Get Mystery Box with random crypto!

መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese

የቴሌግራም ቻናል አርማ rodas9 — መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese
የቴሌግራም ቻናል አርማ rodas9 — መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese
የሰርጥ አድራሻ: @rodas9
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 37.92K
የሰርጥ መግለጫ

ትክክለኛው ቻናሌ ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን ሳይንሳዊ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኔ አይደሉም

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 27

2022-09-10 19:45:14 ጳጉሜን 5 የ2014 ዓ.ም. በእጅጉ ከምወዳት የመጨረሻዋ የዓመቷ ሙሉ ጨረቃ ጋር ከፍ ካለው በእንጦጦ ፓርክ የተነሣኹት ፎቶ። ነገ መስከረም 1 በፀሐይ አቆጣጠር በዓመተ ዓለም 7015 ይኾናል።
በዓመተ ዓለም የጨረቃ አቆጣጠር ደግሞ 7745 ዓመት ከ8 ወር ከ8 ዕለት ይኾናል።
2015 ዓ.ም. ወደ አንድ አኃዝ ሲቀየር 2 + 0 + 1 + 5 = 8 ነው።
ጊዜው የ 8 ነውና እኔም በዐዲሱ ዓመት ከ8 ቁጥር ጋር የተያያዘ 888 የሚል ታላቅ መጽሐፍ ለአንባብያን አበቃለሁ።
በእግዚአብሔር ቸርነት በ2014 ዓ.ም. ያከናወንኳቸውን በዐጭሩ ስቃኛቸው፦
1 [በድርሰት]
24ኛ መጽሐፌ ማዛሮት ጽፌ ማስመረቄና ኹለት ታላላቅ የምርምር መጻሕፍት ጨርሼ ማስቀመጤ
2 [በማስተማር]
350 ተማሪዎችን ቀመረ ፊደል ማስተማሬ
3 [ሰማያዊ አካላትን (ጨረቃ፣ ከዋክብት፣ ፕላኔቶች) በማሳየት]
እጅግ ብዙ ሕፃናትን፣ ወጣቶችን፣ ታላላቅ ሰዎችን በምሽት ሰዓት ማሳየቴ
4 [በሚድያ]
ከዶክተር ጌትነት ፈለቀ ጋር ዐብረን በባላገሩ ቴሌቪዥን በአንድሮሜዳ መርሐ ግብር፣ በራሴ YouTube እና ፌስቡክ ዕውቀት ማስጨበጤ
5 [በመንፈሳዊ አገልግሎት]
3 በሀገር ቤት 3 በሰሜን አሜሪካ ብዙ ሺዎች የታደሙበት ክብረ ቅድስት ድንግል ማርያም አስመልክቶ ያስተማርኩበት ታላቅ ጉባኤ።
በሰሜን አሜሪካ የነበረውን የአቡነ ዘርዐ ቡሩክ የብራና ገድል መጽሐፍ በዚያ ካሉ ኀላፊዎች ጋር በመነጋገር ዲጂታል ኮፒው ለገዳሙ እንዲላክ በማድረግና ሌሎች ብዙዎች የበረከት ሥራዎች ላይ በመሳተፍ ይኽነን ዓመት ጨርሻለሁ።

በምድር ላይ 79 ዓመት ብንኖር 26 ዓመት ሙሉ በእንቅልፍ እናሳልፋለን። ለመተኛት በመሞከር 7 ዓመታትን ስንፈጅ በአጠቃላይ በአልጋ ላይ የምናሳልፈው 33 ዓመታት ወይም 12,045 ቀናት ነው። ቀሪው 46 ዓመት ብቻ ነውና ዕድሜያችንን በአግባቡ መጠቀም ይገባል።

ብራድ ፔይስሌይ የተባለ ጸሐፊ ስለ ዐዲሱ ዓመት ሲናገር "Tomorrow, is the first blank page of a 365 page book. Write a good one" (ነገ (ዐዲሱ ዓመት) 365 ገጾችን የያዘ የመጀመሪያው ባዶ ገጽ ነው። መልካሙን ጻፍበት) ይላል

በመኾኑም በ2015 ዓ.ም. እንደ አምላክ ፈቃድ ምን ብታደርጉበት ደስ ይላችኋል? አስተያየታችኹን ወይም የመጨረሻዋን የዛሬዋ ጨረቃ ፎቶ አጋሩን።
888
4.8K viewsedited  16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 19:45:05
4.4K views16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 13:40:43 ወዳጆቼ ዛሬ ጳጉሜን 5 የዓመቷ የመጨረሻዋ ሙሉ ጨረቃ የምትወጣበት በመኾኑ የጨረቃ ወዳጆች ምሽታችኹ ያማረ ይኹን።
መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
5.9K views10:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-09 11:53:06 Watch "የግእዝ ቁጥሯ ኮከብ የ6 ዓመቷ የአንድሮሜዳ ሕፃን" on YouTube


7.3K views08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 02:26:14 Watch "አስደሳች የከዋክብት ምልከታ ምሽት በእንጦጦ ፓርክ ፌታፊዚክስ በሕፃናት" on YouTube


8.6K views23:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 02:21:35 Watch "ጳጉሜን 3 የሰማይ መከፈት የቀመር ምስጢር" on YouTube


7.9K views23:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 21:47:08 ውድ አንድሮሜዳውያን ከጳጉሜ 1 - 5 ድረስ ሰማይን ከዋክብትን ጨረቃን ፕላኔቶችን በቴሌስኮፕ የመመልከቱ ኤቨንት ነገ ከ8 ሰዓት ጀምሮ በእንጦጦ ፓርክ ይከናወናል። ስለዚህ ከዛ ሰዓት ጀምሮ ቦታው ክፍት ይኾናል።
ደመና ካልሸፈነና ጥርት ያለ ሰማይ ከኾነ ከዋክብት የመመልከቻ ሰዓት ግን ጨለምለም እንዳለ ከ12:30 ጀምሮ ይከናወናል።
ወደ እንጦጦ ፓርክ የምትገቡበት በር በሱሉልታ በር በኩል ነው።
ሰብሰብ ብላችሁ ከኾነ ሚኒባስ ይዛችሁ ብትመጡ የተሻለ ነው።
የኢንትራንስ ክፍያ በጳጉሜ ኤቨንት በሩ ላይ 50 ብር
መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
1.6K viewsedited  18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 11:12:00 Watch "ከጳጉሜ 1 ጀምሮ ከዋክብትን ፕላኔቶችን የማየት ምሽት በእንጦጦ ፓርክ" on YouTube


2.9K views08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 21:00:50 Watch "ጳጉሜ 7 መቼ ነው? ጨለማውና ምልክቱ ምን ይኾን? መቼ ይታያል?" on YouTube


2.9K views18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 19:34:59 Watch "አስደናቂው የኢትዮጵያ ሕፃናት ዕውቀት ታየ፤ ዝቅ ብለው እግር አጠቡ" on YouTube


5.2K views16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