Get Mystery Box with random crypto!

ካነበብኩት የወደድኩት ድንቅ እይታ 'ይህም ያልፋል' በአንድ ወቅት ነበር አንድ ሰው የሰው | የስኬት ምስጢሮች

ካነበብኩት የወደድኩት ድንቅ እይታ

"ይህም ያልፋል"
በአንድ ወቅት ነበር አንድ ሰው የሰው ማሳ ተከራይቶ ሲአርስ አንድ መንገደኛ አይቶ ይጠይቀዋል የአንተ ማሳ ነውን?ይለዋል አይ ተከራይቸ እያመረትኩ ነው ይህም ያልፋል ይለዋል፤

በዓመቱ ይህ ገበሬ የራሱ ማሳ ኑሮት ነገር ግን በሬ ስለሌላው በአዷማ እየቆፈረ ያ ሰውዬ አየው ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ የቀደመ ጥያቄውን ጠየቀው ሰውዬውም መልሱ ይህም ያልፋል ነበር።

አሁንም በሌላ ግዜ እነዚህ ሰወች ተገናኙ ገበሬው በሬ ኑሮት አርሶ አዝምሮ አውድማ ላይ እየወቃ ያ መንገደኛ ሰውዬ መጣ አሁንም ይህም ያልፋል አለው ሰውዬውም በመልሱ ተገርሞ ሄደ።

ከጥቂት አመት በኃላ አገሪቱ ከተማ ሁና ያ ገበሬም ሆቴል ገንብቶ ተገናኙ ሰውዬውም ይህ የማነው ብሎ ጠየቀ ያ ቀድሞ የሚያውቀው የዛ ገበሬ ነበር ፌት ለፊትም እዛው ሆቴል ውስጥ ተገናኝተው ተጠያየቁ ይህም ንብረት ያልፋል ብሎ መለሰለትና ተለያዩ ፤

በአመቱ የዚያች ሀገር ሰዎች ተሰብስበው ይህ ሰው ትኁትና ታዛዥ በዚያውም ላይ ቅን ሰው ነው ስለዚህ የከተማዋ ከንቲባ ሆኖ ያገልግለን ብለው ሹመውት ተገናኙ ድሮ እንደሚለው ይህም ስልጣን ያልፋል አለው አሁንም ዛሬ ስልጣን ላይ ተቀምጦ እንዲህ ይለኛል ብሎ ተገርሞ ሄደ።

ከብዙ አመታት በኃላ ያ መንገደኛ መጥቶ የዚህች ሀገር ከንቲባ የት ሄዶ ነው ብሎ ጠየቀ ሲጠይቅ እንደ ሞተ ነገሩት ወደ መቃብሩም እንዲወስዱት ጠይቆ ወሰዱት በመቃብሩም ላይ ይህም ያልፋል የሚል ቃል ተፅፎ አገኘ እንዴ ከሞት በኃላ ደግሞ ምን አለ ብሎ ነው ይህም ያልፋል ያፃፈ ብሎ ሊቃውንትን ጠየቀ እነሡም አስረዱት ይህ ያየኀው ስጋዊ ሞት ያልፋል የማያልፋል የፈጣሪ መንግስት ብቻ ነው ብለው አስተማሩት።

አንዳንዴ እንደ ተራራ የከበደን ሀዘን አልፎ በደስታ ይተካል ችግራችን በዝቶ ተስፋ በቆረጥንበት ወቅት ይህም እንደሚያልፍ እንገንዘብ።

ሁሌም አመስጋኝ እንሁን

ሼር
https://t.me/SucessSecret
https://t.me/SucessSecret