Get Mystery Box with random crypto!

መንፈስ ቅዱስ 𝐇𝐎𝐋𝐘 𝐒𝐏𝐈𝐑𝐈𝐓

የቴሌግራም ቻናል አርማ salvationisonlyjesus — መንፈስ ቅዱስ 𝐇𝐎𝐋𝐘 𝐒𝐏𝐈𝐑𝐈𝐓
የቴሌግራም ቻናል አርማ salvationisonlyjesus — መንፈስ ቅዱስ 𝐇𝐎𝐋𝐘 𝐒𝐏𝐈𝐑𝐈𝐓
የሰርጥ አድራሻ: @salvationisonlyjesus
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.01K
የሰርጥ መግለጫ

ምስክርነት
🔶 @jesus_op_6 🔶
✏️ አዳዲስ መዝሙር
✏️ መንፈሳዊ ትምህርቶች
✏️የመዝሙር አልበሞች
YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE በማድረግ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን
☞#YouTube
https://youtube.com/channel/UCeCQ43XK7f-xOz0_lO-cHJw

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-17 17:06:54 ብዙ ወጣቶች በፖረኖግራፊ (በሰጋ) እና በዝሙት ዙሪያ በኃጥያት ሲወድቁ ቀስ በቀስ ቤተክርስቲያን ይቀራሉ ። እንደዚህ ያለ ኃጥያት እያደረግኩ እንዴት ወደ እግዚአብሄር ቤት እሄዳለው? ይላሉ

ወንድሜ የአዲስኪዳን ቤተመቅደስ አንተ ነህ በቤትህ ሆነህም በዛ ኃጥያት የምትቀጥል ከሆነ ወደ ቤተክርስቲያን ባለመሄድህ እግዚአብሄርን ከመበደል አልተቆጠብክም።

ታዲያ መፍትሄ ምንድነው ???

እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።(ያዕ 5፡16)

በህብረት ውስጥ መሰራት አለ
በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብንሆንም መጣል ያለብንን ጉድፍ በህብረት ውስጥ እግዚአብሄር ያስጥለናል

ስለዚህ ወንድሜ አንተ ብቻ ምስጢር አርገህ ብቻህን ለምን ትጎዳለህ ? ብዙዎችን መንፈስ ቅዱስ እየረዳ ነው ዛሬ አንተንም መንፈስ ቅዱስ ልፈታህ ይፈልጋል @jesus_op_6 ላይ ያለህን ችግር እስክ ንገረኝ ደግሞ እስከመቼ ነው እንደዚህ አይነት ነገር ውስጥ የምትኖረው ??? #Share # share #share #share_በጌታ_ፍቅር_እለምናችኋለሁ

ቻናሉን ይቀላቀሉ
451 views, 201 yafeti_off, 14:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 17:05:34 በክርስቶስ ኢየሱስ አዳኝነት የሚያምን ሰው በሰው ፊት ስለ እርሱ ሊመሰክር ግድ ነው፡፡ እውነት እናንተ የክርስቶስ ተከታይ ከሆናችሁ ስለ እርሱ በሰው ፊት ለመመስከር አታፍሩም፡፡

ኢየሱስ አንድ የገባላችሁ ቃል አለ! ዛሬ በሕይወት በምድር ሳላችሁ ስለ እርሱ በሰዎች ፊት ሳታፍሩ ከመሰከራችሁ በሚመጣው የትንሳኤ ዓለም ውስጥ እርሱ ስለ እናንተ በአብ ፊት፤ በመልአክት ፊት፤ በቅዱሳን ሁሉ ፊት ይመሰክርላችኃል፡፡

እናንተ ዛሬ በወደቀው ዓለም ውስጥ ስለ ኢየሱስ ስትመሰክሩ፤ ኢየሱስ በአዲሱ የትንሳኤ ዓለም ውስጥ ስለእናንተ ይመሰክራል፡፡ እናንተ በሰው ፊት ስለኢየሱስ ስትመሰክሩ፤ እርሱ በአባቱ ፊት ስለእናንተ ይመሰክራል፡፡ ሰው ስለ ሰው እንኳን በሰው ፊት ይመስክር የለ! ስለሞተላችሁ መመስከር ያሸማቅቃል እንዴ!

