Get Mystery Box with random crypto!

ሀበሻዊ ጥበባት

የቴሌግራም ቻናል አርማ habeshistanyesetlij — ሀበሻዊ ጥበባት
የቴሌግራም ቻናል አርማ habeshistanyesetlij — ሀበሻዊ ጥበባት
የሰርጥ አድራሻ: @habeshistanyesetlij
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 204
የሰርጥ መግለጫ

እኔ የምፈራው ሞት ሞትን ቀድሞ መሞት!!!

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-23 11:28:20 ካሊድ (ሀበሽስታን)


አንድ አንድ ሀሳቦቸ 4


አለ ደግሞ አንድ አንድ ጊዜ እንዲህ ያለ ስሜት… ……የማያውቁትን የሚያስናፍቅ……… የሚያውቁትን የሚያጥላላ……… የማያውቋትን አለም መናፈቅ……… የሚያውቁትን አለም የሚያስቀፍፍ……… ዝም ብሎ ብረር ብረር የሚያሰኝ……… እስኪ ጩህ ይውጣልህ የሚያሰኝ……… ሳቅ የቀላቀለ ሳግ የሚ ያፍንበት ………ሳቁም ሳጉም እኔ ቀድሜ ልውጣ ግብ ግብ የሚገጥሙበት ………… በደስታ ዘፈን እሪ ብሎ የሚያስለቅስ የመከፋት ጥንስስ እንደ ሽል  አንጀት ውስጥ የሚያፈራግጥ  ………በሀዘን ደረት በሚያስደቃ ሁኔታ እጅን እንደ መቀነት ሆድ ላይ ጐንጉና በሳቅ የሚያንተከትክ………የተምታታ………የሚያውቋትን ቀርቶ የማያውቋትን የፍቅር አጋር በሩቅ ተስፋ ፀጉር ስትዳብስ እንደ ቅዠት አድርጐ የሚያሳልም………እየሳቁ ያሉትን ሳቅ ንቆ አዲስ ሳቅ መመኘት……… የሚያለቅሱበት ሰበብ ሳያልቅ የሚያለቅሱት የእንባ ዘለላ ሳይነጥፍ ሌላ የእንባ ማፍለቂያ ሰበብ መሻት………የሚናፍቁት ነገር ማጣት………የሚያዝኑለት ሰው መፈለግ………የማስቀው የሚስቅልኝን ሰው ማሰስ…………ወይም ደግሞ የምር ከአንጀትን ቅጥል አድርጐ የሚያስለቅስ ሰበብ ማነፍነፍ………… ጮሆ የማይወጣ ጋኔልን መለማመጥ………የትኛው የሰውነት ክፍል እንደሆነ ሳይገባ የመቃጠል ስሜት መሰማት………የመንተክተክ……አንዳች የማጥወልወል………የትኛው ውስጥ አነንደሆነ ሳይታወቅ ውስጥ ላይ የማይፈታ ግማድ እንደተተበተበ መሰማት………ሩቅ መመኘት………ከጥበቱ ለመውጣት መፍጨርጨር………እንደገና ወደ ጥበቱ መሸንቆር………ሩቁን በሽንቁር ማጮለቅ………ያሉበትን ብርሀን ከጨለማ ለይቶ አለማስተዋል………ደግሞ የሚጣሉትን ሰው መፈለግ………የሳቀውን ለምን አባህ ትስቃለህ ብሎ መጣላት ማሰኘት………አይዞህ ባዮን ለመደቆስ አይበሉባን ማመቻቸት………መሻትን ማወቅ መሻት የሚፈልጉትን ማጣት ………የፈለጉት ሲሆን የማይፈለገውን ለማድረግ መውተርተር………… የናፈቁትን ሲያገኙ የማያውቁትን መናፈቅ………… ሩቅ መንጐድ ያለፉትን ፈተና እንደገና ለመፈተን መሰናዳት…………የሚያውቁትን የት አባህ ብሎ የማያውቁት ላይ ለመጠምጠም ልብን እና እጅን እንደ አክናፍ መዘርጋት………የሚስቅ ሰው ምፅ አስብሎ የሚያሳዝነን………የሚያለቅስ ሰው አፍን እስክናፍን ከሳቅ የሚያስተናንቀን…………የተወናበደ ውል አልባ ለራስም ስራ ፈት ሀሳብ የሚያሰኝ ስሜት………ምን አይነት ስሜት ነው? ከምንድን ነው የሚመደብ???



@Habeshistan
138 views08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 20:10:42 ካሊድ (ሀበሽስታን)

አንድ አንድ ሀሳቦች 3

አለ ደግሞ እንዲህ ያለ ስሜት……… ይይዙት ይጨብጡት የሚጠፋበት………የምድሩንም የሰማዩንም ሸክ ውስጥ የሚዶል………ኤዲያ አሰኝቶ ሆ ሆ ኸረ ተመስገን ነው የሚያስብል………ቅዝዝ የሚያደርግ………እንደገና ስሜትን አንተክትኮ የሚያገነፍል……… ልብ ጦል የሚያደርግ………አዕምሮን የሚያቦዝዝ………አላስብም የሚያሰኝ እንደገና አላስብምን አብስሎ የሚያሳስብ………ውስጥን የሚያላምጥ………አይነግሩት ስውር ቅኔ አይነገር… ……አያሳዮት አይገለጥ ድብቅ ስውር………… ሲያብሰከስክ ፋታ የማይሰጥ…………ወዲያ ሲሉት ወዲህ………ሂድ ሲሉት ከች………ጠፋ ሲሉት ግርሻት…………ሆነ ሲሉት ካድ………ቀረ ሲሉት ማቆጥቆጥ…………ሲጨብጡት ብናኝ………እንዲህ ያለ ክፉ ስሜት… ……ተውኩህ በቃኸኝ የምን ጭንቀት ሲባል ኤዲያ የምን መድከም ነው ተስፋ ቆራጭ የጌታውን ቅዋ ያልተረዳ ነው። ብሎ ተስፋን በጠፍር አንቀልባ አሸካሚ…………ተስፋ አለኝ ተስፋ አልቆርጥም ትልቅ ጌታ ያለው ትንሽ አይመኝም የተባለ ጊዜ ኡ ኡቴ አልቀረብህም የሚጨበጥ ነገር ሳይኖር ተስፋን ሸክፎ ተሸክሞ የማይመጣን መጠበቅ ምን ይሉታል ባይ…………ትክክሉ ጠፍቶ የልክ ዳና ተሰውሮ ይሄ ነው ልክ የለም ይሄ ነው እያሉ የመቃበዝ ህይወት……የተበተነውን መሰብሰብ እንደገና መበተን………ዝም አይሉት የእግር እሳት የሚያቁነጠንጥ………አይተነፈስ የገደል ማሚቶ ዞሮ ለለፋፊው…………ማን ይሆን ይህንን ቅኔ ፈቺ? ማን ይሆን ይህን ውል አልባ መብሰክሰክ አስካኝ?



@Habeshistan
149 views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-11 18:39:51 እንሂድ ያልኩት ወደሚቆረቆርለት አደራዬ ነው ወደሚለው ሰላቱ አትጨቅጭቀኝ ያለው እሱ!  እንዴት ነው በአንድ ጊዜ ሁለት ነገር የሚኮነው? ባለአደራ እንደዚህ ነው እንዴ? ባለ አደራ አደራውን አስበልቶ በል አደራህን ተው ቢሉት በተበላ አደራ እንዴት እንደዚህ ትለኛለህ እንዴት ይላል?

