Get Mystery Box with random crypto!

በክርስቶስ ኢየሱስ አዳኝነት የሚያምን ሰው በሰው ፊት ስለ እርሱ ሊመሰክር ግድ ነው፡፡ እውነት እና | መንፈስ ቅዱስ 𝐇𝐎𝐋𝐘 𝐒𝐏𝐈𝐑𝐈𝐓

በክርስቶስ ኢየሱስ አዳኝነት የሚያምን ሰው በሰው ፊት ስለ እርሱ ሊመሰክር ግድ ነው፡፡ እውነት እናንተ የክርስቶስ ተከታይ ከሆናችሁ ስለ እርሱ በሰው ፊት ለመመስከር አታፍሩም፡፡

ኢየሱስ አንድ የገባላችሁ ቃል አለ! ዛሬ በሕይወት በምድር ሳላችሁ ስለ እርሱ በሰዎች ፊት ሳታፍሩ ከመሰከራችሁ በሚመጣው የትንሳኤ ዓለም ውስጥ እርሱ ስለ እናንተ በአብ ፊት፤ በመልአክት ፊት፤ በቅዱሳን ሁሉ ፊት ይመሰክርላችኃል፡፡

እናንተ ዛሬ በወደቀው ዓለም ውስጥ ስለ ኢየሱስ ስትመሰክሩ፤ ኢየሱስ በአዲሱ የትንሳኤ ዓለም ውስጥ ስለእናንተ ይመሰክራል፡፡ እናንተ በሰው ፊት ስለኢየሱስ ስትመሰክሩ፤ እርሱ በአባቱ ፊት ስለእናንተ ይመሰክራል፡፡ ሰው ስለ ሰው እንኳን በሰው ፊት ይመስክር የለ! ስለሞተላችሁ መመስከር ያሸማቅቃል እንዴ!

ስለየትኛው ክብር ብላችሁ ነው ስለ ኢየሱስ በጓደኞቻችሁ ፊት መመስከር ያሳፈራችሁ? ነው ወይስ እናንተ በኢየሱስ አፍራችሁ ነው? ብታውቁ እናንተ ስለ ኢየሱስ የምትመሰክሩት ኃጢአተኛ በሆነው አለምና ሰው ፊት ነው፡፡ ኢየሱስ ስለ እናንተ ሳያፍር የሚመሰክረው ጻዲቅ በሆነው አባቱና በመልአክት ፊት ነው፡፡

ዛሬ ላይ ስለ ኢየሱስ በየአደባባዩ ሲመሰክሩ የምታዩአቸው ተከፍሎላቸው አልያም ተገደው እንዳይመስላችሁ የወንጌል እውነት ገብቶአቸው የክርስቶስ ፍቅር ተረድተው ነው፡፡ ስለ ኢየሱስ የሚመሰክሩ በሰማይ ታላቅ ክብር ይጠብቃችኃል፡፡

"፤ ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።" [ ማቴ 10፥33 ]