Get Mystery Box with random crypto!

ካሊድ (ሀበሽስታን) አንድ አንድ ሀሳቦቸ 4 አለ ደግሞ አንድ አንድ ጊዜ እንዲህ ያለ ስሜት… | ሀበሻዊ ጥበባት

ካሊድ (ሀበሽስታን)


አንድ አንድ ሀሳቦቸ 4


አለ ደግሞ አንድ አንድ ጊዜ እንዲህ ያለ ስሜት… ……የማያውቁትን የሚያስናፍቅ……… የሚያውቁትን የሚያጥላላ……… የማያውቋትን አለም መናፈቅ……… የሚያውቁትን አለም የሚያስቀፍፍ……… ዝም ብሎ ብረር ብረር የሚያሰኝ……… እስኪ ጩህ ይውጣልህ የሚያሰኝ……… ሳቅ የቀላቀለ ሳግ የሚ ያፍንበት ………ሳቁም ሳጉም እኔ ቀድሜ ልውጣ ግብ ግብ የሚገጥሙበት ………… በደስታ ዘፈን እሪ ብሎ የሚያስለቅስ የመከፋት ጥንስስ እንደ ሽል  አንጀት ውስጥ የሚያፈራግጥ  ………በሀዘን ደረት በሚያስደቃ ሁኔታ እጅን እንደ መቀነት ሆድ ላይ ጐንጉና በሳቅ የሚያንተከትክ………የተምታታ………የሚያውቋትን ቀርቶ የማያውቋትን የፍቅር አጋር በሩቅ ተስፋ ፀጉር ስትዳብስ እንደ ቅዠት አድርጐ የሚያሳልም………እየሳቁ ያሉትን ሳቅ ንቆ አዲስ ሳቅ መመኘት……… የሚያለቅሱበት ሰበብ ሳያልቅ የሚያለቅሱት የእንባ ዘለላ ሳይነጥፍ ሌላ የእንባ ማፍለቂያ ሰበብ መሻት………የሚናፍቁት ነገር ማጣት………የሚያዝኑለት ሰው መፈለግ………የማስቀው የሚስቅልኝን ሰው ማሰስ…………ወይም ደግሞ የምር ከአንጀትን ቅጥል አድርጐ የሚያስለቅስ ሰበብ ማነፍነፍ………… ጮሆ የማይወጣ ጋኔልን መለማመጥ………የትኛው የሰውነት ክፍል እንደሆነ ሳይገባ የመቃጠል ስሜት መሰማት………የመንተክተክ……አንዳች የማጥወልወል………የትኛው ውስጥ አነንደሆነ ሳይታወቅ ውስጥ ላይ የማይፈታ ግማድ እንደተተበተበ መሰማት………ሩቅ መመኘት………ከጥበቱ ለመውጣት መፍጨርጨር………እንደገና ወደ ጥበቱ መሸንቆር………ሩቁን በሽንቁር ማጮለቅ………ያሉበትን ብርሀን ከጨለማ ለይቶ አለማስተዋል………ደግሞ የሚጣሉትን ሰው መፈለግ………የሳቀውን ለምን አባህ ትስቃለህ ብሎ መጣላት ማሰኘት………አይዞህ ባዮን ለመደቆስ አይበሉባን ማመቻቸት………መሻትን ማወቅ መሻት የሚፈልጉትን ማጣት ………የፈለጉት ሲሆን የማይፈለገውን ለማድረግ መውተርተር………… የናፈቁትን ሲያገኙ የማያውቁትን መናፈቅ………… ሩቅ መንጐድ ያለፉትን ፈተና እንደገና ለመፈተን መሰናዳት…………የሚያውቁትን የት አባህ ብሎ የማያውቁት ላይ ለመጠምጠም ልብን እና እጅን እንደ አክናፍ መዘርጋት………የሚስቅ ሰው ምፅ አስብሎ የሚያሳዝነን………የሚያለቅስ ሰው አፍን እስክናፍን ከሳቅ የሚያስተናንቀን…………የተወናበደ ውል አልባ ለራስም ስራ ፈት ሀሳብ የሚያሰኝ ስሜት………ምን አይነት ስሜት ነው? ከምንድን ነው የሚመደብ???



@Habeshistan