ንፁህ የኩሬን ውሀ አደራ ብለውት እንደሄዱት የኩሬዋ ባለአደራ መሰለኝ ንፁኋን ኩሬ አደራ ጠባቂው ሳይንከባከባት የሚሞላትም ፈጣሪዋ ሆኖ እሱ ቅንጣት ታህል ሳይጠብቃት ያም እየመጣ ሲያደፈርሳት ሲያቆሽሿት  ኖሮ ኖሮ አንድ ቀን አንድ ገዢ ብቅ ብሎ ኩሬህን በሴኩላር ይሉት አፈር ደፍኜ ፎቅ ልሰራ ነው እና ከዚሀ በኋላ እዚህ መጠበቅ አትችልም ቢለው እንዴት ነው ቀኝ አዝማቼ አካኪ ዘራፍ ያለው ባለ አደራውስ ጉዱን ያየ እንደሁ እንዴት ያዝን ያችን የቀልቡን መርጊያ ኩሬ ማቆሸሹን ዝም ቢል መድረቋንም ሞይውን ተማምኖ ቢታገስ ለማዳፈን እንዳሰፈሰፉ ቢያይ……………ማን ነው ቀኝ አዝማቼን ያናደደብኝ ሰላትህን ተው ያለው ማን ይሆን? ባለ ሴኩላሩ ነው ወይስ ውስጥ እራሱ?

መልክህ እኮ ያበደ ነው! ቆንጆ ነህ! ወንዳ ወንድ! ምንም ብታደርግ ያምርብሀል! ደግሞ በዚህ ምላስህ እትት ብትልበት… በዚህ መልክህ ብትጠቀም… ፈጂ ነበር የምትሆነው። ብለው የሀሳብ ጥንስስ ሲጠነስሱበት ለመጠንሰሻነት ሲስማማ እና አደራውን በገዛ እጁ ሲተዋት ምነው እንደዚህ አልተብሰከሰከ?

በኋላ እንሰግዳለን ይሄን moment የትም አናገኘውም ብለው በሞመንት ሲያታልሉትና አደራውን በሞመንት አጣብቀው ሲያጐርሱት ምነዋ አደራው አላነቀው? የዛኔ የበላው አደራ ዛሬ ግድ የለህም ከተውክ አይቀር ትምህርት ቤትም ተዋት ሲባል የአባቶቼ አጥንት እሾህ ሆኖ ይውጋኝ አለሳ ማን ነው ወንድሜን ያስቆጣው?


ይህንን እያምሰለሰልኩ በምን ሰዐት መስጅድ ገብቼ በምን ሰዐት ሰላት ጀምሬ ስንተኛው ረከዐ ላይ እንደሆንኩም ማስታወስ ተሳነኝ ብዙም ሳንቆይ አሰላመትን ።

ከአዝማቾቼ በላይ ተናድጄ ከመስጅድ ወጣሁ ቆይ የእኔ መምጣት ከቀኝ አዝማቼ አለመምጣት በምን በለጠ የእርሱ መቅረት አይሻልም ወይ? ማን ፈራጅ አደረገኝ የራሴን ጉድፍ ሳላጠራ ገብቶ ያልገባ ጠርቶ ያደፈ ሸቀን የወረረው ቀልብ ይዤ ለመፍረድስ ይሁን እንዴት ባለአደራ ነኝ ብዬ አደራ ልወጣ እላለሁ በዚህ ቀልብ ነው እንዴ አደራዬን እንድወጣ የተሰጠኘ?


በተንሸራተተ ሂጃብ ተጀቡኖ በተንሸራተተ ልብ ተወሽቆ በሸቀነ እና ባዳፋ ቀልብ ተሽሞንሙኖ ወደሌላ አካል መጮህ ምን የሚሉት ብሂል ነው? ቀድሞ ውስጥ ላይ መጮህ ነው ቀድሞ እሪታን ዋይታን ከራስ መጀመር ነው ዋይ ቢሉ ዋይታ የገደል ማሚቶ እንዳይሆን ቀድሞ ነው ለዋይታ ቦታ መምረጥ ዋይታው ውስጣችን ላይ ቢጀምር የዛኔ በዝምታም ቅጣት ባዘነብን ነበር!!!

አሁንም ጀሰዴ እየተነዳ ቤቱ ለመድረስ በየት በየት እንደመጣ ምን ያህል ጊዜም እንደፈጀበት አላወቅኩም ብቻ በሩን ከፍቼ ስገባ ቀኝ አዝማቼም ግራ አዝማቼም አሰላለፋቸውን እና ሁኔታቸውን እንደጠበቁ ተቀምጠዋል። በማን በምን እንደተቆጣ ባላውቅም በተቆጣ አንደበት አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ? አልኩ በመሰላቸት እሺም እምቢም ሳይሉ ለአፍታ አይናቸውን ገርበብ አድርገው አስተዋሉኝ…

ቆይ ቆይ የትኛውን ሰላት ነው አደራ የተሰጠን? የትኛውንስ ሰላት ነው የተከለከላችሁት? ማንስ ነው የከለከላችሁ? አንቺስ የትኛውን ሂጃብሽን ነው አውልቂ ያሉሽ ለይተሽዋል? ለምንስ ነው አውልቂ ያሉሽ? ከምንስ ተነስተው እንደዚሀ አሉሸ? ብዬ ስጨርስ ሁለቱም ተያይተው ምፅ ብለው አዝነውልኝ ይሁን ምን ባላውቅም አንገታቸውን ግራ እና ቀኝ አወዛውዘው ወደ ስልክ ተመስጧቸው ተመለሱ።


ጫማዬን አውልቄ ልገባ ሳኮበኩብ የግራ አዝማቼን ድምፅ ሰማሁ እህቴ ሂጃብሽ ውበትሽ እያለች ድምፇን ወደማላውቃቸው ሰዎች እየቀረፀች መሆኑ ገባኝ ። አስከትሎም ቀኝ አዝማቼ ቀጠለ ወንድሜ በሰላት ቀልድ የለም አደራችን ናት አለ። ውስጠቴም እንደዚህ አለኝ አይ ሀበሽ አንተም እኮ ሰገድኩ ብለህ ሞተሀል አልቀረብህም ብሎ ተሳለቀብኝ።

ወይ አደራ ወይ ምክነት የተንሸራተተ ልብ አንግበን በተንሸራተተ ሂጃብ ጉዞ ወዴት ይሆን?

የትኛውን ሰላት ይሆን አደራ የተባልነው? የትኛውንስ ይሆን የከለከሉን? ለምንስ ይሆን የከለከሉን?



@Habeshistan
256 views15:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-11 18:39:50 ካሊድ (ሀበሽስታን)

አንድ አንድ ሀሳቦች 2

……………ጉድ ነው አልኩ ከማነበው መፅሀፍ ላይ እንደ መባነን ብዬ ከወሰደኝ የሀሳብ ማዕበል ተፍጨርጭሬ ለመንቃት እየሞከርኩ አይኔን ሞዠቅ አድርጌ ዙሪያ ገባውን ቃኘት አደረኩ ቀና ብዬ ግድግዳ ላይ ተሰቅሎ ዝንት አለም ሰዐታትን እየቆጠረ ለአመታት ሲያስረክብ እዚህ የደረሰውን የግድግዳ ሰዐት አጨንቁሬ ተመለከትኩት ችግሩ ከአይኔ ይሁን ወይ ሰዐቱ በስተርጅና መሮጥ ጀምሮ ወይ እርጅናው ይብሱኑ ተጫጭኖት መርሳት ጀምሮ እንደቆመ ቀርቶ ባላውቅም ከቀኑ ስድስት ሰዐት ከአስር ደቂቃ ይላል።

መፅሀፌን ያቆምኩበትን ገፅ አይቼ ከከደንኩ በኋላ ጋደም ካልኩበት ተነስቼ ባለማመን ደጋግሜ ያንን አሮጌ ሰዐት አየሁት ያው ነው እየጨመረ ይሄዳል ደቂቃው ይገርማል እርጅና የማይጫጫነው ፍጡር በቃኝ ልረፍ የማይባልበት ህይወት የሰዐት ህይወት ።

እሁድን ሳላጣጥማት እንዴት ነው ሰዐቱ እንደዚህ የሚነጉደው? ብዬ እራሴ ጋር እያጉረመረምኩ የያዝኩትን መፅሀፍ ቦታው ላይ መልሼ ሽቅብ እየተንጠራራሁ ወደውጭ ወጣሁ ። የፀሀይዋን ነፀብራቅ አይኔ እሰኪላመደው ትንሽ ከተጨናበስኩ በኋላ የግቢውን ግራ ቀኝ ስመለከት የግቢው ግራም ቀኝም ላይ ሰው ተቀምጧል