ስለየትኛው ክብር ብላችሁ ነው ስለ ኢየሱስ በጓደኞቻችሁ ፊት መመስከር ያሳፈራችሁ? ነው ወይስ እናንተ በኢየሱስ አፍራችሁ ነው? ብታውቁ እናንተ ስለ ኢየሱስ የምትመሰክሩት ኃጢአተኛ በሆነው አለምና ሰው ፊት ነው፡፡ ኢየሱስ ስለ እናንተ ሳያፍር የሚመሰክረው ጻዲቅ በሆነው አባቱና በመልአክት ፊት ነው፡፡

ዛሬ ላይ ስለ ኢየሱስ በየአደባባዩ ሲመሰክሩ የምታዩአቸው ተከፍሎላቸው አልያም ተገደው እንዳይመስላችሁ የወንጌል እውነት ገብቶአቸው የክርስቶስ ፍቅር ተረድተው ነው፡፡ ስለ ኢየሱስ የሚመሰክሩ በሰማይ ታላቅ ክብር ይጠብቃችኃል፡፡

"፤ ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።" [ ማቴ 10፥33 ]
1.2K views𝒔𝒆𝒃𝒔𝒊𝒃𝒆_𝒐𝒇𝒇𝒊𝒄𝒊𝒂𝒍, 14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 17:05:34 እግዚአብሔርን እንዴት እናመልካለን? የአመልኮ ሥርአት:-

እግ/ርን የምናመልከው በእውነተኛ መንፈስና በፍጹም ልብ ነው::

፨በመጽሐፍ ቅዱስ የብዙ ሰወች የአመላለካቸው ሥርአት የተለያየ ብሆንም እንኳ በእግ/ር ፈት ተቀባይነትን አግንቷል

#ዳዊት በመዝለል እግ/ርን አመለከ
2ኛ ሳሙ 6:17።

#አብርሃም በመታዘዝ እግ/ርን አመለከ።
ዘፍ 22:1-1።

#ሙሴ በአክብሮት ፍቱ በመውደቅ እና
ጫማውን በማውለቅ እግ/ርን አመለከ ዘፀ 3:1-7።

#ዳንኤል በአንድ ቀን ሦስት ጊዜ በመንበርከክ እግ/ርን አመለከ ዳን 6:10።

#ዮሐንስ ፀጥ ብሎ በፍቱ በመውደቅ እግ/ርን አመለከ ራዕ 1:10።

አምልኮን አምልኮ የምያደርገው አካላዊና ስሜታዊ እንቅስቃሴወሰ ሳይሆን በእውነት እና በመንፈስ የምናደርገው የመሰጠት ሕይወት ነው።

@join & @share
472 views𝒔𝒆𝒃𝒔𝒊𝒃𝒆_𝒐𝒇𝒇𝒊𝒄𝒊𝒂𝒍, 14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 18:42:21 የበለዓም ትምህርት

