Get Mystery Box with random crypto!

ጳጉሜን 5 የ2014 ዓ.ም. በእጅጉ ከምወዳት የመጨረሻዋ የዓመቷ ሙሉ ጨረቃ ጋር ከፍ ካለው በእንጦ | መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese

ጳጉሜን 5 የ2014 ዓ.ም. በእጅጉ ከምወዳት የመጨረሻዋ የዓመቷ ሙሉ ጨረቃ ጋር ከፍ ካለው በእንጦጦ ፓርክ የተነሣኹት ፎቶ። ነገ መስከረም 1 በፀሐይ አቆጣጠር በዓመተ ዓለም 7015 ይኾናል።
በዓመተ ዓለም የጨረቃ አቆጣጠር ደግሞ 7745 ዓመት ከ8 ወር ከ8 ዕለት ይኾናል።
2015 ዓ.ም. ወደ አንድ አኃዝ ሲቀየር 2 + 0 + 1 + 5 = 8 ነው።
ጊዜው የ 8 ነውና እኔም በዐዲሱ ዓመት ከ8 ቁጥር ጋር የተያያዘ 888 የሚል ታላቅ መጽሐፍ ለአንባብያን አበቃለሁ።
በእግዚአብሔር ቸርነት በ2014 ዓ.ም. ያከናወንኳቸውን በዐጭሩ ስቃኛቸው፦
1 [በድርሰት]
24ኛ መጽሐፌ ማዛሮት ጽፌ ማስመረቄና ኹለት ታላላቅ የምርምር መጻሕፍት ጨርሼ ማስቀመጤ
2 [በማስተማር]
350 ተማሪዎችን ቀመረ ፊደል ማስተማሬ
3 [ሰማያዊ አካላትን (ጨረቃ፣ ከዋክብት፣ ፕላኔቶች) በማሳየት]
እጅግ ብዙ ሕፃናትን፣ ወጣቶችን፣ ታላላቅ ሰዎችን በምሽት ሰዓት ማሳየቴ
4 [በሚድያ]
ከዶክተር ጌትነት ፈለቀ ጋር ዐብረን በባላገሩ ቴሌቪዥን በአንድሮሜዳ መርሐ ግብር፣ በራሴ YouTube እና ፌስቡክ ዕውቀት ማስጨበጤ
5 [በመንፈሳዊ አገልግሎት]
3 በሀገር ቤት 3 በሰሜን አሜሪካ ብዙ ሺዎች የታደሙበት ክብረ ቅድስት ድንግል ማርያም አስመልክቶ ያስተማርኩበት ታላቅ ጉባኤ።
በሰሜን አሜሪካ የነበረውን የአቡነ ዘርዐ ቡሩክ የብራና ገድል መጽሐፍ በዚያ ካሉ ኀላፊዎች ጋር በመነጋገር ዲጂታል ኮፒው ለገዳሙ እንዲላክ በማድረግና ሌሎች ብዙዎች የበረከት ሥራዎች ላይ በመሳተፍ ይኽነን ዓመት ጨርሻለሁ።

በምድር ላይ 79 ዓመት ብንኖር 26 ዓመት ሙሉ በእንቅልፍ እናሳልፋለን። ለመተኛት በመሞከር 7 ዓመታትን ስንፈጅ በአጠቃላይ በአልጋ ላይ የምናሳልፈው 33 ዓመታት ወይም 12,045 ቀናት ነው። ቀሪው 46 ዓመት ብቻ ነውና ዕድሜያችንን በአግባቡ መጠቀም ይገባል።

ብራድ ፔይስሌይ የተባለ ጸሐፊ ስለ ዐዲሱ ዓመት ሲናገር "Tomorrow, is the first blank page of a 365 page book. Write a good one" (ነገ (ዐዲሱ ዓመት) 365 ገጾችን የያዘ የመጀመሪያው ባዶ ገጽ ነው። መልካሙን ጻፍበት) ይላል

በመኾኑም በ2015 ዓ.ም. እንደ አምላክ ፈቃድ ምን ብታደርጉበት ደስ ይላችኋል? አስተያየታችኹን ወይም የመጨረሻዋን የዛሬዋ ጨረቃ ፎቶ አጋሩን።
888