Get Mystery Box with random crypto!

ካሊድ (ሀበሽስታን) አንድ አንድ ሀሳቦች 2 ……………ጉድ ነው አልኩ ከማነበው መፅሀፍ ላይ እንደ | ሀበሻዊ ጥበባት

ካሊድ (ሀበሽስታን)

አንድ አንድ ሀሳቦች 2

……………ጉድ ነው አልኩ ከማነበው መፅሀፍ ላይ እንደ መባነን ብዬ ከወሰደኝ የሀሳብ ማዕበል ተፍጨርጭሬ ለመንቃት እየሞከርኩ አይኔን ሞዠቅ አድርጌ ዙሪያ ገባውን ቃኘት አደረኩ ቀና ብዬ ግድግዳ ላይ ተሰቅሎ ዝንት አለም ሰዐታትን እየቆጠረ ለአመታት ሲያስረክብ እዚህ የደረሰውን የግድግዳ ሰዐት አጨንቁሬ ተመለከትኩት ችግሩ ከአይኔ ይሁን ወይ ሰዐቱ በስተርጅና መሮጥ ጀምሮ ወይ እርጅናው ይብሱኑ ተጫጭኖት መርሳት ጀምሮ እንደቆመ ቀርቶ ባላውቅም ከቀኑ ስድስት ሰዐት ከአስር ደቂቃ ይላል።

መፅሀፌን ያቆምኩበትን ገፅ አይቼ ከከደንኩ በኋላ ጋደም ካልኩበት ተነስቼ ባለማመን ደጋግሜ ያንን አሮጌ ሰዐት አየሁት ያው ነው እየጨመረ ይሄዳል ደቂቃው ይገርማል እርጅና የማይጫጫነው ፍጡር በቃኝ ልረፍ የማይባልበት ህይወት የሰዐት ህይወት ።

እሁድን ሳላጣጥማት እንዴት ነው ሰዐቱ እንደዚህ የሚነጉደው? ብዬ እራሴ ጋር እያጉረመረምኩ የያዝኩትን መፅሀፍ ቦታው ላይ መልሼ ሽቅብ እየተንጠራራሁ ወደውጭ ወጣሁ ። የፀሀይዋን ነፀብራቅ አይኔ እሰኪላመደው ትንሽ ከተጨናበስኩ በኋላ የግቢውን ግራ ቀኝ ስመለከት የግቢው ግራም ቀኝም ላይ ሰው ተቀምጧል

የግቢው ቀኝ እረድፍ ቀኝ አዝማች እንደማለት ነው አጭር ፀጉሩን እንደ ነጠላ እየቋጨ አንዴ ፈገግ አንዴ ኮስተር እንደገና የያዘውን ስልክ በሁለት እጁ ጨበጥ ለቀቅ ማድረጉን የተያያዘው ዘመዴ ነው ዝምድናው ማን ማንን ቢወልድ እንደሆነ ባላውቅም ዘመድህ ነው አሉኝ ዘመዴ ነህ ብዬ ተቀበልኩት። እንኳንስ ዘመድን ወልደው የለም የኔ አይደለህም ብለው ያላመቱንስ ልጅ ነገሩ ተፋፍሞ ቁርጥ ሲመጣ የአብራኬ ክፋይ ብለው ያመኑ ስንቶቹ ናቸው

የግቢው ግራ እረድፍ ግራ አዝማች ደግሞ የለመደባት ማስቲካ ማኘክ ስለቀረባት ወይም ፆሙ ገና በዚህ ሰዐት አድክሟት ጨጓራዋ ምን ኩነሻል ሴትዮ ብይ እንጅ በአማኑ ቀን ክፉ አስለምደሽኝ እርምሽን ብትፆሚ ተላጥኩ እኮ እያላት በየሰከንዱ የምታዛጋዋ ያመንኳት ዘመዴ ልክ እንደ ቀኝ አዝማቹ እሷም ስልኳን እየነካካች ፈገግ ኮስተር ትላለች።

እህ… እህ አልኩ ተቀላቅያለሁ ለማለት ቀና ያለ የለም እህ ለውጥ የለውም ብዬ የጌታየን ሰላምታ ሰጠሁ በቸልታ መለሱልኝ ይሄንንስ ማን አየበት ብዬ በሆነ ማንቆርቆሪያ ነገር ውሀ ይዤ ከፊታቸው ተቀመጥኩ ፊት አውራሪ እንደማለት ነው።