የግቢው ቀኝ እረድፍ ቀኝ አዝማች እንደማለት ነው አጭር ፀጉሩን እንደ ነጠላ እየቋጨ አንዴ ፈገግ አንዴ ኮስተር እንደገና የያዘውን ስልክ በሁለት እጁ ጨበጥ ለቀቅ ማድረጉን የተያያዘው ዘመዴ ነው ዝምድናው ማን ማንን ቢወልድ እንደሆነ ባላውቅም ዘመድህ ነው አሉኝ ዘመዴ ነህ ብዬ ተቀበልኩት። እንኳንስ ዘመድን ወልደው የለም የኔ አይደለህም ብለው ያላመቱንስ ልጅ ነገሩ ተፋፍሞ ቁርጥ ሲመጣ የአብራኬ ክፋይ ብለው ያመኑ ስንቶቹ ናቸው

የግቢው ግራ እረድፍ ግራ አዝማች ደግሞ የለመደባት ማስቲካ ማኘክ ስለቀረባት ወይም ፆሙ ገና በዚህ ሰዐት አድክሟት ጨጓራዋ ምን ኩነሻል ሴትዮ ብይ እንጅ በአማኑ ቀን ክፉ አስለምደሽኝ እርምሽን ብትፆሚ ተላጥኩ እኮ እያላት በየሰከንዱ የምታዛጋዋ ያመንኳት ዘመዴ ልክ እንደ ቀኝ አዝማቹ እሷም ስልኳን እየነካካች ፈገግ ኮስተር ትላለች።

እህ… እህ አልኩ ተቀላቅያለሁ ለማለት ቀና ያለ የለም እህ ለውጥ የለውም ብዬ የጌታየን ሰላምታ ሰጠሁ በቸልታ መለሱልኝ ይሄንንስ ማን አየበት ብዬ በሆነ ማንቆርቆሪያ ነገር ውሀ ይዤ ከፊታቸው ተቀመጥኩ ፊት አውራሪ እንደማለት ነው።

ምንድን ነው ሰሞኑን እንደዚህ እልል ሳይባል ከስልካቹ ጋር ያጋባችሁ አልኩ በየተራ እየተመለከትኩ ሁለቱንም እ…እ…እ… አለ ቀኝ አዝማች እ…እ…እ… ብሎ ዝም አለ ምን ታልጐመጉማለህ አትናገርም እንዴ አልኩት ቆጣ ብዬ ግን ምን አስቆጣኝ? ስላልመለሰልኝ ነው ወይስ ችላ ማለቱ ነው?

እ…እ…እ… ባክህ ሰላት ተከለከለ ። ማለት አለ አስሬ ከንፈሩን እየላሰ እና በአንድ እጁ አጭር ፀጉሩን እንደ ነጠላ እየቋጨ ማለት ትምሮ ቤት አትሰግዱም መውጣትም አይቻልም ውስጥም መስገድ አይቻልም አሉ አለኝ። እነማን ናቸው አትሰግዱም ያሉ? አልኩት የለም ሳይመልስልኝ ወደ ስልኩ ተመልሶ ገብቷል።

አንቺሰ ግራ አዝማች ምንድን ነው ስልክሽ ጋር ያጣበቀሸ አልኳት እ…እ…እ… አለች ወየው ጉዴ ቆይ ይሄ እ…እ…እ… መንደርደሪያ ነው ወይስ ፈርድ ሆነ ከንግግር በፊት? አልኩ ቆጣ ብዬ ምን መሰለህ ሀበሽ አለች እ… አልኳት ወይኔ እኔም በአንዴ ተጋባብኝ ይሄ እ ለነገሩ ቢጋባብኝ ምን ይገርማል እ እታችን እየተጋባብን አደል ከእርምጃ ይልቅ እያቃሰትን የምንኖር ለመናገር ቅስቻ ለመሄድ ቅስቻ አቃሳች ሂወት።

የመጀመሪያው ምን መሰለህ የሆነ ያልጨረሰችውን ወሬ እስክትጨርስ ቆይ ጠብቀኝ አይነት ስለነበር ምን መሰለህ ሀበሽ አለች ደግማ ትኩረቷን ለመሰብሰብ እየተጣጣረች ሂጃባችሁን አውልቁ አሉን አለች።እነማን ናቸው ሂጃብ አውልቁ ያሉ አልኳት እሷም የለችም ወደማላውቀው አለም በስልኳ ተሳፍራ በራለቸ።

ነገሩ ቢገባኝም ከነሱ አፍ ለመስማት የፈለኩትን ጉዳይ ሳልሰማ ከቅርብ እርቀት የሚገኝ መስጂድ አዛን ያስተጋባው…………………

………………አዛኑ አልቆ ትንሽ ካምሰለሰልኩ በኋላ ባቀረብኩት ውሀ ኡዱዕ አድርጌ ጨራረስኩ በል ተነስ ቀኝ አዝማች እንስገድ አልኩ አንቺም ተነሺ አልኳት በተቀመጠችበት ከላይ እስከታች እየገረመምኳት የለበሰችው ጥቁር ጉርድ ቀሚስ ከሰውነቷ ተጣብቆ እና ጉልበቷን ልከልለው አልከልለው እያለ መወዛገቡን ከላይ ያደረገችው ወይ በእርሷ አስተሳሰብ አውልቂ የተባለችው ሂጃብ ተንሸራቶ ለትልቁ ፀጉር ማስያዣዋ እንጂ አላማው ለፀጉሯ እንዳልሆነ ይመስል ፀጉር ማስያዣዋን ይዞ ተንጠልጥሎ ልውደቅ አልውደቅ ይላል።

ከእርሷ መለስ ብዬ ተነስ እንጂ እንሂድ አልኩት እጁን እንደማወናጨፍ ብሎ ባክህ ሂድ ለራሴ ተናድጃለሁ አንተ ደግሞ ትጨቃጨቀኛለህ ብሎኝ ፀጉሩን እያሻሸ አቀረቀረ።

ብዙም ሳይገርመኝ ለመሄደ በሩን ከከፈትኩ በኋላ መለስ ብዬ ቅድም እኮ ጠይቄህ አልመለስክልኝም እና ማን ነው ሰላቱን የከለከለው አልከኝ ? አልኩት ምንም ምላሽ አልሰጠኝም አንቺስ ግራ አዝማች አልኳት ዝም አለች ቄሱም ዝም መፅሀፉም ዝም ይሄ ይሆን እንዴ? እያልኩ ወጥቼ ወደመስጅድ በቀስታ መራመድ ጀመርኩ


ግን ግን ማን ነው ሰላት ከልካዮ? ለምንስ ከለከለ?
እሺ ማነው ሂጃብ አስወላቂው? ለምንሰ አውልቁ አለ? ሂጃብሰ ምንድን ነው?

