Get Mystery Box with random crypto!

ካሊድ (ሀበሽስታን በጣም አስገረመኝ በሀሳቡ እየተገረምኩ አፌ ላይ እንደመጣልኝ ልክ ብለሀል አልኩ… | ሀበሻዊ ጥበባት

ካሊድ (ሀበሽስታን
በጣም አስገረመኝ በሀሳቡ እየተገረምኩ አፌ ላይ እንደመጣልኝ ልክ ብለሀል አልኩ………እንደዚህ ያለ ሀሳብ ካውጠነጠንኩ ወይም ከአሳቢያን ጋር ካሰብኩ ቀናት ስላለፉኝ በሀሳቡ ብቻ ሳይሆን ከእርሱ ጋር በማውጋቴ ውስጤ በሀሴት እየፈነጠዘ…… በአዕምሮዬ በብርሀን ፍጥነት ካለሁበት ወደሌለሁበት በሀሳብ ክንፍ ታግዤ  በሰፊው የሀሳቤ የብርሀን እልፍኝ ደርሼ የሀሳቤን ጨለማ እየዳሰስኩ ያልበራውን የእልፍኝ ክፍል ለማብራት ስልኮሰኮስ ያለበራውን እያበራሁ የጠፋውን አልያ የደበዘዘውን በያዝኩት የሀሳብ ጧፍ ለመለኮስ ስዛብቅ ደቂቃዎችን የፈጀሁ መሰለኝና ከብርሀን ሀሳቤ በብርሀን ፍጥነት ተምዘግዝጌ እንደመበርገግ ብዬ ነቃሁ ሀሳቡን ለመቀጠል ያህል ልክ ብለሀል አለኩ ደግሜ  ፊትለፊቴ የተቀመጠውን አንድ አሳቢ ወዳጄን ከአይኔ አልፌ በአዕምሮዬ አዕምሮውን የመዳሰስ ያህል ትኩር ብዬ እየተመለከትኩት ትክዝ ብሏል በሀሳቤ ሀሳቡን እየተጠባበቅኩ በሀሳብ ነጐድኩ……… እዚህ ሆኖ እዚያ ፣ እዚያ ሆኖ እዚህ፣ ተቀምጦ ሽምጥ ግልቢያ ፣ እየሮጡ እፎይ ብሎ እንደመቀመጥ ፣ ሄዶ መምጣት ፣ ሳይመጡ መሄድ ፣ ሳይሄዱ መምጣት ፣ አልሄድም ብሎ በአልሄድም ዛቢያ መሽከርከር ፣ ሄጃለሁ ብሎ እራሰን ካስቀመጡበት ጐርባጣ ላይ ማግኘት ፣ መሽከርከር በሀሳብ ነፋስ ወደ ሀሳብ ጉድጓድ መገፋት ፣ መሸንቆር ከሀሳብ ሲሸሹ የማያመልጡት ላይ መሰንቀር ፣ መባተል እንደገና እሁሁሁ ብሎ ማረፍ እንደገና ወደ እሁሁሁ የሃሳብ ኩሬ ላይ መዘፈቅ ፣ ተፍጨርጭሮ መውጣት እንደገና ያረፉ መምሰል በማረፍ ውስጥ አለማረፍ እራስን ካስወመጡበት ላይ በድን ሆኖ ማግኘት አንድ ሆነን ለሺህ መከፈል አንድ ሆነን በብዙ የሀሳብ መነሀሪያ ለመሳፈር ትኬት መቁረጥ መበታተን እራስን ስብሰባ ካሉበት ተነስቶ በዚያው የሀሳብ በቅሎ መማሰን ለመሰብሰብ እንደገና መበታተን ። ሀሳብ በራስ ላይ ሎሌ መሆን ፣ ፈልገውም ይሁን ተገደው የሀሳብ አሽከር መሆን ፣ እንዴት ያለ ነገር እራስ ለእራስ ሎሌ ፣ እራስ ለእራስ አሽከር ፣ እራስ ለእራስ ማብሪያ መሆን ፣ እራስ ለእራስ ማጥፊያ መሆን ፣ በእራሰ ውስጥ ወገግ ብሎ መብራት ፣ እንደገና በእራስ ውስጥ ክስም ብሎ መጥፋት አይ ሀሳብ ሳይሾሙት ተሹሞ እንደፈለግነው ሳይሆን እንደፈለገ የሚያስተዳድረን እንቆጣጠርህ ስንል እምብኝ ባይ እሺ እየተመካከርን ስንልም ከተስማማሁ ብሎ እንደፈለገ የሚያኳትነን የውስጣችን ውስጥ የመኖሪያችን መሳጢር በእራስ ውስጥ ሀገር መሆኛ አይ ካሉት እንኳንሰ ሀገር መንደር እንዳንሆን ሆኖ መጥበቢያ……… አይ ሀሳብ ስንጠቀምበት መጠቀሚያ ጠቃሚ ሲጠቀምብን ከራሱ አለፎ ለብዙው መጥፊያ……… ሀሳብ ይሉት ውቅያኖስ ወይ አይጠጡት ወይ ዋኝተው አይወጡት ሰርክ መፍጨርጨር ሲፍጨረጨሩ መስመጥ ሲሰምጡ ትንፋሽ ማጣት ተረጋግተው ሲንሳፈፉበት አጫዋች ………በዚህ መሀል ሀበሽ አለኝ ቀና ብዬ ተመለከትኩት ስለ ሀሳብ በሀሳብ እያሰብኩ አጠገቡ ሆኜ እርቄው ተጉዤ ከነበረበት በሄድኩበት ፍጥነት ወደ በድኔ ተመልሼ ወደ ሀሳቤ ውቅያኖስ ገብቼ ለመውጣት ማሰብን ስጨብጥ ሲያሰምጠኝ አለማሰብን ስይዝ ያንሳፈፈ መስሎ ውሀ እያሳሳቀ ነው የሚወስደው እንደሚባለው እያሳሳቀ ይዞኝ ሲሄድ መመለስን ስሻ እንደገና ስዘፈቅበት ምን ያህል ጊዜን እንደቆየሁ ባላውቅም ሀሳቤ ከበድኔ ገጣጥሜ በአይን ንግግር ያለ ይመስል ስመለከተው  የተቀመጠበትን ወንበር እያስተካከለ አይኑን ከፊታችን በተሰደሩት የቡና ሲኒዎች ላይ ተክሎ

