Get Mystery Box with random crypto!

2ኛ. ስለራሳቸው የሚሰማቸው ስሜት በሌሎች እንዲወሰን መፍቀድ አንዳንዴ ሌሎች ሰዎች በንግግር ወይ | የስኬት ምስጢሮች

2ኛ. ስለራሳቸው የሚሰማቸው ስሜት በሌሎች እንዲወሰን መፍቀድ

አንዳንዴ ሌሎች ሰዎች በንግግር ወይም በአካኋናቸው የበታችነት እንዲሰማን ወይም በአጠቃላይ ስለራሳችን ያለን ስሜት ቀና እንዳይሆን ሊያደርጉን ይችላሉ። የአእምሮ ጽናት ያላቸው ሰዎች ግን እንዲህ ላለ ነገር በጄ አይሉም። ስሜታቸውንም ሆነ ድርጊታቸውን ራሳቸው ይዘውሩታል እንጂ ሌሎች እንዲጠመዝዙት አይፈቅዱም። የብርታታቸው አንዱ ምንጭ ለሚገጥማቸው ነገር የሚሰጡትን ምላሽ በራሳቸው ለመምረጥ ያላቸው አቅም ነው።

3ኛ. ለውጥን መሸሽ

የአእምሮ ጽናት ያላቸው ሰዎች ለውጥ ሲመጣ “ግባ በሞቴ” የሚሉ ናቸው። የሚፈሩት ነገር ለውጥን ሳይሆን ባሉበት መርገጥን ነው። ለውጥ እና አንዳንዴም የማያስተማምን የሚመስል ሁኔታ እንዲህ ያሉ ሰዎችን የበለጠ ለመትጋት ያነሣሣቸዋል።

4ኛ. ከቁጥጥራቸው ውጪ የሆኑ ነገሮች ላይ ጊዜ ማጥፋት

የአእምሮ ጽናት ያላቸው ሰዎች ስለመንገድ መጨናነቅ፣ ስለጠፋባቸው እቃ፣ ወይም ስለሌሎች ሰዎች እምብዛም ሲያማርሩ አይሰሙም። ለምን ቢባል፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ከእነርሱ ቁጥጥር ውጪ ናቸው። አጉል ነገር ሲገጥማቸው ከማማረር ይልቅ መቆጣጠር የሚችሉት ነገር ላይ ያተኩራሉ፤ ያም ለዚያ ነገር እነርሱ የሚሰጡት ምላሽ ነው።


5ኛ. ሌሎችን ለማስደሰት መጨነቅ

ሰው ለማስደሰት ሲሉ ራሳቸውን ውጥንቅጥ ውስጥ የሚከቱ ሰዎች ታውቁ ይሆን? አሊያም በተገላቢጦሽ ሌሎችን “ለማብሸቅ” ሲሉ አሳራቸውን የሚያዩስ? ሁለቱም በጎ አይደሉም። የአእምሮ ጽናት ያለው ሰው ለሁሉም መልካም እና ፍትሃዊ
ለመሆን ይጥራል፤ ሆኖም ሌላን ሰው ለማስደሰትም ሆነ ለማስከፋት ሲል ያልሆነውን አያስመስልም፤ አቋሙን አይቀያይርም። ይህም ሆኖ፣ አቋሙን ለመፈተሽ ፈቃደኛ ነው፤ ምናልባት ሰዎችን ቢያስከፋም ከእነርሱ በኩል ጉዳዩ ምን እንደሚመስል ለማጤን ፈቃደኛ ነው።

6ኛ. አደጋን (ሪስክን) መፍራት

የአእምሮ ጽናት ያላቸው ሰዎች የተጠና “ሪስክ” መውሰድን አይፈሩም። ይህ ማለት ሳያመዛዝኑ ያገኙት ነገር ውስጥ ሁሉ ዘው ይላሉ ማለት አይደለም። ይሁን እንጂ፣ አደጋ (“ሪስክ”) ያለውን ነገር ጥቅም እና ጉዳቱን መዝነው ለመጋፈጥ አይፈሩም።

7ኛ. ያለፈ ነገር ላይ ችክ ማለት

ያለፈ ነገርን መቀበል፣ ከዚያ የሚገኝ ማበረታቻም ሆነ መሻሻል ያለበት ነገር ካለ መማር አስፈላጊ ነው። ዳሩ ግን ያለፈ ጊዜን እያሰቡ መብከንከንም ሆነ “ደጉን ዘመን” እያሰቡ በቀን ሕልም መዋኘት የአእምሮ ጽናት ያላቸው ሰዎች የማያደርጉት ነገር ነው። አብዛኛውን አቅማቸውን የሚያውሉት የአሁኑን እና መጪውን ጊዜ የተሻለ ማደረግ ላይ ነው።