የአዕምሮዬ ድርብርብ ድሪቶ ጥያቄዎቸ ናቸው ለመመለስ አዕምሮዬ ቢዘጋጅም መልሱ የተገለጠ መፅሀፍ ቢሆንም ሙግት ውስጥ ተደነጐረ።

ቀደም ብዬ ከቤት ስወጣ ያጤንኳት ግራ አዝማች ዘመዴ በአዕምሮዬ ተመላለሰች አለባበሷ እና ስነ ምግባሯ በእዝነ ህሊናዬ ተንሸራሸረ

ቀድሞ ለተንሸራተተ ሂጃብ ሂጃብሽን አውልቂ መባል ቆይ ለምንድን ነው የገረማት? መጀመሪያ ከፍ አድርገው ሲያስለብሷት ቀደም ብለው ፀጉርሽ እኮ ሲያምር ብለው በስሱ ሲያስከፍቷት ቀጥሎ አረ አውልቂው እንደሚመጣ አላስተዋለችውም ነበር ነው? ፈልጋ ለማውለቅ እየዳዳት ያለውን ሂጃብ ማን ይሆን ላግዝሽ እንተጋገዝና አውልቂው ብሎ ያናደዳት? ማን ነው እህቴን የተዳፈራት ውስጧ እራሷ ናት ወይስ አውልቂው ባዮ ነው? አውልቂው ባዮ ምን አጠፋ የወለቀ ነገር ወይ ጌጥ ወይ መለያ አይሆንም ለሀገርም ገፅታ ለሴኩላሩም ብዙም ምቾት አይሰጥም ብሎ በለሆሳስ ስለተናገረ ነው።

ልክ ነው እኮ ግንጥል ጌጥ ሆኗል  ሂጃብ! ማውለቅ ነበር ተብሎ የሚደረግ ። ታዲያ ማውለቁን ላግዝ ባለ እንዴት ተናደደችበት? ማን ነው እህቴን ያስከፋት? ሂጃብሽን አውልቂ ብሎ? ቅርፅሽ እኮ የሰጠ ነው ፓ ብለው አድንቀው በገዛ ልብሷ በገዛ ፈቃዷ ሲያጣብቋት መርሀባ ብላ ተጣብቃ ዛሬ ደግሞ አጣባቂው አዝኖላት ብታወልቂው እኮ እንደዚህ ላስጨነቀሽ ብሎ ባዘነላት ለምንድን ነው ያዘነችው? ማን ነው እህቴን ያስከፋብኝ? ብዙም ለነገሮች አትጨናነቂ እራስሽን ማስጨነቅ ጥሩ አይደለም ደግሞ እንደዚህ ቆንጆ ሆነሽ የምን መሸማቀቅ ለቀቅ በይ አይን አፋርነት ባክሽ የፋራ ነው ብለው አደቧን ከላዯ ላይ አጣጥበው እጣቢውን አርቀው ደፍተው ጥለዋት ከሄዱ በኋላ ቢበርዳት ማን ነው ተጠያቂው አጣቢው ነው? ታጣቢው? ማን ነው እህቴን ግራ አዝማቼን ያናደደብኝ?


ቀኝ አዝማች ዘመዴ ግራ አዝማቿን ዘመዴን በግድ ከአዕምሮዬ የሀሳብ ፈለግ በጥሶ እራሱን የሀሳብ ፈለግ አድርጐ ተካ 
186 views15:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-30 23:19:23 ካሊድ (ሀበሽስታን)

አንድ አንድ ሀሳቦች 1

ሰርከም ሰርከም እያልኩ ከላይ  የት አባህ ማን በዚህ ሰዐት ውጣ አለህ እያለች መዐቱን ከምታፈላዋ ፀሀይ ሽሽት አንድ እጄን እንደ አቅጣጫ ጠቋሚ ከግንባሬ ትይዮ ቀስሬ…………  ከታች ይሄን የጥቁር አስፖልት ወበቅ ለመዝለል በሚመስል ሳልረግጥ እየተራመድኩ ……ከጐን እና ከጐን መኪና ማየት ተስኖኝ መራመድ የተሳነው ወይም መኖር የተሳነው ከመሆን ለጥቂት አፈተለኩ።

ስለ ፀሀይዋ ሲነሳ አጃዔብ ያሰኛል ወደ ማደሪያዋ ገብታ እንኳን (ግን የት ነው የምታድር ስታድርም ሌላ የምታቃጥለው አዳሪ ወይም ዋይ ይኖር ይሆን? በማታ እንኳን ስለሷ ወግ ከተወጋ ላብ ያጠምቀኛል(በአዲስ አበባ ፀሀይ የማያልበኝ ምላሴን ብቻ እንደሆነ በቅርብ ያጠናቀርኩት ጥናቴ ይናገራል) እንደ ቀኑ የእጅህን መዳፍ ተከልል ተከለል ይለኛል።

አሁን አሁንማ ልምድ ሆኖብኝ ብብቱን እንደተወጋ አምሽቶ ገቢ እጄን ሰቅዬ መዞር ጀምሪያለሁ በቅርብ እንደውም ኮፍያ አድርጌም ከልምዴ የተነሳ መዳፌን ከልዬ ስሄድ አንድ ወታደር ሲቪል ለባሽ አለቃው ጋር በምን እንደተመሳሰልኩበት እንጃለቱን ሰላምታ ሰጥቶኝ ሄደ ፀሀይ አስከበረችኝ።


ከሁሉም ተርፌ እንደገና "ከሁሉም ለመትረፍ" አዛኑን ወደ አስተጋባው የአቅራቢያ መስጂድ እየተጣደፍኩ ገባሁ ። ጥድፊያየን ላየ የጀነት መግቢያዋን በ250 አለቀች ይላል በ250  እያለ የተጣራ እንጂ የተለመደው አዛን የተደረገ አይመስልም።

እውነት ግን ከአዛኑ ጋር የጀነቷን መግቢያ በ250 በ250 ይላል አለቀች አለቀች ቢባል ተጣድፈን እንገዛ ይሆን ? ወይስ እንደ አንዳንድ መዝለያ ፕሮግራም የለም የለም በአቅራቢያችን ባለ ባንክ እንድናገኝ እንድንገዛ ይመቻችልን እንል ይሆን?

ጫማዬን ለማውለቅ ዝቅ ብዬ ስመለከታት ምነው ምነው ሀበሽ? መርገጡንስ እርገጠኝ ተረገጥ ተብሎ የተፈጠረ  ወትሮስ ሌላ እጣ የለው: : አልረገጥም የለም አሻፈረኝ ቢልም እርግጫውን ቅጥ ያጣ ይሆንበት ይሆናል እንጂ ከመረገጥ አይዘልም:: በወግ መረገጥም እኮ ወግ ነው ::

ሀበሽ አረ ግድ የለህም አድምጠኝ  እኔም የምልህ ይሄንኑ ነው በወጉ እርገጠኝ መንገዱን ምረጥልኝ መንገድ ከመረጥክልኝ አለወግ ብትረግጠኝም እድሜዬ ይረዝማልና የመገላገል እጣ ይኖረኝ ይሆናል እንደው ከሰማዐኝ ልምከርህ ላንተም ስል ነው እንደው ምን አለ እያረፍክስ ቢሆን መርገጡ! ለአንተም እኮ ለጤናህ ጥሩ አይደለም እንደምታዬኝ እኔንም አቧራ ለአቧራ ስታኳትነኝ ሳሉ ቀትሎ ሊገድለኝ ነው ብላኝ ቀሰስ ያለች ትንታ ቢጤ ሳል ያሳለች መሰለኝ።

ተረጋጭ ሲመክርም ሲናገርም አይንህን ለአፈር ነውና ጫማ ማስቀመጫው ላይ ወዝፊያት ሽቅብ የመስጅዱን ደረጃ ወጣሁ እፎይ ያለች መሰለኝ ጫማዬ ለካ ለጥቂትም ጊዜ ማረፍ  ለጥቂትም መትረፍ እፎይ ያሰኛል።

ሰው የእለት ግዴታዬን ልወጣ ብሎ ወደሚገባበት መስጂድ እኔ ብሂሉን ቀይሬ የእለት ውዴታዬን ልወጣ ብዬ እየገባሁ ነበር ኡዱዕ ለማድረግ ሰልፍ ያዝኩ መቼም ለአዲስ አበቤ ሰልፍ እንደ አንገት ሀብል ጌጥ ከሆናት ቆየ ።


ሌላው ቢቀር ሰው እንዴት ለሽንት ቤት ይሰለፋል? አንድ አንድ ጊዜ ሰብር የሌለው አ*ም ባይ*ራስ ብሎ ተሰላፊውን አ*ም አመናጭቆ ይሄዳል ተሰላፊውም አ*ም ገርመም አድርጐት ፈገግ ይላል ፈገግታዋ መልዕክት አዘል ምፀት ናት።

