Get Mystery Box with random crypto!

🦋እራስን ፍለጋ🦋🦋67

የቴሌግራም ቻናል አርማ erasnflega — 🦋እራስን ፍለጋ🦋🦋67
የቴሌግራም ቻናል አርማ erasnflega — 🦋እራስን ፍለጋ🦋🦋67
የሰርጥ አድራሻ: @erasnflega
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.11K
የሰርጥ መግለጫ

ቢራቢሮዎች ነን ኑ አብረን እንብረር ።ለራሳችን የሚያስፈልገንን እየወሰድን ትውልድን እንቃኝ ወጣትነታችንን ሳንቆጭበት በደስታ እናሳልፍ ኑ ለትውልድ አብረን እንስራ
ይቀላቀሉን
👇👇👇
@erasnflega77
ይጫኑት ያገኙናል ሌላ ስንከተል ከራሳችን ጋር እንዳንተላለፍ

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-01 02:08:36 ነገ final የምትጀምሩ fresh ተማሪዎች
Arbaminch University
Bahir Dar University
..........
እና ጀምራችሁ በዝህ ሳምንትም የምትቀጥሉ
Jimma University
Wolkite University
........

መልካም ፈተና እንድሆን እንመኛለን ።

@erasmflega
319 views23:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 08:35:30 መዘጋጀት/preparation

➜ስኬት ለሚዘጋጁ ሰዎች ሳትሆን ለተዘጋጁ ናት።እየተዘጋጁ ከሚሮጡ ይልቅ ተዘጋጀተው የሚሮጡ በህይወት የላቀ ስኬትና ደስታ አላቸው።

❖ብዙዎች ወይም ከመቶ 80% የሚያህሉ አብዛኛውን ቁጥር የያዙ ሰዎች የህይወታቸውን ሩጫ የሚሮጡት ተዘጋጀተው ሳይሆን እየሮጡ ነው የሚዘጋጁት ይህ ደግሞ አላስፈላጊ ዋጋ መክፈልና መባከን ያመጣል።በባህላችን ወግ የተለመደ አባባል አለ <<ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ሲሮጡ ይፈታል>>የሚባል አባባል ህይወታችሁ ሲሮጡ የታጠቁት እንዳይሆን ከመሮጣችሁ በፊት መታጠቅ ያለባችሁን መታጠቅ ማጥበቅ ያለባችሁን ማጠበቅ አለባችሁ ይህ ደግሞ ነጋችሁን ቀላልና ውጤታማ ያደርገዋል።

ነገ ምንም ከማድረጋችሁ በፊት ለምታድርጉት ወይም ለምታቅዱት ማንኛውም ጉዳይ በቂ የሆነ ዝግጅት ማድረጋችሁን እርግጠኛ ሁኑ።ስኬት ዕቅዶችን እየጀመሩ ማቆም አይደለም።ጀምሮ አለመጨረስን የመሰለ ነገ የሚያበላሽ

❖የመጨረስህ አቅም ያለው ዝግጅትህ ውስጥ ነውና።ስትዘጋጅ ምንም አትጀምር።ለነገ ዛሬ ተዘጋጀ ዛሬ የተሰጠህ ነገን እንድትሰራበት ነውና።እንዳለፉት አመታቶች ለነገ ነገ አትዘጋጀ ዛሬ ያልተዘጋጅህላቸው ነገዎች ከዛሬ በምንም አይሻሉም።የብዙዎች በሽታ ለነገ ነገ መዘጋጀታው ነው።
269 views05:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 08:33:30 አቡነ ጴጥሮስ የተሰዎት ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም ነው።ታላቁ ባለቅኔና የተውኔት አዘጋጅ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ዘመን ተሻጋሪ የሆነችውን “ጴጥሮስ ያችን ሰዓት” የምትለዋን ግጥም የፃፈው አንድ ቀን ምሽት ከማዘጋጃ ቤት ሲወጣ ባየው ትዕይንት ምክንያት ነው።
ነገሩ እንዲህ ነው።
ፀጋዬ ገ/መድህን ከማዘጋጃ ቤት እንደወጣ ቁልቁል ወደ አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ሲያመራ አንድ ጀብራሬ (በሎሬቱ አነጋገር) ከአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ላይ ሸንቱን ሲሸና ተመለከተ።ፀጋዬም በደም ፍላት ወደ ጀብራሬው ተንደረደረ። ጀብራሬው ግን “አንተ ድንጋይ እሸናብሃለሁ።ድንጋይ ነህ…ድንጋይ ነህ...” እያለ በሐውልቱ ላይ ይሸናል።በዚህ ሰዓት ነበር ሎሬቱ“ጴጥሮስ ድንጋይ አይደለም”ብሎ ጀብራሬውን በደም ፍላት ዘሎ ያነቀው።ከዚያም አብረውት የነበሩት ሰዎች ገላገሉትና እየተብሰከሰከ አራት ኪሎን ተሻግሮ ቀበና ገባ።ማታውን አልተኛም አነሆ“ጴጥሮስ ያችን ሰዓት” የምትለዋን ግጥምና ኑዛዜ ሲጭር አደረ።

ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ «አቡነ ጴጥሮስ እንዴት ሞቱ?» ሲል ጣልያናዊ ጋዜጠኛን ጠይቋቸው እርሳቸውም የሚከተለውን ተናግረዋል።«አቡነ ጴጥሮስ የተገደሉ ዕለት እዚያው ነበርኩ።መጀመሪያ በእጃቸው ይዘውት የነበረውን መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ተሳለሙት።ቀጥለውም የያዙትን መስቀል አማትበው ሕዝቡን ባረኩ።የኪሳቸውንም ሰዓት አውጥተው ካዩ በኋላ መልሰው ከኪሳቸው ከተቱት።ወዲያው ወታደሮች በእሩምታ ተኩሰው ገደሏቸው።
ሂያጅ፡ ተሳፋሪ፡ ሰዎች፡ ከሆናችሁ
ኧረ፡ ለመቼው፡ ቀን፡ ቤት፡ ትሠራላችሁ።
መልሱን፡ ስጡት፡ እንጂ፡ ለምን፡ ዝም፡ አላችሁ
ተጣርቶ፡ ተጣርቶ፡ ያ፡ ሰው፡ ሄደላችሁ።
አቡነ ጴጥሮስ ለእናት ሀገራቸው ኢትዮጵያ ክብር ሲሉ የሞትን ፅዋ ተጎነጩ።
ምንጭ፦የኢትዮጵያና የኢጣሊያ ጦርነት በጳውሎስ ኞኞ
236 views05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 06:37:14 አንዲት ሴት የገዛችውን የሱፐርማርኬት
እቃ በጋሪ ከትታ ወደ መክፈያው ተጠጋች
ቦርሳዋን ስትከፍተው ውስጡ ሪሞት ኮንትሮል ይዛ ስለተመለከተ ካሼሪው
አላስቻለውም ጠየቀ "ሁልጊዜ የቲቪ ሪሞት በቦርሳሽ ይዘሽ ነው የምትወጭው?"
"አይ ባለቤቴ ወደ ሱፐርማርኬት አብረን
እንሂድ ስለው ኳስ አያለሁ አልሄድም ስላለኝ ተናድጄ ይዤበት ወጥቼ ነው።
የታሪኩ ጨመቅ(ሞራል)ሚስትህን ሁልጊዜ መሄድ ወደምትፈልግበት አጅበህ ተከተላት...ታሪኩ አላለቀም
ይሄን እየተጨዋወቱ ሳለ ካሼሪው ስቆ እቃዎቹን ወደ መደርደርያው መመለስ
ጀመረ።
ምነው?ምን እያደረግኽ ነው?
ባልሽ ሳይናደድብሽ አይቀርም አሁን በዚህች ደቂቃ ATM ካርድሽን አዘግቶታል የታሪኩ ጨመቅ(ሞራል) የባለቤትሽን ስሜት አክብሪለት ...ታሪኩ አላለቀም
ሚስት ሆዬ ወድያው ከቦርሳዋ የባሏን ATM ካርድ አውጥታ አቀያይራ ሞከረች
አልታገደም። የታሪኩ ጨመቅ(ሞራል) የሴት ልጅን ብልሃት አሳንሰህ አትመልከት
...ታሪኩ አላለቀም
ካርዱ ከተለዋወጠ(swipe) በኋላ ማሽኑ ፒን ኮድ ጠይቆ ትክክለኛው (የባሏ) ስላልገባለት አዲስ ፒን ወደ ስልኩ በመሴጅ ላከ
"እባክዎ ወደ ስልክዎ በመልእክት የላክነውን ፒንኮድ ያስገቡ።ደግመውም
በትክክል ማስገባትዎን ያረጋግጡ" የሚል መልስ ሰጠ።
የታሪኩ ጨመቅ(ሞራል)ወንድ ልጅ ዝንጉ ሲሆን ማሽኑ ይታደገዋል....ታሪኩ
ይቀጥላል
ሚስት ሳቅ ብላ ከቦርሳዋ የሜሴጅ ድምፅ የሚያሰማ ሌላ ስልክ አውጥታ ፒኑን በማስገባት ከፈለች።ለካ እየገበየች ሳለ ባሏ እየደወለ ሪሞቱን እንዳይነዘንዛት
ስልኩንም ይዛበት ነው የወጣችው
የምትፈልገውን እቃ ተረጋግታ "ረብጣውን እየመዠረጠች" ገብይታ ስታበቃ ወደ
ቤቷ ተመለሰች የታሪኩ ጨመቅ(ሞራል) የተናደደች ሚስትህን አትፈታተናት ጉዳቱ ላንተው ነው...ታሪኩ ይቀጥላል
ሚስት ቤት ስትደርስ ባል ማስታወሻ
ፅፎላት መኪናውን አስነስቶ ሄዷል
"ውዴ ስልኬን ብፈልገው አጣሁት ቢሮ ጥዬው ሳልመጣ አልቀርም ላመጣው
ሄጃለሁ። ስጨርስ ኳስ ለማየት ከጓደኞቼ ጋር ማመሻሸቴ አይቀርም እንዳትቆጪ።
የምትፈልጊው ነገር ካለ ደውይ" የታሪኩ ጨመቅ(ሞራል) ባለቤትሽን የት ወጣህ ገባህ ብለሽ አትነዝንዥው
በተለይ ቅዳሜ ማታ!!