°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
(ዘኁልቁ24&25)(2ጴጥ2:15) (ይሁዳ1:11)(ራዕ2:14)
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ጠላት ሰይጣን ሁሌ እኛን የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ እንደሚዞር የእግዚአብሔር ቃል ይነግረናል ሁሌ የሚዞርበት ምክንያቱ ተስፋ አለመቁረጡ ነው ሁሌም እኛን ለማጥቃት ይሞክራል አባታችን እግዚአብሔር ግን ስለሚጠብቀን በሰላም እንኖራለን ጠላት ሁሌ ይረግመናል፣ ያስፈራራናል፣ ክፉ ነገር ይመኝብናል አሁንም ግን እኛ #ምንም #አንሆንም አንድ ነገር እስከምናደርግ ድረስ በዛ ነገር ከተገኘንለት ግን መረቡ ውስጥ እንገባለን ይሔም ጉዳይ የበለአም ትምህርት ነው በብሉይ ዘመን አንድ ባላቅ የሚባል ንጉሥ በለዓም የሚባልን 'ነቢይ' አስጠርቶ የያዕቆብን ልጆች አይሁድን ሊያስረግም ሞከረ ነገር ግን አልሆነም እግዚአብሔር የተባረከ ህዝብ ነው አትርገመው አለው (እኛም በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍረራ በመንፈሳዊ በረከት መባረካችንን አስታውሱ) እናም በለአም ሊረግም ሲል ግን ከአንደበቱ ባርኮት ነበር የሚወጣው በሗላ ላይ ግን የእስራኤላውያንን ደካማ ጎን ስላወቀ አንድ ክፉ ምክር በመስጠቱ ብዙ እሰስራኤላውያን ሊቀሰፉ ችለዋል እርሱም ያደረገው ሕዝቡ ከሌላ ህዝብ ጋር በማመንዘር እንዲረክስና ህዝቡ ቅድስናውን እንዲያጣ ነበር እንዳለውም ብዙ እስራኤላውያን ከእግዚአብሔር መንገድ ዞር በማለታቸው ጠፉ እኛም ከዚህ የምንማረው ሰይጣን ቅድስናችንን በማጉደፍ እግዚአብሔር ከሰራልን ብርቱ ቅጥር በአመጻ እንድንወጣ እና ለጥፋት እንድንጋለጥ ያደርገናል ስለዚህ ጌታ በሚሰጠን ጸጋ ከጌታ ፍቃድ ከሚያወጡን ለስጋ ከመመቹ አጥፊ ከሆኑ የዘመናችን በለዓም ትምህርቶች መጠበቅ ነው (መክብብ10:8) ላይ ቅጥርን የሚያፈርስ እባብ ትነድፈዋለች ይላል ስለዚህ የቅድስና ቅጥር መፍረስ የለበትም ማለት ነው መጠንቀቅ ያለብን የጠላትን እርግማን ሳይሆን ወደ ልብ የሚገባና የሚመርዘውን የጠላትን ክፉ ትምህርት ነው።
#ጸሎት
እግዚአብሔር ሆይ ስለ ቃልህ በልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ተባረክ አባት ሆይ ሕይወታችንን ከሚያበላሽ ከቅድስና እንድንጎድል ከሚያደርግ ከበለዓም ምክር ልባችንን ጠብቅ ጌታ ሆይ በልባችን ያለ ማንኛውም ክፉ አሳብ በልጅህ ደም አስወግድልን የጠላትን ሀሳብ እንዳንስት ልባችንን በማስልዋል ሙላ ጸጋህ ከአለማዊ ምኞት ይጠብቀን አብ አባት ሆይ በአለም ምድረበዳ በመንፈስህ ምራን እጃችንን ይዘህ ምራን ስለሰማኸን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተባረክ! ክብር ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ይሁን አሜን፡፡

#join and#share #share
386 views𝒔𝒆𝒃𝒔𝒊𝒃𝒆_𝒐𝒇𝒇𝒊𝒄𝒊𝒂𝒍, 15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 22:46:43 የማን ነህ?......በማን ነህ?
ምላስህ የክርስቶስ እንጂ ያንተ እንዳልሆነ ሲገባህ አትሳደብበትም!!

ጥርስህ የክርስቶስ እንጂ ያንተ እንዳልሆነ ሲገባህ በሰው ውድቀት አትስቅበትም!!

ጆሮህ የክርስቶስ እንጂ ያንተ እንዳልሆነ ሲገባህ የማይገባውን አትሰማበትም!!

አይንህ የክርስቶስ እንጂ ያንተ እንዳልሆነ ሲገባህ ወደ መጥፎው አታይበትም!!

እጅህ የክርስቶስ እንጂ ያንተ እንዳልሆነ ሲገባህ አትሰርቅበትም!!

