Get Mystery Box with random crypto!

ሲያፌዙብህ ባንተ መክሳት መጥቆርህን አርገው ምክንያት ነዋይ ከእጅህ እርቆብህ ማጣትህ ጐልቶ ታይ | ሀበሻዊ ጥበባት

ሲያፌዙብህ ባንተ መክሳት
መጥቆርህን አርገው ምክንያት

ነዋይ ከእጅህ እርቆብህ
ማጣትህ ጐልቶ ታይቶብህ
ብትሳቀቅ ከሰው መደነብ
ቢያሰቃይህ አለማግኘት ሲደራረብ


አልራገፍ እምቢኝ ሲልህ ፣  ሲሆን ድሪቶ
ማማርህን ሲያጠፋብህ ፣ ልክ እንደ ቡትቶ

አልጥም ቢል ወግህ ፣ ስትናገር ባትደመጥ
የሌለህን ያልመጣ ሳቅ ፣ ለመሳቅ ሰርክ ስታምጥ

ፈገግ ሲል ጥርስህ
ሲደብን አንጀትህ

ሲናገር ምላስህ
ሲቃጠልብህ ቆሽትህ

የምትናገረው ቅኔ ሆኖ ፣ ስታጣ የሚገባው
ከላይ እህ ብሎ ሰምቶ ፣ ሲበዛ የሚፈርደው
ሲደክምህ ሲጨንቅህ
መውጫ ቀዳዳው ሲጠፋብህ

የምታደርገው ግራ ገብቶህ
ሲባዝንብህ አዕምሮህ………


አቤት በለው ለጌታህ
ለዚያ ከእናትህ አስቀድሞ ለሚያውቅህ
ለዚያ ከእናትህ በላይ ለሚወድህ
ለዚያ ከእርሷ በላይ እንደሚወድህ
ሰርክ አብዝቶ ለነገረህ
ንገረው ለጌታህ!!!!!




@Habeshistan