ጓዴ ሲወጥርህ ትመለሳታለህን ከተሰላፊ አ*ም ወደ ትዕግስት የለሽ አ*ም ግልባጭ ለሽንት ቤቱ አስተዳደር የምትል መልዕክትን ታስተላልፋለች። አ*ም አ*ሙን እየገላመጠ ነው እኮ የማ*ራ የሚመስለው እንዲ*ራብን ቀበቶውን ተጋግዘን የምንፈታለት። ጐበዝ ከነአ*ችሁ ለምን አትከባበሩም በኋላ ያጣደፈው እንዳ*ራባችሁ ልል ዳዳኝና ድዴን ሲሉኝ ስለታየኝ ዝም አልኩ።

ሌላ ነገር ትኩረቴን ሳበው አንድ ሰው ላይ አይኔ አረፈ ኡዱዕ ለማድረግ ከተሰለፍን ከእኔና አንድ ከፊቴ ካለ ሌላ ሰው ውጪ ትጥበቱን የጀመረ አንድ ሰው ላይ አይኔ አረፈ።  እሰይ ተራዬ እስኪደርስ የማስበው አገኘሁ ይመስል ውስጤ ተፍነከነከ። በሁለት ነገሩ በሰውየው እኔና ውስጤ ተገረምን።

አንደኛ ለትጥበት (ኡዱዕ) ተብሎ የተዘጋጀ መቀመጫ እያለ አጐንብሶ መጠቀሙ እና ቧንቧዋን እንዳትሞት እነዳትሽር አድርጐ በጭላንጭል ከጭላንጭልም ጭላንጭል በሚመስል ከፍቶ ኡዱዕ እያደረገ መሆኑ ነው።

መቼም በዚሀ ቧንቧ አከፋፈቱ ኡዶውን ትቶ ባልዲ ቢደቅንበት ዘመን አልፎ ውሀው ሞልቶ  የምን መዝረክረክ ነው ብሎ
የሚዘጋው ደጃል ይመስለኛል ወይም ወይም በዚህ አደራረጉ የሚጨርስ ቂያማ ሲቆም ነው ያው የሞት መላይካውም ኡዶውን ከማቋርጠው ብሎ ትቶት ዘመኑ አልፎ የተነሱ መለከቱ ሲነፋ ኢቃም መስሎት ዞር ሲል ሰውዬ ቧንቧውን ዝጋውና እዚያ ሜዳ ላይ ሂድ ሂሳብ እየተወራረደ ነው ብሎ አንድ መላይካ ገላምጦት የሚሄድ ይመስለኛል።

ጥያቄዎች ውስጤን ወጠሩኝ ቆይ ሰውዬው ውሀ እያቆጠበ መስሎት ይሆን? መስሎት ነው እንበል ግን ቧንቧዋን በጥቂቷ ከፍቶ ውሀ ሲቆጥብ የራሱን ጨምሮ የብዙሀኑን ጊዜ በሰፊው ከፍቶ እያባከነው እንደሆነ አልተገለጠለትም ይሆን?

ስንቱ ይሆን አንዱን ቆጥቦ ሌላውን አብዝቶ ያባከነው?።የቆጡን አወርድ ብላ የሚባለውስ ይሄ ይሆን? ቆይ ከጊዜ እና ከውሀስ የቱን ነው መቆጠብ ያለብን? በውሀ ጊዜ ይሰራል? በጊዜ ውሀ እንጂ

የምንቆጥበው በውል ያልተገለጠልን የቆጣቢ አባካኝ የቁጥብ ብኩን የሆንን መስሎ ተሰማኝ።

ሰው ወይ አባካኝ ወይ ቆጣቢ ይሆናል ወይ አመዛዝኖ ይኖራል እንጂ እንዴት አንዱን ቧንቧ አፈንድቶ በአንዱ ቧንቧ ቀንሼ ልጠቀም ይባላል?

ጨርሶ ሲሄድ ምዕተ አለም አልፎ ቧንቧውን ለመዝጋት ደጃልን ያየሁ መስሎኝ ደንገጥ አልኩ ኢቃም ተባለ በሱም ደንገጥ አልኩ የተነሱ መለከት መስሎኝ ይሄ ሰውዬ አንድ ነገር ሳልከውን ትንሳዔዬን አመጣብኝ ብዬ።

የእሱን እለህ የተወጣሁ ይመስል ውሀውን አባክኜ ጊዜየን ቆጥቤ የመጀመሪያው መጐንበስ ላይ ደረስኩ እንደደረስኩ ልክ በማሽን እንደሚታጠፍ ወፈር ያለ ብረት አፍታ ሳይፈጅብኝ ከአጐንባሹ ጋር ተጐነበስኩ።


@Habeshistan
231 viewsedited  20:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-16 20:38:12 አንድ ሰው ልክም ይሁን ትክክልም አይሁን እውነት ነው ብሎ ካለ ለእራሱ የእራሱ እውነት ከታየው በሚታየው እውነታ ያምናል።


እውነትስ ምንድን ነው?

አንድ እናት ለአመታት መውለድ ሳትችል በእንባ የምታምነውን ስትለምን ኖራ ከበዛ አመታት በኋላ የሚያምር ልጅ በከባድ ምጥ ስትገላገል ሁሌም አይኗ በሚያየው ፀጋ በደስታ ሲያነባ ልቧ ደስ ሲሰኝ በስስት እንስፍስፍ ስትል አመታት አልፈው በእግሩ ድክ ድክ ሲል ሳይወድቅ እኔን ብላ ቀድማው ስትወድቅ ሲስቅ ስትፍነከነክ ሲያለቅስ ስትንዘፈዘፍ እንዲህ እያሉ ከቀን ወደ ቀን ፍቅሯ ሲያይልባት ከጐና ፀጉሩን እየዳበሰች እንቅልፍ ሸለብ ሲያደርገው ትንፋሹን እያዳመጠች ሀሴት ሲሰማት ክንዷን አንተርሳው ከጐንፏ ሸጉጣ ከሙቀቷ ሙቀትን ስትቸረው ኖራ ኖራ በአንዱ ቀን ከተኛችበት ስትነሳ ልጇ እንደ ወትሮው ከመንቃት ይልቅ ባሸለበበት ቢቀር ያቺ እናት ምን ታደርጋለች ትንፋሹን ታዳምጣለች በህይወት መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ ነገር ግን ያ የምትሳሳለት ህፃን እስትንፋሱ ተቋርጣለች ሞቷል እንደሞተ አረጋገጠች ከዚያስ ታምናለች ወይ? መሞቱን ከማመን ይልቅ እሷ ጤነኛ አለመሆኗን ማመን ለእርሷ ሚዛን ይደፋል……………አይታመን የለ መሞቱን አምና አፈር አልብሳው ቤቷ ተመልሳ አልጋዋ ላይ ጋደም ብላ አብሮ ያለ ያህል ሲሰማት……… ወራት አመት አልፎም እንቅልፍ ሲያንገላጃት ብንን ብላ ፍራሿን ስትዳብስ የቱ ነው እውነት መሞቱ? መቅበሯ? ወይስ ልቧ እና አዕምሮዋ አጠገቧ እንዳለ ሲነግሯት ፍራሿን መዳበሷ? 




