Get Mystery Box with random crypto!

ካሊድ (ሀበሽስታን) አንድ አንድ ሀሳቦች 3 አለ ደግሞ እንዲህ ያለ ስሜት……… ይይዙት ይጨብጡት | ሀበሻዊ ጥበባት

ካሊድ (ሀበሽስታን)

አንድ አንድ ሀሳቦች 3

አለ ደግሞ እንዲህ ያለ ስሜት……… ይይዙት ይጨብጡት የሚጠፋበት………የምድሩንም የሰማዩንም ሸክ ውስጥ የሚዶል………ኤዲያ አሰኝቶ ሆ ሆ ኸረ ተመስገን ነው የሚያስብል………ቅዝዝ የሚያደርግ………እንደገና ስሜትን አንተክትኮ የሚያገነፍል……… ልብ ጦል የሚያደርግ………አዕምሮን የሚያቦዝዝ………አላስብም የሚያሰኝ እንደገና አላስብምን አብስሎ የሚያሳስብ………ውስጥን የሚያላምጥ………አይነግሩት ስውር ቅኔ አይነገር… ……አያሳዮት አይገለጥ ድብቅ ስውር………… ሲያብሰከስክ ፋታ የማይሰጥ…………ወዲያ ሲሉት ወዲህ………ሂድ ሲሉት ከች………ጠፋ ሲሉት ግርሻት…………ሆነ ሲሉት ካድ………ቀረ ሲሉት ማቆጥቆጥ…………ሲጨብጡት ብናኝ………እንዲህ ያለ ክፉ ስሜት… ……ተውኩህ በቃኸኝ የምን ጭንቀት ሲባል ኤዲያ የምን መድከም ነው ተስፋ ቆራጭ የጌታውን ቅዋ ያልተረዳ ነው። ብሎ ተስፋን በጠፍር አንቀልባ አሸካሚ…………ተስፋ አለኝ ተስፋ አልቆርጥም ትልቅ ጌታ ያለው ትንሽ አይመኝም የተባለ ጊዜ ኡ ኡቴ አልቀረብህም የሚጨበጥ ነገር ሳይኖር ተስፋን ሸክፎ ተሸክሞ የማይመጣን መጠበቅ ምን ይሉታል ባይ…………ትክክሉ ጠፍቶ የልክ ዳና ተሰውሮ ይሄ ነው ልክ የለም ይሄ ነው እያሉ የመቃበዝ ህይወት……የተበተነውን መሰብሰብ እንደገና መበተን………ዝም አይሉት የእግር እሳት የሚያቁነጠንጥ………አይተነፈስ የገደል ማሚቶ ዞሮ ለለፋፊው…………ማን ይሆን ይህንን ቅኔ ፈቺ? ማን ይሆን ይህን ውል አልባ መብሰክሰክ አስካኝ?



@Habeshistan