዊ
ለመሆን ይጥራል፤ ሆኖም ሌላን ሰው ለማስደሰትም ሆነ ለማስከፋት ሲል ያልሆነውን አያስመስልም፤ አቋሙን አይቀያይርም። ይህም ሆኖ፣ አቋሙን ለመፈተሽ ፈቃደኛ ነው፤ ምናልባት ሰዎችን ቢያስከፋም ከእነርሱ በኩል ጉዳዩ ምን እንደሚመስል ለማጤን ፈቃደኛ ነው።

6ኛ. አደጋን (ሪስክን) መፍራት

የአእምሮ ጽናት ያላቸው ሰዎች የተጠና “ሪስክ” መውሰድን አይፈሩም። ይህ ማለት ሳያመዛዝኑ ያገኙት ነገር ውስጥ ሁሉ ዘው ይላሉ ማለት አይደለም። ይሁን እንጂ፣ አደጋ (“ሪስክ”) ያለውን ነገር ጥቅም እና ጉዳቱን መዝነው ለመጋፈጥ አይፈሩም።

7ኛ. ያለፈ ነገር ላይ ችክ ማለት

ያለፈ ነገርን መቀበል፣ ከዚያ የሚገኝ ማበረታቻም ሆነ መሻሻል ያለበት ነገር ካለ መማር አስፈላጊ ነው። ዳሩ ግን ያለፈ ጊዜን እያሰቡ መብከንከንም ሆነ “ደጉን ዘመን” እያሰቡ በቀን ሕልም መዋኘት የአእምሮ ጽናት ያላቸው ሰዎች የማያደርጉት ነገር ነው። አብዛኛውን አቅማቸውን የሚያውሉት የአሁኑን እና መጪውን ጊዜ የተሻለ ማደረግ ላይ ነው።
617 viewsMasresha, edited  03:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