Get Mystery Box with random crypto!

የማን ነህ?......በማን ነህ? ምላስህ የክርስቶስ እንጂ ያንተ እንዳልሆነ ሲገባህ አትሳደብበትም! | መንፈስ ቅዱስ 𝐇𝐎𝐋𝐘 𝐒𝐏𝐈𝐑𝐈𝐓

የማን ነህ?......በማን ነህ?
ምላስህ የክርስቶስ እንጂ ያንተ እንዳልሆነ ሲገባህ አትሳደብበትም!!

ጥርስህ የክርስቶስ እንጂ ያንተ እንዳልሆነ ሲገባህ በሰው ውድቀት አትስቅበትም!!

ጆሮህ የክርስቶስ እንጂ ያንተ እንዳልሆነ ሲገባህ የማይገባውን አትሰማበትም!!

አይንህ የክርስቶስ እንጂ ያንተ እንዳልሆነ ሲገባህ ወደ መጥፎው አታይበትም!!

እጅህ የክርስቶስ እንጂ ያንተ እንዳልሆነ ሲገባህ አትሰርቅበትም!!

እግርህ የክርስቶስ እንጂ ያንተ እንዳልሆነ ሲገባህ ወደ ክፋት አትሄድበትም!!

አንተ የክርስቶስ እንጂ የራስህ እንዳልሆንክ ሲገባህ ለራስህ አትኖርም!!

አንተ ደግሞ የራስህ አይደለህም!!

የራስህ ሕይወት የለህም!!

የራስህ ኑሮ የለህም!!

የራስህ ሩጫ የለህም!!

አንተ ራስህ የለህም!!

የክርስቶስ ነህ!!..........በክርስቶስ ነህ!!

❝ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ #እኔም_አሁን_ሕያው_ሆኜ_አልኖርም #ክርስቶስ_ግን_በእኔ_ይኖራል፤ #አሁንም_በሥጋ_የምኖርበት_ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።❞
—ገላትያ 2: 20

❝በሕይወት ሆነን #ብንኖር_ለጌታ እንኖራለንና፥ #ብንሞትም_ለጌታ እንሞታለን። እንግዲህ በሕይወት ሆነን #ብንኖር ወይም #ብንሞት_የጌታ_ነን።❞
—ሮሜ 14: 8

sʜᴀʀᴇ◈ JOIN ◈sʜᴀʀᴇ

⇲⇲⇲⇲ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦
sebsibe official
"""“""""""""“""""""""""""""""“"""""""""
╔════ஜ۩۞۩ஜ════╗
@SalvationisonlyJesus
╚════ஜ۩۞۩ஜ════╝
⇘⇘⇘⇘⇘SHARE⇘⇘⇘⇘⇘
── ❖ ── ✦ ── ❖ ──