Get Mystery Box with random crypto!

#ከፈሰሰ_አይታፈስ.. አንዲት ወጣት ሴት ለጉዞ ኤርፖርት ዉስጥ ተቀምጣለች። በመንገደኞች የመጠበ | የስኬት ምስጢሮች

#ከፈሰሰ_አይታፈስ..

አንዲት ወጣት ሴት ለጉዞ ኤርፖርት ዉስጥ ተቀምጣለች። በመንገደኞች የመጠበቂያ ክፍል የምትሄድበትን አዉሮፕላን ትጠብቃለች። አዉሮፕላኑ እንደሚዘገይ ባወቀች ጊዜ ኤርፖርት ዉስጥ ካሉት ሱቆች ኩኪስና መፅሐፍ ገዛች። መጠበቂያ ወንበር ላይ ተደላድላ ተቀምጣ ማንበብ ጀመረች። አጠገቧ እንዲሁ አንድ ሰዉ መፅሔት ያነባል። በሁለት ወንበሮች የጋራ መደገፊያ ላይ ኩኪስ ተቀምጧል። በንባቧ መካከል መተከዣ ሁኗታል። ታድያ ከኩኪሱ አንድ ስትወስድ አጠገቧ የተቀመጠዉ ሰዉዬ አንድ አነሳ። ገረማት።
ሳያስፈቅዳት እንኳ መዉሰዱ አስደነቃት።
ግን ዝም አለች። ቀጥላ እርሷ አንድ ስትወስድ እርሱም ሌላ ወሰደ። አሁን ተበሳጨች። ድፍረቱ አናደዳት። በዚህ አላበቃም፣ እስከ መጨረሻዉ ቀጠለ።
ቅጥል አለች። ግን ንቃ ተወችዉ። በአካባቢዉ ያሉ ሰዎችን አትኩሮት መሳብ አልፈለገችም። ለዚህ ብቻ አይደለም በኩኪስ ምክኒያት ለሚነሳ ረብሻ ሰበብ መሆን አልወደደችም።

እንዲህ...እንዲህ እያለ የመጨረሻዉ አንዲት ኩኪስ ቀረች። ይህ የተረገመ ሰዉ ምን ያደርግ ይሆን? ስትል አሰበችና በቀስታ ማየት ጀመረች። ከዚያም ሰዉየዉ ኩኪሷን ሁለት ቦታ ከፈላትና ግማሹን ወሰደ። ለድፍረቱ ጥግ አጣችለት። ከልክ ያለፈ ስራዓት የለሽ እንደሆነ ደመደመች።

አዉሮፕላን ዉስጥ እንደገባች መነፀር ለማዉጣት ቦርሰዋን ስትከፍት አይኗን ማመን አልቻለችም። ያልተከፈተ የታሸገዉ ኩኪሷ ቦርሰዋ ዉስጥ አለ።
በጣም አፈረች። ተሸማቀቀች። ለካ የእርሷን ኩኪስ ቦርሰዋ ዉስጥ ረስታዉ የሰዉየዉን ነበር ስትበላ የቆዬችዉ።
ከሁሉም በላይ ያፀፀታት ሰዉዬዉ እስከ መጨረሻዉ አንዲት ኩኪስ ድረስ ያካፍላት የነበረዉ ምንም ሳይቆጣና ሳይመረር በደስታ መሆኑ ነበር።

የራሱን ኩኪስ እየተካፈለች ሰዉየዉ ላይ ስትበሳጭበት በመቆየቷ እጅግ አፈረች።
አሁን ይቅርታ ለመጠየቅ እንኳ ጊዜዉ አልፏል። እርሱም በሌላ አዉሮፕላን ወደ ሀገሩ አቅንቷል። እርሱን የማግኘት አንድ ተጨማሪ እድል እንኳ የላትም። ብዙ ተመኘች። ማመስገን፣ ይቅርታ መጠየቅ።
ጉዳዩን ማብራራት...ፈለገች ግን ሁሉም እርሷ ጋ ቀሩ...አልፏል።

አራት የማይጠገኑ ነገሮች አሰበች፦

ድንጋይ ከተወረወረ በኃላ
ቃላት ከተናገርናቸዉ በኃላ
ድርጊቶች ካመለጡን በኃላ
ጊዜ ካለፈ በኃላ

ከፈሰሰ...አይታፈስ።

እንደዚች ሴት የህይወት ቦርሳችንን እንክፈተዉ።
እስካሁን ስንበላዉ የነበረዉ የሌሎች መሆኑን፣ የምንበሳጨዉም ትክክለኛ ባልሆነ ነገር መሆኑ ይገባናል።
የእኛ እንደታሸገ ነዉ፣ የሰዎቹን ግን ጨርሰናል። እኛ ከትርፋችን የማንሰጣቸዉ ሰዎች እነርሱ ግን አንዱን ለሁለት ቆርሰዉ አካፍለዉናል።
የብዙዎች መልካምነት የሚታወቀን ካጠገባችን ከሄዱ በኃላ ነዉ። ብዙ ባሎች የሚስታቸዉን ደግነት ያወቁት ስትሞት ነዉ። ብዙ ሚስቶች ባላቸዉን ያመሰገኑት ሲሞት ነዉ። ነገር ግን ቁጭቱ ሃይለኛ ነዉ። እንደዉም እኛ ኢትዮጵያዉያን ሰዉ ካልሞተ እና ለቆ ካልሄደ አናመሰግንም። ይህ ሀገራችንን የጎዳ ክፉ ባህላችን ነዉ። እንደዉም እንደ ሀገር ስናስብ ሙት አንግሶች ነን ማለት ይቻላል።
ለማንኛውም አስተዉሉ ዛሬ የምንበሳጨዉና የምንቆጣዉ ምን አልባት ባለማዎቅ ሊሆን ይችላልና በኃላ እንዳናፍር አስቀድመን እንጠንቀቅ።

ሁለት ሰዎች ተጣልተዉ አንደኛዉ ዶክተሩን “አንተ መሃይም” እያለ ሊመታዉ ይጋበዛል። አለቃ ገብረ ሀና ደረሱና ለማስታረቅ ቀኝ እና ግራ አስቀምጠዉ ሲዳኙ አንድ ሰዉ ሲያልፍ አይቷቸዉ አለቃ ገብረ ሀና ምን እያደረጉ ነዉ? ቢላቸዉ፦ “ስድብ ቦታ ተለዋዉጦ ቦታ ቦታዉ እየመለስኩ ነዉ”አሉ ይባላል።

ዛሬም ወቀሳ ቦታ ተለዋዉጧል፣
ምስጋናም ያለ ቦታዉ ይነጉዳል።

አንድ ቀን ሁሉም ወደ ቦታዉ ይመለሳል።
አምባሳደር ሚዲያ
እፁብ ድንቅ ሚሽት ይሁንልን!
#ወደዱት፡ ለሌሎችም #ሼር በማድረግ አካፍሉ፡፡
https://t.me/SucessSecret
https://t.me/SucessSecre