Get Mystery Box with random crypto!

መፍቀድ:- ቀድሞን ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥሎ ማልቀስ...ይላል ያ | 🦋እራስን ፍለጋ🦋🦋67

መፍቀድ:-
ቀድሞን ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥሎ ማልቀስ...ይላል ያገሬ ሰው።አንድን ነገር እሺ ለማለት በልብ አስቦ ቢሆን የነገን ነገር፣ ማንኛውም ግንኙነት ጥሩ ያደርገዋል አሰማምቶ ብቻ ሳይሆን መጥኖ አስቦ ነገን ሩቅ ተመልክቶ እሺ ማለት። በዚህ ጊዜ እሺ ማለት የቀለለ ነገር እየሆነ ነው ለብዙ ነገር ሳናቅ እሺ እያለን ነው በፊት ምንጠየፋቸውን ነገሮች አሁን በቀላሉ ለማድረግ ቀላል ሆነው ልባችንን ሳይቆረቁሩ መሰስ ብለው በእኛ ዘንድ ድርጊት ሆነው ይከወናሉ። ተቀራኒ ሆነን አለን እቢ ምንላቸውን አሺ እሺ ማለት ያለብንን ደግሞ እንግዳ ሆነውብን እቢ እያልናቸው ነው። ውድ ነገሮች ቀለው ዋጋቸው በረከሱ ነገሮች ተተክተዋል ይህ ሁሉ ነገር ለምን ሆነ ብዬ ሳስብ ፈቃዳችን ተወርሷል አንዳንዶቻችን እንቢ ለማለት እንኳ አቀም አጥተናል። ቤት ሰርቶ የተቀመጠን ነገር እንቢ ለማለት እኮ ይከብዳል። እናስተውል በልባችን ጓዳ የገቡ ነገሮች የፈቃዳችንን ነገር መቆጣጠራቸው አይቀርም ወይ! እንቢ ለማለት እንኳ ድፍረት ስለሚያሳጡን ከወዲሁ ነቅተን ክፋትን መጋበዛችንን እናቁም።ተባረኩ