ምንድን ነው ሰሞኑን እንደዚህ እልል ሳይባል ከስልካቹ ጋር ያጋባችሁ አልኩ በየተራ እየተመለከትኩ ሁለቱንም እ…እ…እ… አለ ቀኝ አዝማች እ…እ…እ… ብሎ ዝም አለ ምን ታልጐመጉማለህ አትናገርም እንዴ አልኩት ቆጣ ብዬ ግን ምን አስቆጣኝ? ስላልመለሰልኝ ነው ወይስ ችላ ማለቱ ነው?

እ…እ…እ… ባክህ ሰላት ተከለከለ ። ማለት አለ አስሬ ከንፈሩን እየላሰ እና በአንድ እጁ አጭር ፀጉሩን እንደ ነጠላ እየቋጨ ማለት ትምሮ ቤት አትሰግዱም መውጣትም አይቻልም ውስጥም መስገድ አይቻልም አሉ አለኝ። እነማን ናቸው አትሰግዱም ያሉ? አልኩት የለም ሳይመልስልኝ ወደ ስልኩ ተመልሶ ገብቷል።

አንቺሰ ግራ አዝማች ምንድን ነው ስልክሽ ጋር ያጣበቀሸ አልኳት እ…እ…እ… አለች ወየው ጉዴ ቆይ ይሄ እ…እ…እ… መንደርደሪያ ነው ወይስ ፈርድ ሆነ ከንግግር በፊት? አልኩ ቆጣ ብዬ ምን መሰለህ ሀበሽ አለች እ… አልኳት ወይኔ እኔም በአንዴ ተጋባብኝ ይሄ እ ለነገሩ ቢጋባብኝ ምን ይገርማል እ እታችን እየተጋባብን አደል ከእርምጃ ይልቅ እያቃሰትን የምንኖር ለመናገር ቅስቻ ለመሄድ ቅስቻ አቃሳች ሂወት።

የመጀመሪያው ምን መሰለህ የሆነ ያልጨረሰችውን ወሬ እስክትጨርስ ቆይ ጠብቀኝ አይነት ስለነበር ምን መሰለህ ሀበሽ አለች ደግማ ትኩረቷን ለመሰብሰብ እየተጣጣረች ሂጃባችሁን አውልቁ አሉን አለች።እነማን ናቸው ሂጃብ አውልቁ ያሉ አልኳት እሷም የለችም ወደማላውቀው አለም በስልኳ ተሳፍራ በራለቸ።

ነገሩ ቢገባኝም ከነሱ አፍ ለመስማት የፈለኩትን ጉዳይ ሳልሰማ ከቅርብ እርቀት የሚገኝ መስጂድ አዛን ያስተጋባው…………………

………………አዛኑ አልቆ ትንሽ ካምሰለሰልኩ በኋላ ባቀረብኩት ውሀ ኡዱዕ አድርጌ ጨራረስኩ በል ተነስ ቀኝ አዝማች እንስገድ አልኩ አንቺም ተነሺ አልኳት በተቀመጠችበት ከላይ እስከታች እየገረመምኳት የለበሰችው ጥቁር ጉርድ ቀሚስ ከሰውነቷ ተጣብቆ እና ጉልበቷን ልከልለው አልከልለው እያለ መወዛገቡን ከላይ ያደረገችው ወይ በእርሷ አስተሳሰብ አውልቂ የተባለችው ሂጃብ ተንሸራቶ ለትልቁ ፀጉር ማስያዣዋ እንጂ አላማው ለፀጉሯ እንዳልሆነ ይመስል ፀጉር ማስያዣዋን ይዞ ተንጠልጥሎ ልውደቅ አልውደቅ ይላል።

ከእርሷ መለስ ብዬ ተነስ እንጂ እንሂድ አልኩት እጁን እንደማወናጨፍ ብሎ ባክህ ሂድ ለራሴ ተናድጃለሁ አንተ ደግሞ ትጨቃጨቀኛለህ ብሎኝ ፀጉሩን እያሻሸ አቀረቀረ።