እግርህ የክርስቶስ እንጂ ያንተ እንዳልሆነ ሲገባህ ወደ ክፋት አትሄድበትም!!

አንተ የክርስቶስ እንጂ የራስህ እንዳልሆንክ ሲገባህ ለራስህ አትኖርም!!

አንተ ደግሞ የራስህ አይደለህም!!

የራስህ ሕይወት የለህም!!

የራስህ ኑሮ የለህም!!

የራስህ ሩጫ የለህም!!

አንተ ራስህ የለህም!!

የክርስቶስ ነህ!!..........በክርስቶስ ነህ!!

❝ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ #እኔም_አሁን_ሕያው_ሆኜ_አልኖርም #ክርስቶስ_ግን_በእኔ_ይኖራል፤ #አሁንም_በሥጋ_የምኖርበት_ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።❞
—ገላትያ 2: 20

❝በሕይወት ሆነን #ብንኖር_ለጌታ እንኖራለንና፥ #ብንሞትም_ለጌታ እንሞታለን። እንግዲህ በሕይወት ሆነን #ብንኖር ወይም #ብንሞት_የጌታ_ነን።❞
—ሮሜ 14: 8

sʜᴀʀᴇ◈ JOIN ◈sʜᴀʀᴇ

⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
sebsibe official
"""“""""""""“""""""""""""""""“"""""""""
╔════ஜ۩۞۩ஜ════╗
@SalvationisonlyJesus
╚════ஜ۩۞۩ஜ════╝
⇘⇘⇘⇘⇘SHARE⇘⇘⇘⇘⇘
── ❖ ── ✦ ── ❖ ──
487 views𝒔𝒆𝒃𝒔𝒊𝒃𝒆_𝒐𝒇𝒇𝒊𝒄𝒊𝒂𝒍, 19:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 21:32:01 እንደ ሕልም በሚበንን፣ እንደ ሣር ፈጥኖ በሚጠወልግ፣ እንደ እንፋሎት በሆነ፡ እጅግ አጭር ሕይወት ከእግዚአብሔር ጋር የመታረቅን ጉዳይ ለነገ የምትሉ ወገኖቼ ለንስሐ ጊዜ ሳላችሁ ከኃጢአታችሁ ተመለሱ፣ በኢየሱስ ክርስቶስም ጌታነትና አዳኝነት እመኑ፤ ራሳችሁን ክደችሁ እርሱን መከተል ጀምሩ። በዚህች አጭር ሕይወት ልታደርጉ የምትችሉት ለዘላለማዊ ደስታ ፋይዳ ያለው ብቸኛ ነገር ይህ ነውና። አይ ካላችሁማ ለዘላለም ስቃይ መጓዛቹን ትቀጥላላችሁ። ፍጻሜ ለሌለው ዘመን የሃያሉን አምላክ ቁጣ ስትጨልጡ ትኖራላችሁ።
625 views𝒔𝒆𝒃𝒔𝒊𝒃𝒆_𝒐𝒇𝒇𝒊𝒄𝒊𝒂𝒍, 18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 06:12:15 የሆነ ወንጀል ሰርተህ ብትከሰስና ከፍርድ ወንበር ፊት ቆመህ ከሕጉ አንፃር መከራከር ባትችል ስላንተ እንዲከራከርልህ ጠበቃ በገንዘብ ትቀጥራለህ።

ጠበቃ ማለት አንተን ተክቶ የሚቆም "ምትክ" ማለት ነው።
አንተ ዝም ትልና ጠበቃህ በዳኛው ፊት ቆሞ ያደረከውን "አላደረገም" እያለ or የሰራኀውን ስራ "ከሕጉ አንፃር ልክ ነው፤ መከሰስ የለበትም" እያለ ስላንተ ሽንቱን ገትሮ ይከራከርልሃል።