እንዲህ አወጋ ወይም ጥያቄዎቹን ያዥጐደጉድብኝ ያዘ

ልክ ብለሀል ነው ያልከኝ አለኝ ይመለከታቸው ከነበሩት ሲኒዎች ላይ አይኑን ለአፍታ ነቅሎ ወደእኔ ሰርስሮ ውስጥን በሚበረብር እይታ እየተመለከተኝ… በአዎንታ እራሴን እየነቀነቅኩ ምን ሊያስብ እንደሆነ ለማሰብ የሀሳብ ፈረሴን ፊጥ አልኩበት አዕምሮዬ በሀሳቤ ነጭ ፈረስ ላይ ለመገስገስ ልጓሙን ጨብጦ መጭ ለማለት ዳዳው ሀሳቡን ሀሳብ ይሁን ጥያቄ ያለየልኝን ንግርት ያጐርፈው ጀመር


"ልክ መሆን ምንድን ነው ወይም ምን ማለት ነው? ልክ አለመሆንስ ምንድን ነው ወይም ምን ማለት ነው?"

ምን ሊያስብ እንደሆነ ለማሰብ የሀሳብ ፈረሱ ላይ ፊጥ ያለው አዕምሮዬ አስቦ እንዳስብ ወይም ጠይቆ እንዳስብ ያነሳውን ልክ መሆን ልክ አለመሆን ይሉትን የሀሳብ ጓዝ የሀሳብ ነጭ ፈረሴ ላይ ጭኜ ከሩቅ ሲያዩት ለሀሳብ ፈረስ የማይመቸውን መንገድ ልገሰግሰው ጠንካራውን የሀሳብ ነጭ ፈረሴን መጭ ብዬ ሽምጥ ጋለብኩት።

ግልቢያው ለጉድ ነው የሀሳብ ፈረሴ ፍጥነት ልኩን ያለፈ በመሆኑ ልክ መሆን ልክ አለመሆንን አልፎ ሩቅ ለመጓዝ ሲፈረጥጥ ተሳፋሪው አዕምሮዬ የዚህ ጊዜ ልጓሙን ለቀም አድርጐ ፍጥነቱን ገታ አደረገ መሄድን የማይጠግበው የሀሳቤ ነጭ ፈረስ መገታትን ተቃውሞ ሽቅብ ሁለት እግሩን ቢያነሳም ተሳፋሪው አዕምሮዬ ለመቆጣጠር  አልቸገረውም።
በሀሳቡ ነጭ ፈረስ ላይ የተሳፈረው አዕምሮዬ እዛው እንደተመቻቸ ሀሳቡን በሀሳብ ያንከላውስ ጀመር………