@Habeshistan
279 views17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-16 20:36:09 ካሊድ (ሀበሽስታን
በጣም አስገረመኝ በሀሳቡ እየተገረምኩ አፌ ላይ እንደመጣልኝ ልክ ብለሀል አልኩ………እንደዚህ ያለ ሀሳብ ካውጠነጠንኩ ወይም ከአሳቢያን ጋር ካሰብኩ ቀናት ስላለፉኝ በሀሳቡ ብቻ ሳይሆን ከእርሱ ጋር በማውጋቴ ውስጤ በሀሴት እየፈነጠዘ…… በአዕምሮዬ በብርሀን ፍጥነት ካለሁበት ወደሌለሁበት በሀሳብ ክንፍ ታግዤ  በሰፊው የሀሳቤ የብርሀን እልፍኝ ደርሼ የሀሳቤን ጨለማ እየዳሰስኩ ያልበራውን የእልፍኝ ክፍል ለማብራት ስልኮሰኮስ ያለበራውን እያበራሁ የጠፋውን አልያ የደበዘዘውን በያዝኩት የሀሳብ ጧፍ ለመለኮስ ስዛብቅ ደቂቃዎችን የፈጀሁ መሰለኝና ከብርሀን ሀሳቤ በብርሀን ፍጥነት ተምዘግዝጌ እንደመበርገግ ብዬ ነቃሁ ሀሳቡን ለመቀጠል ያህል ልክ ብለሀል አለኩ ደግሜ  ፊትለፊቴ የተቀመጠውን አንድ አሳቢ ወዳጄን ከአይኔ አልፌ በአዕምሮዬ አዕምሮውን የመዳሰስ ያህል ትኩር ብዬ እየተመለከትኩት ትክዝ ብሏል በሀሳቤ ሀሳቡን እየተጠባበቅኩ በሀሳብ ነጐድኩ……… እዚህ ሆኖ እዚያ ፣ እዚያ ሆኖ እዚህ፣ ተቀምጦ ሽምጥ ግልቢያ ፣ እየሮጡ እፎይ ብሎ እንደመቀመጥ ፣ ሄዶ መምጣት ፣ ሳይመጡ መሄድ ፣ ሳይሄዱ መምጣት ፣ አልሄድም ብሎ በአልሄድም ዛቢያ መሽከርከር ፣ ሄጃለሁ ብሎ እራሰን ካስቀመጡበት ጐርባጣ ላይ ማግኘት ፣ መሽከርከር በሀሳብ ነፋስ ወደ ሀሳብ ጉድጓድ መገፋት ፣ መሸንቆር ከሀሳብ ሲሸሹ የማያመልጡት ላይ መሰንቀር ፣ መባተል እንደገና እሁሁሁ ብሎ ማረፍ እንደገና ወደ እሁሁሁ የሃሳብ ኩሬ ላይ መዘፈቅ ፣ ተፍጨርጭሮ መውጣት እንደገና ያረፉ መምሰል በማረፍ ውስጥ አለማረፍ እራስን ካስወመጡበት ላይ በድን ሆኖ ማግኘት አንድ ሆነን ለሺህ መከፈል አንድ ሆነን በብዙ የሀሳብ መነሀሪያ ለመሳፈር ትኬት መቁረጥ መበታተን እራስን ስብሰባ ካሉበት ተነስቶ በዚያው የሀሳብ በቅሎ መማሰን ለመሰብሰብ እንደገና መበታተን ። ሀሳብ በራስ ላይ ሎሌ መሆን ፣ ፈልገውም ይሁን ተገደው የሀሳብ አሽከር መሆን ፣ እንዴት ያለ ነገር እራስ ለእራስ ሎሌ ፣ እራስ ለእራስ አሽከር ፣ እራስ ለእራስ ማብሪያ መሆን ፣ እራስ ለእራስ ማጥፊያ መሆን ፣ በእራሰ ውስጥ ወገግ ብሎ መብራት ፣ እንደገና በእራስ ውስጥ ክስም ብሎ መጥፋት አይ ሀሳብ ሳይሾሙት ተሹሞ እንደፈለግነው ሳይሆን እንደፈለገ የሚያስተዳድረን እንቆጣጠርህ ስንል እምብኝ ባይ እሺ እየተመካከርን ስንልም ከተስማማሁ ብሎ እንደፈለገ የሚያኳትነን የውስጣችን ውስጥ የመኖሪያችን መሳጢር በእራስ ውስጥ ሀገር መሆኛ አይ ካሉት እንኳንሰ ሀገር መንደር እንዳንሆን ሆኖ መጥበቢያ……… አይ ሀሳብ ስንጠቀምበት መጠቀሚያ ጠቃሚ ሲጠቀምብን ከራሱ አለፎ ለብዙው መጥፊያ……… ሀሳብ ይሉት ውቅያኖስ ወይ አይጠጡት ወይ ዋኝተው አይወጡት ሰርክ መፍጨርጨር ሲፍጨረጨሩ መስመጥ ሲሰምጡ ትንፋሽ ማጣት ተረጋግተው ሲንሳፈፉበት አጫዋች ………በዚህ መሀል ሀበሽ አለኝ ቀና ብዬ ተመለከትኩት ስለ ሀሳብ በሀሳብ እያሰብኩ አጠገቡ ሆኜ እርቄው ተጉዤ ከነበረበት በሄድኩበት ፍጥነት ወደ በድኔ ተመልሼ ወደ ሀሳቤ ውቅያኖስ ገብቼ ለመውጣት ማሰብን ስጨብጥ ሲያሰምጠኝ አለማሰብን ስይዝ ያንሳፈፈ መስሎ ውሀ እያሳሳቀ ነው የሚወስደው እንደሚባለው እያሳሳቀ ይዞኝ ሲሄድ መመለስን ስሻ እንደገና ስዘፈቅበት ምን ያህል ጊዜን እንደቆየሁ ባላውቅም ሀሳቤ ከበድኔ ገጣጥሜ በአይን ንግግር ያለ ይመስል ስመለከተው  የተቀመጠበትን ወንበር እያስተካከለ አይኑን ከፊታችን በተሰደሩት የቡና ሲኒዎች ላይ ተክሎ

እንዲህ አወጋ ወይም ጥያቄዎቹን ያዥጐደጉድብኝ ያዘ

ልክ ብለሀል ነው ያልከኝ አለኝ ይመለከታቸው ከነበሩት ሲኒዎች ላይ አይኑን ለአፍታ ነቅሎ ወደእኔ ሰርስሮ ውስጥን በሚበረብር እይታ እየተመለከተኝ… በአዎንታ እራሴን እየነቀነቅኩ ምን ሊያስብ እንደሆነ ለማሰብ የሀሳብ ፈረሴን ፊጥ አልኩበት አዕምሮዬ በሀሳቤ ነጭ ፈረስ ላይ ለመገስገስ ልጓሙን ጨብጦ መጭ ለማለት ዳዳው ሀሳቡን ሀሳብ ይሁን ጥያቄ ያለየልኝን ንግርት ያጐርፈው ጀመር


"ልክ መሆን ምንድን ነው ወይም ምን ማለት ነው? ልክ አለመሆንስ ምንድን ነው ወይም ምን ማለት ነው?"

ምን ሊያስብ እንደሆነ ለማሰብ የሀሳብ ፈረሱ ላይ ፊጥ ያለው አዕምሮዬ አስቦ እንዳስብ ወይም ጠይቆ እንዳስብ ያነሳውን ልክ መሆን ልክ አለመሆን ይሉትን የሀሳብ ጓዝ የሀሳብ ነጭ ፈረሴ ላይ ጭኜ ከሩቅ ሲያዩት ለሀሳብ ፈረስ የማይመቸውን መንገድ ልገሰግሰው ጠንካራውን የሀሳብ ነጭ ፈረሴን መጭ ብዬ ሽምጥ ጋለብኩት።

ግልቢያው ለጉድ ነው የሀሳብ ፈረሴ ፍጥነት ልኩን ያለፈ በመሆኑ ልክ መሆን ልክ አለመሆንን አልፎ ሩቅ ለመጓዝ ሲፈረጥጥ ተሳፋሪው አዕምሮዬ የዚህ ጊዜ ልጓሙን ለቀም አድርጐ ፍጥነቱን ገታ አደረገ መሄድን የማይጠግበው የሀሳቤ ነጭ ፈረስ መገታትን ተቃውሞ ሽቅብ ሁለት እግሩን ቢያነሳም ተሳፋሪው አዕምሮዬ ለመቆጣጠር  አልቸገረውም።
በሀሳቡ ነጭ ፈረስ ላይ የተሳፈረው አዕምሮዬ እዛው እንደተመቻቸ ሀሳቡን በሀሳብ ያንከላውስ ጀመር………

ልክ መሆን ልክ አለመሆን ምንድን ነው ከንግግሬ ተነስቼ ስቃኘው ልክ ነህ ማለቴ ያነሳውን ሀሳብ ለመደገፍ ልክ ነህ የሚለው ለአፌ ቀሎኝ በግድ የለሽነት ልክ ነህ ማለቴ ታወሰኝ። ልክ ነህ ማለቴ ደጋፊ ከሆነ ትክክል ነህ ለማለት እንደፈለግኩ ተገለጠልኝ ወይም በተናገረው ነገር ላይ እርግጠኝነቴን ላሳየሁ እንደሻሁ አስተዋልኩ ወይም ደግሞ ልክ ወይም ትክክል መሆኑን በእርግጠኝነት ማመኔን ልነግረው እንደፈለግኩ አወቅኩ ግን…………

ልክ መሆን ወይም ልክ አለመሆን

ትክክል መሆን አሊያም ትክክል አለመሆን

የቱ ነው መለኪያው ልክ ወይስ ትክክል?

