Get Mystery Box with random crypto!

ስለ መፍቀድ የቀጠለ... ውሃን ከስኳር ጋር ስታዋህደው ጥፍጥናው ጣፋጭ ሲሆን ከጨው ጋር ስትቀላቅ | 🦋እራስን ፍለጋ🦋🦋67

ስለ መፍቀድ የቀጠለ...
ውሃን ከስኳር ጋር ስታዋህደው ጥፍጥናው ጣፋጭ ሲሆን ከጨው ጋር ስትቀላቅለው የጨውን ጣዕም ይሰጣል፣ የውሃ ባህሪ እንዲዋሃደው በፈቀደው ልክ የተቀያየረ ይሆናል።
ያልነቃውበትን ነገር ሳስብ ብዙ ጊዜዬን የሰጠውት ነገር ከእኔ ጋር ውህድ እንደሚፈጥር ነበር። ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ይል የለ የሀገሬ ሰው ሲተርት ውሎዬን እንደምመስ አሁን በጣም ገብተኛል። ውሎዬን ፍቃዴን ሰጥቼው ያደረኩት ነገር ነው አንጂ በሆነ መንገድ ደጋግሜ ማለፌ አይደለም አልያም ቸርች መምጣቴም ለካ አይደለም እንደዛ ከሆ ዮሴፍ ይስቅብኛል ዮሴፍ በአምሎኮ ስፍራ ተብሎ በሚጠራው ቤትልሄም አይደለም ያለው በጶጢፋራ ቤት በባርነት ነበር ሳስበው የዮሴፍ ልብ ከዚህ በፊት ለማይሆን ለሴት ፍቅር የተሸነፈ ቢሆን ኖሮ ገና ከጅምሩ የጶጢፋራን ባለቤት እርሱ ነበር መተናኮል የሚጀምረው። ጦጣ ለሙዝ እንደምትቋምጥ በልቤ ፈቃዴን የተቆጣጠረው ነገር ነው ለካ ለምን እንደምቋምጥ የሚገፋኝ።
ልብ ምን ያደረገውን ብቅል ያወጣዋል ነው የሚለው የሀገሬ ሰው በልብ ሞልቶ ከተረፈው ነብስ የምትናገረው ፈቃዴን የተቆጣጠረውን ነገር በየጊዜው ማወቅ እንዳለብኝ አሁን እየገባኝ መቷል አትርፍ ባይ አጉዳይ እንዳልሆን መጣር አለብኝ ቅዱስ ጳውሎስ ሮጬ ሮጬ የተጣልኩ እንዳልሆን እንዳለ ፈቃዴን ለምንና ለማን ማስገዛት እንዳለብኝ ከፊት ይልቅ አሁን እጅግ እየተረዳው መጥቻለው...