Get Mystery Box with random crypto!

8ኛ. ተመሳሳይ ስህተት ደጋግሞ መሥራት “እብደት ማለት ተመሳሳይ ነገር ደጋግመው እያደረጉ የተለየ | የስኬት ምስጢሮች

8ኛ. ተመሳሳይ ስህተት ደጋግሞ መሥራት

“እብደት ማለት ተመሳሳይ ነገር ደጋግመው እያደረጉ የተለየ ውጤት መጠበቅ ነው” የሚል አባባል አለ። የአእምሮ ጽናት ያለው ሰው የተሳሳተውን ነገር ተቀብሎ እና አርሞ ለመጓዝ ፈቃደኛ ብቻ ሳይሆን ቀዳሚ ነው።

9ኛ. በሌሎች ሰዎች ስኬት መቆጨት

በሌሎች ሰዎች ስኬት የእውነት መደሰት ጠንካራ ባህሪን ይጠይቃል። የአእምሮ ጽናት ያላቸው ሰዎች ይህንን ጠንካራ ባህሪ የተጎናጸፉ ናቸው። ሌሎች ሲሳካላቸው ቅናት ጠቅ አያደርጋቸውም። ያም ሆኖ “ይህ ሰው እንዴት ሆኖ ነው እዚህ ስኬት ላይ የደረሰው?” ብለው በመጠየቅ ለራሳቸው ትምህርት ይቀስማሉ። “አቋራጭ” ሳያሻቸው በራሳቸው ስኬትን ለማግኘት ይተጋሉ።

10ኛ. ሳይሳካላቸው ሲቀር ተስፋ መቁረጥ

እያንዳንዷ ውድቀት የመሻሻል እድል አብራ ይዛ ትመጣለች። በዓለም ታሪክ ታላላቅ የሚባሉ የቢዝነስ ጀማሪዎች እንኳን፣ በተለይ መጀመሪያ አካባቢ አንድን ነገር አቃንተው ከሠሩበት ያበላሹበት ጊዜ እንደሚበዛ ለመናገር አያፍሩም። የአእምሮ ጽናት ያላቸው ሰዎች ወደሚፈልጉት ግብ የሚያቀርባቸው ይሁን እንጂ፣ አሥሬ እየወደቁ አሥሬ አቧራቸውን አራግፈው ለመነሣት ፈቃደኛ ናቸው።

11ኛ. ብቻቸውን መሆን መፍራት

የአእምሮ ጽናት ያላቸው ሰዎች ለብቻቸው ጊዜ ማሳለፍ አያሸብራቸውም፤ እንደውም ይናፍቁታል። የብቻ ጊዜያቸውን ለማሰላሰል፣ ለማቀድ እና ውጤታማነታቸው ላይ ለመሥራት ይጠቀሙታል። ከዚህም በላይ፣ ደስታቸው ሙሉ በሙሉ በሌሎች አብሮነት ላይ የተደገፈ አይደለም። ከሌሎች ጋር አብረው በመሆን ደስ እንደሚላቸው ሁሉ፣ ብቻቸውን ሆነውም ደስታን ማጣጣም ይችላሉ።


12ኛ. የይገባኛል ስሜት

ከተማሩት ትምህርት ወይም ካለፉበት የተለያየ የዝግጅት ሂደት የተነሣ፣ እንዲህ ያለ ሥራ፣ ኑሮ፣ ሕይወት ወዘተ ሊኖረኝ ይገባል ብለው የሚያምኑ ብዙ ሰዎች አሉ። እንዲህ ከማለት አልፈው፣ ያለምንም ተጨማሪ ጥረት እንዲህ ያሉ ነገሮች የኔ ሊሆኑ ይገባል የማለት አባዜ ግን አይጠቅምም። የአእምሮ ጽናት ያላቸው ሰዎች እነዚህኑ ነገሮች (አንዳንዴ እንደውም በይበልጥ) ቢፍልጉም፣ ነገሮቹን ለማግኘት ጠንክረው መሥራት እንዳለባቸው ይገነዘባሉ።

13ኛ. ፈጣን ውጤትን መፈለግ

ክብደት መቀነስ ይሁን፣ አዲስ ቢዝነስ መጀመር ይሁን ወይም ሌላ የሕይወት ጉዞ፣ የአእምሮ ጽናት ያላቸው ሰዎች በአንድ ጀንበር የስኬት ማማ ላይ የሚደረስበት እንዳልሆነ በሚገባ ያውቃሉ። ከቀን ቀን የመትጋት፣ ከቀን ቀን የማሻሻል ቁርጠኝነት አላቸው።