ትክክል መሆን ምንድን ነው የምንስ ተቃራኒ ነው?

ልክ መሆንስ?

ትክክል ወይም ልክ ማለት እንደ እይታው ለየቅል ቢሆንም ወይም ባይሆንም እርግጠኝነትን የሚለካ ይመስለኛል እማይመስለኝም ይመስለኛል።

እርግጠኝነት እርግጠኝነትስ? መተማመን (እምነት) አለመጠራጠር ቢሆንስ ሆነ እንበል እንበል ነው እንጂ አሁንም እርግጠኞች አይደለንም። ምክንያቱም ልክ መሆን ትክክል መሆን እርግጠኛ መሆን መተማመን እሩቅ ነው! እሩቅስ……

አንድ ሰው ትክክል መሆኑ ነው ልክ ወይሰ ልክ መሆኑ ነው ትክክል
እርግጠኝነቱ ነው ትክክል ወይስ ማመኑ ነው ልክ

አንድ ሰው እርግጠኛ ሲሆን ወይም ሲያምን ትክክል ነው የሚሆነው ወይስ ልክ ነው የሚሆነው
ልክ የሚለው መስፈሪያ ነው ወይስ ማረጋገጫ?
ትክክል ፣ ልክ ፣ እምነት ፣ እርግጠኝነት ወይም ተቃራኒው ልክ መሆን ወይም ልክ አለመሆን ትክክል መሆን ትክክል አለመሆን በማህበረሰብ አይታ እንዴት ይታያል?

ትክክክ /እንደ እይታ ለአንድ ድርጊት ንግግር ወይም ሌላ ቀጣይነት እንዲኖረው ማበረታቻ ወይም ያለመበላሸት ማረጋገጫ መደገፊያ
ልክ /እንደ እይታ የነገራቶች መስፈሪያ መለኪያ ማስተያያ

ሁለቱም በአንድ ላይ ለአንድ ጥቅም ሲውሉ ልክም ትክክልም ተዋዋሽ የሚሆኑ ይመስለኛል አንድ ሰው ትክክል ነህ የሚባለው ትክክል ካልሆነ ነገር ጋር ተነፃፅር ተለክቶ ተመዝኖ የትክክል ሚዛን ሲያዘቀዝቅ ነው ስለዚህ ልክም ትክክልም ሲዋዋሱ ማረጋገጫ ይሆናሉ ነገሮች ደግሞ ሲረጋገጡ ይታመናሉ የሚታመኑት ደግሞ እውነት ናቸው ብለን ስለምናስብ ነው የልክ የትክክል የእርግጠኝነት የእምነት ጭማቂ ደግሞ እውነት ይሆናል ምክንያቱም አንድ ሰው ካሰበ ሳያረጋግጥ አያምንም የሚያረጋግጠው ደግሞ በልክ እና በትክክል አለፍ ሲል በእውነት መስፈሪያ ስለሆነ።ልክም ትክክልም ካለ እውነት ልክ አይሆኑም አንድ ሰው ልክም ይሁን ትክክልም አይሁን እውነት ነው ብሎ ካለ ለእራሱ
239 viewsedited  17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-19 17:51:11 ሲያፌዙብህ ባንተ መክሳት
መጥቆርህን አርገው ምክንያት

ነዋይ ከእጅህ እርቆብህ
ማጣትህ ጐልቶ ታይቶብህ
ብትሳቀቅ ከሰው መደነብ
ቢያሰቃይህ አለማግኘት ሲደራረብ


አልራገፍ እምቢኝ ሲልህ ፣  ሲሆን ድሪቶ
ማማርህን ሲያጠፋብህ ፣ ልክ እንደ ቡትቶ

አልጥም ቢል ወግህ ፣ ስትናገር ባትደመጥ
የሌለህን ያልመጣ ሳቅ ፣ ለመሳቅ ሰርክ ስታምጥ

ፈገግ ሲል ጥርስህ
ሲደብን አንጀትህ

ሲናገር ምላስህ
ሲቃጠልብህ ቆሽትህ

የምትናገረው ቅኔ ሆኖ ፣ ስታጣ የሚገባው
ከላይ እህ ብሎ ሰምቶ ፣ ሲበዛ የሚፈርደው
ሲደክምህ ሲጨንቅህ
መውጫ ቀዳዳው ሲጠፋብህ

የምታደርገው ግራ ገብቶህ
ሲባዝንብህ አዕምሮህ………


አቤት በለው ለጌታህ
ለዚያ ከእናትህ አስቀድሞ ለሚያውቅህ
ለዚያ ከእናትህ በላይ ለሚወድህ
ለዚያ ከእርሷ በላይ እንደሚወድህ
ሰርክ አብዝቶ ለነገረህ
ንገረው ለጌታህ!!!!!




@Habeshistan
372 viewsedited  14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-19 17:51:09
ካሊድ (ሀበሽስታን)

ስትባል


እንዲህ ቢሉህ………

ሸክሙ ሲከብድ ፣ ሲደራረብ ጫንቃህ ሲዝል
ማራገፉ መጣል ሲያሻህ መገላገል

ሲያስጨንቅህ በልብህ ሲንገዋለል
አዕምሮ ሲከፈል በሀሳብ ሲወጣጠር

በጭንቀት ማዕበል ሲገፋ ሲንጥህ
ከአንዱ ሀሳብ ወደ ሌላው ፣ ሲያወጣ ሲያስገባህ

ሲደፍቅህ ከስምጡ ፣ ሲሆንብህ ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ
ሲጠናብህ መረበሹ ፣ ህይወት ስትጠም ስትል እምቢ

ደግሞ አንችን እንዲህ ቢሉሽ………

ቆሞ ቀር ናት አትገደር
ወይ አታምር ወይ አታፍር

እንዲህ ብለው በአንቺ ፣ ሁል ጊዜ ቢቀልዱ
ስምሽን ለማጠፋት ሴትነትሽን ቢማግዱ

ብለው ቢሉህ………

ሲዝልብህ ጉልበትህ ፣ አልችል ብሎ ሲብረከረክ
ሸክሙ እያደር ሲጠና ፣ ለማራገፍ እየሞከርክ

አንችንም………

ይህቺ ብለው ስም ቢቀጥሉብሽ
በሌለሽበት ባልዋልሽበት ቢከልሱሽ

ደግሞ አንተን………

ሳይመችህ ስትጠቁር ስትከሳ
ያገኘሀት ሆና ሲሶ ፣ እንዳትጠፋ ስትሳሳ

ብለው ቢሉሽ………

አያምርባት ምን ብትለብስ
ትውላለቸ ከጓዳዋ ይህች ትብስብስ…
ተብሎ በአንቺ ላይ ቢነዛብሸ
የነገር ቁርሾው ቢበዛብሸ ……
ቁንጅናሽ ቢሳሳ እድሜሽ ሄዶ
ለመጥፋትሽ ሲማግዱ ማገዶ………
እንዳልነበር!

