2022-06-30 18:39:48
#የብዙዎች #ጥያቄ
#መንፈስቅዱስ #ማነዉ? (1)
~»>መንፈስቅዱስ ከስላሴ አካል አንዱ በመሆኑ:ሰው ሁሉ ከኃጢያት ለመዳን እየሱስ ክርስቶስ እንደሚያስፈልገው
እንዲገነዘብ ለማድረግ እየሰራ ነዉ
~»>በማንኛውም እየሱስ ክርስቶስን እንደ ግልአዳኙ ከተቀበለበት ቅፅበት ጀምሮ በማንኛውም ክርስትያን ውስጥ መኖር ይጀምራል:
~»>ቤተክርስቲያንን ለማነፅ ፀጋን ይሰጣል:
~»>የቃሉን እውነት ለመረዳት እና
~»>የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ
መንፈሳዊ ፍሬ ለማፍራት የሚያስችል ኃይል እንደሚሰጥ ቃሉ ያስተምራል
:-"የመንፈስቅዱስ አምላክነት -:"
~»>መንፈስቅዱስ አምላክ ነዉ
~»>መንፈስቅዱስአምላክ መሆኑን ቃሉ በዝርዝር ያስተምራል
#1ኛ መንፈስቅዱስ እግዚአብሔር ነዉ
~»>በሐዋ5 : 1-6 ሀናንያ እና ሰጴራ በቁጥር 3 ሲዋሹ ሐዋርያዉ ጴጥሮስ
"መንፈስቅዱስን ለምን ዋሸህ" ብሎ ከተናገረ በሁአላ
"እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አልዋሸህም"ብሎ "እግዚአብሔር" እና "መንፈስቅዱስ" የሚለውን ስም አቀያይሮ ሲናገር ይታያል::
~ይሄ ማለት መንፈስቅዱስ እግዚአብሔር እንደሆነ እና እግዚአብሔር መንፈስቅዱስ
እንደሆነ በደንብ ያሳያል::
#2ኛ ሐዋርያዉ ጴጥሮስ በ1ቆሮ 3:16-17 እና 6:19-20)
አማኞች የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ እንደሆኑ ሲፅፍ "የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ እንደሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖራችሁም አታውቁምን"? ቅዱስ ቤተ መቅደስ ናችሁ በማለት
"መንፈስቅዱስ" እና "እግዚአብሔርን" በማቀያየር ይናገራል::
~»>በመሆኑም መንፈስቅዱስ ብቻ ተብሎ ሳይሆን እግዚአብሔር ተብሎ መጠራቱ አምላክነቱን ያሳያል::
ተባርካችሁአል!
......ሼር አርጉ .......
472 views𝒔𝒆𝒃𝒔𝒊𝒃𝒆_𝒐𝒇𝒇𝒊𝒄𝒊𝒂𝒍, 15:39