@erasnflega
257 views03:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 14:47:07 የዛሬው የኔ ጀግና ባለታሪካችን
356 viewsedited  11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 04:27:31 ስለ መፍቀድ የቀጠለ...
ውሃን ከስኳር ጋር ስታዋህደው ጥፍጥናው ጣፋጭ ሲሆን ከጨው ጋር ስትቀላቅለው የጨውን ጣዕም ይሰጣል፣ የውሃ ባህሪ እንዲዋሃደው በፈቀደው ልክ የተቀያየረ ይሆናል።
ያልነቃውበትን ነገር ሳስብ ብዙ ጊዜዬን የሰጠውት ነገር ከእኔ ጋር ውህድ እንደሚፈጥር ነበር። ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ይል የለ የሀገሬ ሰው ሲተርት ውሎዬን እንደምመስ አሁን በጣም ገብተኛል። ውሎዬን ፍቃዴን ሰጥቼው ያደረኩት ነገር ነው አንጂ በሆነ መንገድ ደጋግሜ ማለፌ አይደለም አልያም ቸርች መምጣቴም ለካ አይደለም እንደዛ ከሆ ዮሴፍ ይስቅብኛል ዮሴፍ በአምሎኮ ስፍራ ተብሎ በሚጠራው ቤትልሄም አይደለም ያለው በጶጢፋራ ቤት በባርነት ነበር ሳስበው የዮሴፍ ልብ ከዚህ በፊት ለማይሆን ለሴት ፍቅር የተሸነፈ ቢሆን ኖሮ ገና ከጅምሩ የጶጢፋራን ባለቤት እርሱ ነበር መተናኮል የሚጀምረው። ጦጣ ለሙዝ እንደምትቋምጥ በልቤ ፈቃዴን የተቆጣጠረው ነገር ነው ለካ ለምን እንደምቋምጥ የሚገፋኝ።
ልብ ምን ያደረገውን ብቅል ያወጣዋል ነው የሚለው የሀገሬ ሰው በልብ ሞልቶ ከተረፈው ነብስ የምትናገረው ፈቃዴን የተቆጣጠረውን ነገር በየጊዜው ማወቅ እንዳለብኝ አሁን እየገባኝ መቷል አትርፍ ባይ አጉዳይ እንዳልሆን መጣር አለብኝ ቅዱስ ጳውሎስ ሮጬ ሮጬ የተጣልኩ እንዳልሆን እንዳለ ፈቃዴን ለምንና ለማን ማስገዛት እንዳለብኝ ከፊት ይልቅ አሁን እጅግ እየተረዳው መጥቻለው...
359 views01:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 04:27:31 መፍቀድ:-
ቀድሞን ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥሎ ማልቀስ...ይላል ያገሬ ሰው።አንድን ነገር እሺ ለማለት በልብ አስቦ ቢሆን የነገን ነገር፣ ማንኛውም ግንኙነት ጥሩ ያደርገዋል አሰማምቶ ብቻ ሳይሆን መጥኖ አስቦ ነገን ሩቅ ተመልክቶ እሺ ማለት። በዚህ ጊዜ እሺ ማለት የቀለለ ነገር እየሆነ ነው ለብዙ ነገር ሳናቅ እሺ እያለን ነው በፊት ምንጠየፋቸውን ነገሮች አሁን በቀላሉ ለማድረግ ቀላል ሆነው ልባችንን ሳይቆረቁሩ መሰስ ብለው በእኛ ዘንድ ድርጊት ሆነው ይከወናሉ። ተቀራኒ ሆነን አለን እቢ ምንላቸውን አሺ እሺ ማለት ያለብንን ደግሞ እንግዳ ሆነውብን እቢ እያልናቸው ነው። ውድ ነገሮች ቀለው ዋጋቸው በረከሱ ነገሮች ተተክተዋል ይህ ሁሉ ነገር ለምን ሆነ ብዬ ሳስብ ፈቃዳችን ተወርሷል አንዳንዶቻችን እንቢ ለማለት እንኳ አቀም አጥተናል። ቤት ሰርቶ የተቀመጠን ነገር እንቢ ለማለት እኮ ይከብዳል። እናስተውል በልባችን ጓዳ የገቡ ነገሮች የፈቃዳችንን ነገር መቆጣጠራቸው አይቀርም ወይ! እንቢ ለማለት እንኳ ድፍረት ስለሚያሳጡን ከወዲሁ ነቅተን ክፋትን መጋበዛችንን እናቁም።ተባረኩ
315 views01:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 06:15:29 #አንድም ቀን #ሳይበድለኝ......."
በ156 ዓ.ም በሰርኔስ ከተማ ከግንድ ጋር ታስሮ የተቃጠለው የ86 ዓመት አዛውንት ነበር #ፓሊካርፕ ፡፡
ጌታ ኢየሱስን እንዲክድ ለመጨረሻ ጊዜ ከመቃጠሉ በፊት ለቀረበት ጥያቄ እንዲህ ነበር ያለው" ይሔን ሁሉ ዘመን ክርስቶስን ሳገለግለው አንድም ቀን በድሎኝ አያውቅም......
ታድያ በዚህ እድሜዬ ንጉሴን ምን አደረገኝ ብዬ እክደዋለው"? (ምንጭ፡ ከፍኖተ መንግስት መጽሐፍ ገፅ 58)
@erasnflega jo in
285 views03:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 06:15:29 የምትሆነው የመረጥከውን ነው!