…ስትጠፊ ቢያሙሽ
ደግመው ሌላ ስም ቢለጥፉብሽ……
እንዳይከፋሽ

አንተንም………
298 viewsedited  14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-01 20:25:39 "ፊት"!!! ያፈቀርኩ እለት!!!




ካሊድ (ሀበሺስታን)


3

አንድ ቀን ልክ በቁም ነገር እንደሚማር እንደሚገባው ሰው በጠዋቱ መጥቶ ክፍል ውስጥ ገባ ።ስንማር ቆይተን በእረፍት ሰዐት ካለ ወትሮው <<ሀበሽ ና ፈልጌህ ነው>> ብሎ ከዘላለም ነጥሎ ይዞኝ ሄደ።

ብዙም አልገረመኝም። ይዞኝ ተማሪው ብዙም ብር ያለው ስለሌለ መምህራን ብቻ ወደሚጠቀሙበት ሻይ ክበብ ሄደ ።

ይሄ ክበብ ከሚገርመኝ የሚጠቀሙበት መምህራን ስሙ ግን የተማሪዎች ክበብ መባሉ ነው። <<ምን ልናደርግ ነው እዚህ የመጣነው?>> ስለው ዝም ብሎኝ መንገዳችንን ቀጠልን። ደርሰን ማን በላ ማን ቀረ እንደሚቆጣጠር ሰው ረጅም ደቂቃ ቆምን። መጨረሻውን ለማየት እኔም ምንም ሳልለው ቆሜ እየጠበቅኩት ከሚኒ ሚዲያ የጥላሁንን ውብ አይናማ ዘፈን ጆሮ በሚቆረቁር ማይክ ይሰማናል። ብዙም ልብ ብሎ የሚሰማው ተማሪ ግን የለም።
<<ውብ አይናማ ከእግር እስከ እራሷ
ውብ አይናማ…………>>


ትንሽ ቆይቶ <<ስማ ሀበሽ>> አለ ዙሪያ ገባውን በአይኑ እያማተረ። <<እኔ እዛ ጋር እጠብቅሀለሁ በዚህ ሳንቡሳ ገዝተህ ይዘህ ና>> ብሎ ከእጁ ሶስት የወረቀት ብር እጄ ላይ አስቀመጠልኝ።በጣም ደነገጥኩ የደነገጥኩ ሰርቆ እንደሚያመጣው ስለማውቅ ነው።

ፈራ ተባ እያልኩ ክበብ ገብቼ የሰጠኝን ሶስት ብር ከእጄ አውጥቼ ለአስተናጋጇ ሰጠኋት። ሄጄ ገዛሁ ማንም እንዳያየኝ እና ዘይቱ ልብሴን እንዳይነካኝ እየተጠነቀቅኩ ያለኝ ቦታ ደርሼ ሳንቡሳውን አቀበልኩትት እና የተመለሰልኝን ሀምሳ ሳንቲም <<እንካ>> ስለው ሳንቡሳውን ተቀብሎ ሳንቲሙን ቆይ ያዘው ብሎ ከመቀመጫው ተነስቶ መሄድ ጀመርን። ከላይ ያለውን ቅርፊት ሰጥቶኝ ሌላውን በላው።

የእረፍት ሰዐት አልቆ ወደ ክፍል ተመለስን። ከተወሰኑ ደቂቃ በኋላ ተጠራን እናቱ ነበረች። ሰረቁ ተብሎ መምህሩ ሁላ ጥርሱን ነከሰብን። << እኔ አልሰረቅኩም እሱ ነው የገዛው>> ሲል ድርቅ አልኩ። ካላመናችሁ ፈትሹት መልሱም ኪሱ ውስጥ ነው ብሎ አስፈተሸኝ። ሀምሳ ሳንቲሟ በመገኘቷ ሌባ ሲሉኝ መምህራን የአብዱልሀኪም እናት ግን <<ተው እሱ አይሰርቅም የእኔው ልጅ ነው ሌባ ቆይ ማታ እንገናኝ>> ብላ ዝታበት ሄደች። ከዚያ ቀን በኋላ ሳንቡሳ ሳይ አብዱልሀኪም ነው የሚመጣብኝ ሳንቡሳ እና አብዱልሀኪም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ነው የሚመስሉኝ።


ከእኔ እና ዘላለም ጐን ተግባር የሚባል ልጅ ይቀመጣል። ተግባርና ንፅህና ደግሞ የማይቀራረቡ ፀበኞች እንደሆኑ የምታውቁት ተግባርን ፀጐሩን በአምስት ጣቱ ሲያክ ሲያክ ከማለት ይልቅ ሲቆፍር ይቀርባል ከተመለከታችሁ ነው።የዮኒፎርሙ የሸሚዝ እጅጌ ንፍጡን ስለሚጠርግበት ሲደርቅ ያብለጨልጫል፤ አንድ ጊዜ እንደውም በእሱ እጅጌ በጠረገው እና ሲደርቅ በሚያብለጨልጨው ልብሱ ምክንያት አንፀባርቆብኝ አይኔን ለህመም ዳርጐኛል (ሲጋነን ነው)

ተግባር ምስኪን ልጅ ነበር። ከትምህርት ቤት ተለቀን ሁሉም ወደጨዋታው ሲያቀና እሱ ጫማ ተራ ገብቶ በትርፍ ሰዐቱ ሊስትሮ ይጠርጋል። ጫማ ይሰፋል። በገቢ ደረጃ ሐ ግብር ከፋይ ያህል ገቢ ያለው ብቸኛው የክፍላችን ተማሪ ነው። ከክፍላችን ውጪ ያለ አንድ ልጅ ብቻ ደረጃ ለ በመሆን በገቢ ደረጃ ይገዳደረዋል። ሳስበው የተግባር ህልም ሰርቶ ቢሊየነር መሆን ሳይሆን የሚበልጠውን ደረጃ ለ ልጅ መብለጥ ይመስለኛል።


ከእኛ በፊት ለፊት ያለ እረድፍ ላይ የሚቀመጥ መሀመድ የሚባል ልጅ ነው። መሀመድን ሁሉም የሚያውቀው በሁለት ነገር ነው አንደኛው በዛ እድሜው ፀጉሩ ገብቶ ገብቶ መሀል ላይ በመድረሱ ነው። መላጣ ሲባል ከሰማ ግን የትም ቢገባ መላጣ ያለውን ልጅ ከአቦ ሸማኔ በሚስተካከል እሩጫ አሳዶ ይዞ ዞማ ማለትም የእኔን የማለ ፀጉር ያለውን ልጅ መላጣ የሚያደርግ ጥፊ ይሰማል። አንድ አንድ ጊዜ ሳየው ትንሹ መለስ ዜናዊም ይመስለኝ ነበር። ከመለስ ጋር የሚያመሳስለው መላጠው ብቻ ነው። ልክ እንደፀጉሩ እውቀቱም መላጣ ነበር እንጥፍጣፊ እውቀት አልነበረውም።

ሁለተኛው በዮኒፎርም ሱሪው ኪሱ ሙሉ ይዞ በሚመጣው ቆሎ ነው። እረፍት ሰአት ስንወጣ አንድ ጥግ ሄዶ ቆሎ መፍጨት የዘወትር ተግባሩ ነበር። ግርም የሚለኝ <<ፈጣሪ ይሄን ልጅ በፀጉር እና በእውቀት ፋንታ ጥርስ መርቆ ነው እንዴ የሰጠው>> እላለሁ። ያልኩበት ምክንያት ሙሉ ከረጢት የሚያህል ኪስ የተወሸቀ ቆሎ በአስራ አምስት ደቂቃ ፈጭቶ አጠናቆ ምንም ሳይደክመው ሲመለስ ስለምመለከተው ነው። አድጌ ከረጅም ጊዜ በኋላ በስራ አለም የጠጠር መፍጫ ክሬቸር ስመለከት መጀመሪያ አዕምሮዬ ላይ የመጣው መሀመድ መላጣው ነበር።




ይቀጥላል……………





@Habeshistan
421 views17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