Get Mystery Box with random crypto!

በሕይወታችን አብዛኛዎቹ ነገሮች ልክ እንደጽንስ ናቸው፡፡ ጽንስ ገና እንደተፈጠረ ወይም የመወለጃው | የስኬት ምስጢሮች

በሕይወታችን አብዛኛዎቹ ነገሮች ልክ እንደጽንስ ናቸው፡፡ ጽንስ ገና እንደተፈጠረ ወይም የመወለጃው ወቅት ሳይደርስ አይወለድም፣ ቢወለድም ወይ ጎዶሎ ሆኖ ይኖራል ወይም ደግሞ ካለጊዜው ስለተወለደ ካለጊዜው ይሞታል፡፡

ጽንስ በጽንስነት ዘመኑ በቂ ጊዜን ካሳለፈ በኋላ እውነተኛውን አለም ለመቋቋም የሚችልበት ደረጃ ሲደርስ ነው መወለድ ያለበት፡፡ ጊዜው ሲደርስ ደግሞ እኛ ሳንገፋው ራሱ ገፍቶ መምጣቱ አይቀርም፡፡

ብዙ ነገራችን የሚበላሽብን ካለጊዜው ለመውለድ ስለምንሞክር ነው፡፡ ጓደኛን እንይዛለን፣ ጓደኝነቱ ፍቅርን ጸንሶ፣ ጽንሱ ደግሞ ጊዜውን ወስዶ በተፈሯዊው መንገድ እንዲወለድ ጊዜ አንሰጠውም፡፡ ስለዚህም እናጣድፈዋለን፣ ቶሎ እንዲፈጠር እንፈልጋለን፣ እንወልደዋለን፡፡ የተፈጥሮን ሂደት ተከትሎ አድጎ እንዲወለድ ጊዜን ከመስጠት ይልቅ አዋክበን ወደመኖር ልናመጣው እናግለበልበዋለን፡፡ ከዚያም ካለጊዜው የተወለደን አንካሳ፣ ሰባራና ጤናቢስ ነገር ይዘን መላው ይጠፋብናል፡፡

ያለን ማሕበራዊ ግንኙነት፣ ስራ፣ ንግድም ሆነ ሌሎች ነገሮቻችን የዚህ መርህ ተገዢ ናቸው፡፡ አንድን ነገር ከጀመርን በኋላ ነገሩ ተፈጥሯዊውን ሂደት እስኪጨርስ መታገስ አስፈላጊ ነው፡፡

ይህንን የተፈጥሮ ሂደት መከተል እውነተኛውን ከውሸተኛው ሕይወት ያለውን ከሌለው የምንለይበት ብቸኛ መንገድ ነው፡፡


በምድር ላይ የምናደርጋቸው መልካም ነገሮች ሁሉ በሰማይ ላይ የዘላለም ደመወዝ ሆነው ይከፈሉናል፡፡ ሁሌም ቢሆን ከክፋት ይልቅ በጎ በጎውን ነገር እናስብ መልካምነት ለራስ ነው፡፡

መልካም ቀን!
እፁብ ድንቅ ቀን ይሁንልን!
#ወደዱት፡ ለሌሎችም #ሼር በማድረግ አካፍሉ፡፡
https://t.me/SucessSecret
https://t.me/SucessSecre