ይሄ ሁሉ ሆኖ ግን እንደ አጋጣሚ ጠበቃህ ቢሸነፍ "ወንጀለኛ" ተብሎ የሚቀጣው እሱ ሳይሆን በእርሱ ውስጥ የተደበቅከው አንተ ነህ።
ጥብቅና በሰው አእምሮ ይሄን ያክል ብቻ ነው።



"በድላችኋል ፡ አጥፍታችኋል" ተብለን በከሳሽ ዲያብሎስ ተከሰን ከፍርድ ወንበር ፊት ቆምን። አንዳንዶች ጠበቃ እንዲሆንላቸው የበግ፡ የዋኖስ፣ የፍየል፣ የኮርማ… ደም በገንዘባቸው አመጡ፤ ነገር ግን የነዚህ ደም ተከራክሮ ማሸነፍና እነርሱን ነፃ ማውጣት አልቻለም።
እኔ ግን ይህን ደም እንኳን ይዤ ለመግባት አልታደልኩም ነበር።

እና በዚህ ሁሉ መኃል አንድ ከነጭራሹ የማላውቀው እርሱ ግን ጨርሶ የሚያውቀኝ ከፍቅር የሆነ ጠበቃ "እኔ ልከራከርልህ" ብሎ ከፍርድ ወንበር ፊት ቆመ።

ከሳሽ ሰይጣንም ክሱን ቀጠለ
"አመንዝሯል፣ ተሳድቧል፣ ዘርፏል፣ ሰው ገሏል…" እያለ በእኔ ያየውን ሁሉ ለፍርድ ቤቱ አንድ በአንድ ተረከላቸው።
ይናገር የነበረው ሁሉም እውነት ነበር።

የኔ ጠበቃ ግን ዝም ብሎ ይሰማ ነበር፤ እንደውም ስለኔ በመከራከር ፈንታ "እውነት ነው፤ አጥፍቷል" እያለ የከሳሼን ቃል ያፀናው ነበር። የሚሆነው ነገር ግራ ቢያጋባኝም ለካ ደግመኛ እንዳልከሰስ ፈልጎ ነው።

እናም በመጨረሻ ፍርድ ቤቱ የሀጢአቴን ብዛት አይቶ የሞት ፍርድ ፈረደብኝ።
ፍርዴን ለመቀበል እራሴን አሳምኜ ሳለሁ ጠበቃዬን "ልሞት ነው እኮ በቃ" ስለው "ጠበቃህ እኮ ነኝ" አለኝ።

ለካስ የእርሱ ጥብቅና ከፍርድ ወንበር ፊት ቆሞ እስከመከራከር ብቻ ሳይሆን፤
ሞት እኔን ፈልጎ ሲመጣም "ጠበቃው ነኝ" ብሎ እኔን ተክቶ እስከመጋፈጥ ድረስ ነው።

በቆምኩ ሰዓት አቅፎ በወደቅኩ ጊዜ ከውስጡ ላያወጣኝ
በወደቅኩ ሰዓት ይዞ በቆምኩ ጊዜ ላይተወኝ ምትኬ ሆነልኝ።

ማንም አውጥቶ ላይቀጣኝ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ተደብቅያለው።
ሞቱን ሳይሆን ሞቴን ሞተልኝ።
ሕይወቴን ሳይሆን ሕይወቱን ሰጠኝ።

በመጨረሻም "ይህን ሁሉ የምትሆንልኝ ለምንድ ነው?" ብዬ ጠየኩት።
"ስለወደድኩህ ነው!" ብሎ መለሰልኝ።
አሁንም መልሼ "ለምን ወደድከኝ" አልኩት።
"ስለወደድኩህ" ብሎ አቀፈኝ።
ጭራሽ የወደደኝ ሁላ ስለወደደኝ ነው።
509 views𝒔𝒆𝒃𝒔𝒊𝒃𝒆_𝒐𝒇𝒇𝒊𝒄𝒊𝒂𝒍, 03:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 06:11:43 ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,#እምነት,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
አባቶችም በእምነት…………….. እኔም በእምነት /ዕብ.11/