ከመስታውት ፊት ለፊት ቆመህ በአንተ ላይ ያሉ በሺዎች የሚቀጠሩ ችግሮችን ወይም ግድፈቶችን ማውጣት ትችላለህ፤ ወይም ደግሞ በመስታውት ውስጥ እያየህ ጥሩ ስሜት ይሰማኛል፣ ጤናዬ የተጠበቀ ነው፣ ፈጣሪ ያደለኝ ሰው ነኝ እያልክ ልታስብ ትችላለህ። እኔ ራሴን ለማየት የምመርጠው በዚህ መንገድ ነው። Isla Fisher

ፈጣሪ ባጎናፀፈን ነፃ ፍቃድ ምክንየት ሰው የሚሆነው የመረጠውን ነው። እናም የፈለጋችሁትን መምረጥ ትችላላችሁ! ምን ለመሆን መረጥን???

@eras flega
@erasnflega
253 views03:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 06:15:29 ትልቁ ነጥብ ስህተት መስራትህ አይደለም ወይ መውደቅህ ጥፋት ማጥፋትህ አይደለም ግን መልሰህ ካልተነሳህ ነው፤ ልብስም እኮ ይቆሽሻል ግን አጥበህ መልሰህ ትለብሰዋለህ።

አንተም ስትሳሳት ራስህ ላይ አትጨክንበት፤ ያጠፋ ሰው አንዴ ነው የሚቀጣው፤ በየቀኑ "እኔኮ አልረባም" እያልክ ራስህን አትውቀሰው! ልብሱ ከታጠበ አንተ የማትለወጥበት ምክንያት የለም!

@erasnflega
228 views03:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