#መንፈስቅዱስ #ማነው ? (2) ~»>መንፈስ ቅዱስ አካል አለው ~»"መንፈስ" የሚለውን ቃል በእብራይስጥ "ሩህ" በግሪክ "ኑማ" ከሚነፍስ ንፋስ ጋር ያገናኘዋል ከዚህ የተነሳ መንፈስቅዱስን አካል የሌለው የሚነፍስ ኃይል አርጎ የመረዳት አዝማሚያዎች አሉ ~»>መንፈስቅዱስ እንደ አብ እና ወልድ ሁሉ አካል ያለው መሆኑን በቅዱሳን መፅሀፍት ተፅፎአል:: ~»በተደጋጋሚ "እኔ" አያለ በመናገሩ ምክንያት አካል ያለው መሆኑን ያሳያል ዮሐንስ 14 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁵-¹⁶ ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ ¹⁷ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ። “አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።” — ዮሐንስ 14፥26 ዮሐንስ 16 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹³ ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል። ¹⁴ እርሱ ያከብረኛል፥ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋልና። ~»>እየሱስ ክርስቶን በመተካት ሌላ አፅናኝ (ጳራቅሊጦስ) በመባሉ “.....ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤” — ዮሐንስ 14፥15-16 ~»>መንፈስ ቅዱስ እውቅት ስሜት ፈቃድ ያለው አምላክ ነዉ:: “አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።” — ዮሐንስ 14፥26 “ይህን ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድ ለእያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል።” — 1ኛ ቆሮንቶስ 12፥11 “ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።” — ኤፌሶን 4፥30 (እብ 3:7-9 ሐዋ 16:6) ተባርካችሁአል! 422 views𝒔𝒆𝒃𝒔𝒊𝒃𝒆_𝒐𝒇𝒇𝒊𝒄𝒊𝒂𝒍, 08:27