አቤል………………………………’’በእምነት’’ መስዋዕቱ ተቀባይነት አገኘ፡፡

ሄኖክ………………………………..’’በእምነት’’ ሞትን እንዳያይ ተወሰደ፡፡

ኖህ………………………………….’’በእምነት’’ አለምን በጽድቁ ኮነነ፡፡

አብርሃም………………………….’’በእምነት’’ ታዘዘ፤ ጸደቀ፡፡

ሣራ……………………………………’’በእምነት’’ ሀይልን አገኘች፡፡

አብርሃም…………………………….’’በእምነት’’ ልጁን ለእግዚአብሔር አቀረበ፡፡

ይስሃቅ………………………………..ሊመጣ ስላለው ነገር ‘’በእምነት’’ ያዕቆብንና ኤሳውን ባረካቸው፡፡

ያቆብ………………………………….’’በእምነት’’ የዮሴፍን ልጆች ባረካቸው፡፡

ዮሴፍ…………………………………’’በእምነት’’ ስለአጥንቱ አዘዛቸው፡፡

የሙሴ ቤተሰቦች…………………..’’በእምነት’’ ሙሴን ሶስት ወር ሸሸጉት፡፡

ሙሴ…………………………………የፈርኦን የልጅ ልጅ እንዳይባል ‘’በእምነት’’ እንቢ አለ፡፡

ሙሴ…………………………………አጥፊው የበኩር ልጆችን እንዳይነካ ደምን መርጨትን ‘’በእምነት’’ አደረገ፡፡

እስራኤሎች…………………………በደረቅ ምድር እንደሚያልፍ በኤርትራ ባህር ‘’በእምነት’’ ተሻገሩ፡፡

የኢያሪኮ ቅጥር……………………ሰባት ቀን ከዞሩበት በኋላ ‘’በእምነት’’ ወደቀ፡፡

ረዓብ………………………………..’’በእምነት’’ ሰላዮችን በሰላም ስለተቀበለቻቸው ከማይታዘዙት ጋር አልጠፋችም፡፡

ቀሪ አባቶችም ሁሉ……………………’’በእምነት’’ መንግስታትን ድል ነሱ፡፡
…………………………………………………………………………………………….
“እነዚህም ሁሉ በእምነታቸው ተመስክሮላቸው ሳሉ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አላገኙም፤ ያለ እኛ ፍጹማን እንዳይሆኑ እግዚአብሔር ስለ እኛ አንዳች የሚበልጥ ነገርን አስቀድሞ አይቶ ነበርና፡፡” ዕብ. 11፡40
 ወዳጄ ጉዳዩ የማመንህ እንጂ የመስራትህ አይደለም፤ በብሉይ እንኳ የተመሰከረላቸው በስራቸው አይደለም፡፡ ማንም በስራው እግዚአብሔርን አያስደስትም፡፡ እግዚአብሔር በአንዱ ልጁ ሰው ሆኖ በእርሱ ተደስቷል!!! አሁን ማድረግ ያለብህ በመስራት ለማስደሰት ከመጣር ይልቅ በልጁ ላይ ባለህ እምነት መመላለስ ጀምር፡፡
464 views𝒔𝒆𝒃𝒔𝒊𝒃𝒆_𝒐𝒇𝒇𝒊𝒄𝒊𝒂𝒍, 03:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 11:27:12 እግዚአብሔርን ለሚወዱ ሰዎች...
የሚሰጡ በረከቶች