ብዙም ሳይገርመኝ ለመሄደ በሩን ከከፈትኩ በኋላ መለስ ብዬ ቅድም እኮ ጠይቄህ አልመለስክልኝም እና ማን ነው ሰላቱን የከለከለው አልከኝ ? አልኩት ምንም ምላሽ አልሰጠኝም አንቺስ ግራ አዝማች አልኳት ዝም አለች ቄሱም ዝም መፅሀፉም ዝም ይሄ ይሆን እንዴ? እያልኩ ወጥቼ ወደመስጅድ በቀስታ መራመድ ጀመርኩ


ግን ግን ማን ነው ሰላት ከልካዮ? ለምንስ ከለከለ?
እሺ ማነው ሂጃብ አስወላቂው? ለምንሰ አውልቁ አለ? ሂጃብሰ ምንድን ነው?

የአዕምሮዬ ድርብርብ ድሪቶ ጥያቄዎቸ ናቸው ለመመለስ አዕምሮዬ ቢዘጋጅም መልሱ የተገለጠ መፅሀፍ ቢሆንም ሙግት ውስጥ ተደነጐረ።

ቀደም ብዬ ከቤት ስወጣ ያጤንኳት ግራ አዝማች ዘመዴ በአዕምሮዬ ተመላለሰች አለባበሷ እና ስነ ምግባሯ በእዝነ ህሊናዬ ተንሸራሸረ

ቀድሞ ለተንሸራተተ ሂጃብ ሂጃብሽን አውልቂ መባል ቆይ ለምንድን ነው የገረማት? መጀመሪያ ከፍ አድርገው ሲያስለብሷት ቀደም ብለው ፀጉርሽ እኮ ሲያምር ብለው በስሱ ሲያስከፍቷት ቀጥሎ አረ አውልቂው እንደሚመጣ አላስተዋለችውም ነበር ነው? ፈልጋ ለማውለቅ እየዳዳት ያለውን ሂጃብ ማን ይሆን ላግዝሽ እንተጋገዝና አውልቂው ብሎ ያናደዳት? ማን ነው እህቴን የተዳፈራት ውስጧ እራሷ ናት ወይስ አውልቂው ባዮ ነው? አውልቂው ባዮ ምን አጠፋ የወለቀ ነገር ወይ ጌጥ ወይ መለያ አይሆንም ለሀገርም ገፅታ ለሴኩላሩም ብዙም ምቾት አይሰጥም ብሎ በለሆሳስ ስለተናገረ ነው።

ልክ ነው እኮ ግንጥል ጌጥ ሆኗል  ሂጃብ! ማውለቅ ነበር ተብሎ የሚደረግ ። ታዲያ ማውለቁን ላግዝ ባለ እንዴት ተናደደችበት? ማን ነው እህቴን ያስከፋት? ሂጃብሽን አውልቂ ብሎ? ቅርፅሽ እኮ የሰጠ ነው ፓ ብለው አድንቀው በገዛ ልብሷ በገዛ ፈቃዷ ሲያጣብቋት መርሀባ ብላ ተጣብቃ ዛሬ ደግሞ አጣባቂው አዝኖላት ብታወልቂው እኮ እንደዚህ ላስጨነቀሽ ብሎ ባዘነላት ለምንድን ነው ያዘነችው? ማን ነው እህቴን ያስከፋብኝ? ብዙም ለነገሮች አትጨናነቂ እራስሽን ማስጨነቅ ጥሩ አይደለም ደግሞ እንደዚህ ቆንጆ ሆነሽ የምን መሸማቀቅ ለቀቅ በይ አይን አፋርነት ባክሽ የፋራ ነው ብለው አደቧን ከላዯ ላይ አጣጥበው እጣቢውን አርቀው ደፍተው ጥለዋት ከሄዱ በኋላ ቢበርዳት ማን ነው ተጠያቂው አጣቢው ነው? ታጣቢው? ማን ነው እህቴን ግራ አዝማቼን ያናደደብኝ?


ቀኝ አዝማች ዘመዴ ግራ አዝማቿን ዘመዴን በግድ ከአዕምሮዬ የሀሳብ ፈለግ በጥሶ እራሱን የሀሳብ ፈለግ አድርጐ ተካ