Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ሰው ልክም ይሁን ትክክልም አይሁን እውነት ነው ብሎ ካለ ለእራሱ የእራሱ እውነት ከታየው በሚ | ሀበሻዊ ጥበባት

አንድ ሰው ልክም ይሁን ትክክልም አይሁን እውነት ነው ብሎ ካለ ለእራሱ የእራሱ እውነት ከታየው በሚታየው እውነታ ያምናል።


እውነትስ ምንድን ነው?

አንድ እናት ለአመታት መውለድ ሳትችል በእንባ የምታምነውን ስትለምን ኖራ ከበዛ አመታት በኋላ የሚያምር ልጅ በከባድ ምጥ ስትገላገል ሁሌም አይኗ በሚያየው ፀጋ በደስታ ሲያነባ ልቧ ደስ ሲሰኝ በስስት እንስፍስፍ ስትል አመታት አልፈው በእግሩ ድክ ድክ ሲል ሳይወድቅ እኔን ብላ ቀድማው ስትወድቅ ሲስቅ ስትፍነከነክ ሲያለቅስ ስትንዘፈዘፍ እንዲህ እያሉ ከቀን ወደ ቀን ፍቅሯ ሲያይልባት ከጐና ፀጉሩን እየዳበሰች እንቅልፍ ሸለብ ሲያደርገው ትንፋሹን እያዳመጠች ሀሴት ሲሰማት ክንዷን አንተርሳው ከጐንፏ ሸጉጣ ከሙቀቷ ሙቀትን ስትቸረው ኖራ ኖራ በአንዱ ቀን ከተኛችበት ስትነሳ ልጇ እንደ ወትሮው ከመንቃት ይልቅ ባሸለበበት ቢቀር ያቺ እናት ምን ታደርጋለች ትንፋሹን ታዳምጣለች በህይወት መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ ነገር ግን ያ የምትሳሳለት ህፃን እስትንፋሱ ተቋርጣለች ሞቷል እንደሞተ አረጋገጠች ከዚያስ ታምናለች ወይ? መሞቱን ከማመን ይልቅ እሷ ጤነኛ አለመሆኗን ማመን ለእርሷ ሚዛን ይደፋል……………አይታመን የለ መሞቱን አምና አፈር አልብሳው ቤቷ ተመልሳ አልጋዋ ላይ ጋደም ብላ አብሮ ያለ ያህል ሲሰማት……… ወራት አመት አልፎም እንቅልፍ ሲያንገላጃት ብንን ብላ ፍራሿን ስትዳብስ የቱ ነው እውነት መሞቱ? መቅበሯ? ወይስ ልቧ እና አዕምሮዋ አጠገቧ እንዳለ ሲነግሯት ፍራሿን መዳበሷ? 




@Habeshistan