ልክ መሆን ልክ አለመሆን ምንድን ነው ከንግግሬ ተነስቼ ስቃኘው ልክ ነህ ማለቴ ያነሳውን ሀሳብ ለመደገፍ ልክ ነህ የሚለው ለአፌ ቀሎኝ በግድ የለሽነት ልክ ነህ ማለቴ ታወሰኝ። ልክ ነህ ማለቴ ደጋፊ ከሆነ ትክክል ነህ ለማለት እንደፈለግኩ ተገለጠልኝ ወይም በተናገረው ነገር ላይ እርግጠኝነቴን ላሳየሁ እንደሻሁ አስተዋልኩ ወይም ደግሞ ልክ ወይም ትክክል መሆኑን በእርግጠኝነት ማመኔን ልነግረው እንደፈለግኩ አወቅኩ ግን…………

ልክ መሆን ወይም ልክ አለመሆን

ትክክል መሆን አሊያም ትክክል አለመሆን

የቱ ነው መለኪያው ልክ ወይስ ትክክል?

ትክክል መሆን ምንድን ነው የምንስ ተቃራኒ ነው?

ልክ መሆንስ?

ትክክል ወይም ልክ ማለት እንደ እይታው ለየቅል ቢሆንም ወይም ባይሆንም እርግጠኝነትን የሚለካ ይመስለኛል እማይመስለኝም ይመስለኛል።

እርግጠኝነት እርግጠኝነትስ? መተማመን (እምነት) አለመጠራጠር ቢሆንስ ሆነ እንበል እንበል ነው እንጂ አሁንም እርግጠኞች አይደለንም። ምክንያቱም ልክ መሆን ትክክል መሆን እርግጠኛ መሆን መተማመን እሩቅ ነው! እሩቅስ……

አንድ ሰው ትክክል መሆኑ ነው ልክ ወይሰ ልክ መሆኑ ነው ትክክል
እርግጠኝነቱ ነው ትክክል ወይስ ማመኑ ነው ልክ

አንድ ሰው እርግጠኛ ሲሆን ወይም ሲያምን ትክክል ነው የሚሆነው ወይስ ልክ ነው የሚሆነው
ልክ የሚለው መስፈሪያ ነው ወይስ ማረጋገጫ?
ትክክል ፣ ልክ ፣ እምነት ፣ እርግጠኝነት ወይም ተቃራኒው ልክ መሆን ወይም ልክ አለመሆን ትክክል መሆን ትክክል አለመሆን በማህበረሰብ አይታ እንዴት ይታያል?

ትክክክ /እንደ እይታ ለአንድ ድርጊት ንግግር ወይም ሌላ ቀጣይነት እንዲኖረው ማበረታቻ ወይም ያለመበላሸት ማረጋገጫ መደገፊያ
ልክ /እንደ እይታ የነገራቶች መስፈሪያ መለኪያ ማስተያያ

ሁለቱም በአንድ ላይ ለአንድ ጥቅም ሲውሉ ልክም ትክክልም ተዋዋሽ የሚሆኑ ይመስለኛል አንድ ሰው ትክክል ነህ የሚባለው ትክክል ካልሆነ ነገር ጋር ተነፃፅር ተለክቶ ተመዝኖ የትክክል ሚዛን ሲያዘቀዝቅ ነው ስለዚህ ልክም ትክክልም ሲዋዋሱ ማረጋገጫ ይሆናሉ ነገሮች ደግሞ ሲረጋገጡ ይታመናሉ የሚታመኑት ደግሞ እውነት ናቸው ብለን ስለምናስብ ነው የልክ የትክክል የእርግጠኝነት የእምነት ጭማቂ ደግሞ እውነት ይሆናል ምክንያቱም አንድ ሰው ካሰበ ሳያረጋግጥ አያምንም የሚያረጋግጠው ደግሞ በልክ እና በትክክል አለፍ ሲል በእውነት መስፈሪያ ስለሆነ።ልክም ትክክልም ካለ እውነት ልክ አይሆኑም አንድ ሰው ልክም ይሁን ትክክልም አይሁን እውነት ነው ብሎ ካለ ለእራሱ