❶ እግዚአብሔርን ለሚወዱ ነገር ሁሉ ለበጎ ይደረግላቸዋል (ሮሜ 8፥28)
❷ እግዚአብሔርን ለሚወዱ አይን ያላየውን፣ ጆሮ ያልሰማውን፣ በሰው ልብም ያልታሰበ ታላቅ በረከት አዘጋጅቷል (1 ቆሮ 2፥9)
❸ እግዚአብሔርን ለሚወዱ ይቅርታ እና ጥበቃ ይደረግላቸዋል
❹ እግዚአብሔርን ለሚወዱ እድገት ይሆንላቸዋል
❺ እግዚአብሔርን ለሚወዱ ብልጥግና ይሆንላቸዋል
❻ እግዚአብሔርን ለሚወዱ የሰላም ተስፋ ገብቷል
❼ እግዚአብሔርን ለሚወዱ እስከ ሺ ትውልድ ድረስ ምሕረት እና ፍቅሩን ያሳያል
❽ እግዚአብሔርን ለሚወዱ በኃይል እንደወጣ ፀሐይ ይሆናሉ (መሳ 5፥31)
❾ እግዚአብሔርን ለሚወዱ ሕይወት ይሆንላቸዋል (ዘዳ 30፥19-20)
❿ እግዚአብሔርን ለሚወዱ እግዚአብሔርን ለሚወዱ መጨመር ይሆንላቸዋል (ዘዳ 19፥9)
⓫ እግዚአብሔርን ለሚወዱ ከእነርሱ የበረቱ ጠላቶቻቸውን ማሳደድ ይችላሉ (ኢያሱ 23፥9-11)
⓬ እግዚአብሔርን ለሚወዱ የጸሎታቸውን መልስ በጸሎት ቤት ውስጥ ያገኛሉ
⓭ እግዚአብሔርን ለሚወዱ በሁሉም አቅጣጫ ልማት ይሆንላቸዋል (መዝ 122፥6)
⓮ እግዚአብሔርን ለሚወዱ ሁልጊዜ ምሕረት አለ (መዝ 119፥132)
⓯ እግዚአብሔርን ለሚወዱ ጥበቃው ያለማቋረጥ ይሆንላቸዋል (መዝ 45፥17-20)
⓰ እግዚአብሔርን ለሚወዱ የእግዚአብሔር አብሮነት ከእነርሱ ጋር ይሆናል በሕልውናውም ይባርካቸዋል (ዩሐ 14፥21-23)
432 views𝒔𝒆𝒃𝒔𝒊𝒃𝒆_𝒐𝒇𝒇𝒊𝒄𝒊𝒂𝒍, 08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 11:27:09 #መንፈስቅዱስ #ማነው ? (2)

~»>መንፈስ ቅዱስ አካል አለው
~»"መንፈስ" የሚለውን ቃል በእብራይስጥ "ሩህ" በግሪክ "ኑማ" ከሚነፍስ ንፋስ ጋር ያገናኘዋል ከዚህ የተነሳ መንፈስቅዱስን አካል የሌለው የሚነፍስ ኃይል አርጎ የመረዳት አዝማሚያዎች አሉ
~»>መንፈስቅዱስ እንደ አብ እና ወልድ ሁሉ አካል ያለው መሆኑን በቅዱሳን መፅሀፍት ተፅፎአል::
~»በተደጋጋሚ "እኔ" አያለ በመናገሩ ምክንያት አካል ያለው መሆኑን ያሳያል
ዮሐንስ 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵-¹⁶ ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤
¹⁷ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።
“አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።”
— ዮሐንስ 14፥26
ዮሐንስ 16
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።
¹⁴ እርሱ ያከብረኛል፥ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋልና።
~»>እየሱስ ክርስቶን በመተካት ሌላ አፅናኝ (ጳራቅሊጦስ) በመባሉ
“.....ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤”
— ዮሐንስ 14፥15-16
~»>መንፈስ ቅዱስ እውቅት ስሜት ፈቃድ ያለው አምላክ ነዉ::
“አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።”
— ዮሐንስ 14፥26
“ይህን ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድ ለእያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 12፥11
“ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።”
— ኤፌሶን 4፥30
(እብ 3:7-9 ሐዋ 16:6)

ተባርካችሁአል!
422 views𝒔𝒆𝒃𝒔𝒊𝒃𝒆_𝒐𝒇𝒇𝒊𝒄𝒊𝒂𝒍, 08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