Get Mystery Box with random crypto!

በዜሮ የተባዛው አገልግሎት! አንድ ንጉስ አስር አመት ሙሉ በታማኝነት ያገለገለው አገልጋዩ እንዲት | የስኬት ምስጢሮች

በዜሮ የተባዛው አገልግሎት!

አንድ ንጉስ አስር አመት ሙሉ በታማኝነት ያገለገለው አገልጋዩ እንዲት ስህተት ስለሰራ ብቻ ቅጣትን አስተላለፈበት፡፡ በንጉሱ ሕግ መሰረት ማንኛውም ስህተት የሰራ አገልጋይ በኃይለኛነታቸውና በተናካሽነታቸው የታወቁት የንጉሱ ውሾች ወደሚኖሩበት ግቢ ለቅጣት ታልፎ ይሰጣል፡፡

ይህንን የንጉሱን ውሳኔ የሰማው ታማኝ አገልጋይ በሁኔታው በጣም አዘነ፡፡ እሱን ያሳዘነው የተላለፈው ቅጣት ሳይሆን፣ ለአስር አመታት ካለምንም ስህተት አገልግሎ፣ አንዲት ስህተት ብቻ ስለተገኘችበት የንጉሱ መጨከን ነው፡፡

ይህ አገልጋይ ቁጭ ብሎ፣ “ይህንን ቅጣት አስቀረሁትም፣ አላስቀረሁት ንጉሱ ግን ይህንን ጥሩ ያልሆነ ልምምድ የሚያቆምበትን አንዲት ትምህርት ባስተምረው ደስ ይለኛል” ብሎ አሰበና አንድ ብልሃት መጣለት፡፡

ንጉሱንም፣ “ቅጣቱን እቀበላለሁ፣ ቅጣቱ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ግን አስር ቀን ይሰጠኝና ከዚያ በኋላ በፈቃዴ ለቅጣቱ እመጣለሁ” ብሎ ጠየቀው፡፡ ንጉሱም ፈቀደለት፡፡

በእነዚህ አስር ቀናት ለውሾቹ የሚሆንን ምግብ አዘጋጅቶ እነሱ ያሉበት ግቢ በመሄድና ቀስ ብሎ በመቅረብ እያበላቸው፣ እየተንከባከባቸውና እያሻሻቸው በሚገባ ካገለገላቸው በኋላ በአስረኛው ቀን ወደ ንጉሱ መጣ፡፡ ፍርዱ አልቀረለትም ነበረና ወደውሾቹ ግቢ እንዲጣል ትዝዛዝ ተላለፈበትና ተጣለ፡፡ ውሾቹ ለአስር ቀን የተንከባከባቸውንና ያገለገላቸውን ይህንን ሰው ምንም ነገር አላደረጉትም ነበር፡፡

ንጉሱም ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተ ሁኔታ በመሆኑ ተገርሞ አስጠራውና የተፈጠረውን ጠየቀው፡፡ አገልጋዮም፣ “ንጉስ ሆይ፣ እርሶን አስር አመት በታማኝነት አገልግዬ አንዲት ጥፋት ስለተገኘብኝ ብቻ ያ ሁሉ ታማኝነቴና አገልግሎቴ ተረሳና ምህረትም አላገኘሁም፡፡ እነዚህ ውሾች ግን ለአስር ቀናት ብቻ ስላገለገልኳቸው ምንም እንኳን ጥፋተኛ ሆኜ ለእነሱ ታልፌ ብሰጥም ያንን አገልግሎቴን ባለመርሳት ምንም አላደረጉኝም” አለው ይባላል፡፡

ንጉሱ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ይህንን ባህሪውን ለማረም ክፍት ወደመሆን እንደመጣ ይነገራል፡፡

ሰዎች ያሳዩንን የብዙ ዓመታት ታማኝነትና አገልግሎት በአንዲት ስህተት ምክንያት በዜሮ አናባዛው፡፡ ይቅርታን እንልመድ! ለሰዎች ሁለተኛ እድልን መስጠትን እንልመድ! ውለታ ቢሶች አንሁን!

መልካም ቀን!
እፁብ ድንቅ ቀን ይሁንልን!
#ወደዱት፡ ለሌሎችም #ሼር በማድረግ አካፍሉ፡፡
https://t.me/SucessSecret
https://t.me/SucessSecre