Get Mystery Box with random crypto!

መዘጋጀት/preparation ➜ስኬት ለሚዘጋጁ ሰዎች ሳትሆን ለተዘጋጁ ናት።እየተዘጋጁ ከሚሮጡ ይል | 🦋እራስን ፍለጋ🦋🦋67

መዘጋጀት/preparation

➜ስኬት ለሚዘጋጁ ሰዎች ሳትሆን ለተዘጋጁ ናት።እየተዘጋጁ ከሚሮጡ ይልቅ ተዘጋጀተው የሚሮጡ በህይወት የላቀ ስኬትና ደስታ አላቸው።

❖ብዙዎች ወይም ከመቶ 80% የሚያህሉ አብዛኛውን ቁጥር የያዙ ሰዎች የህይወታቸውን ሩጫ የሚሮጡት ተዘጋጀተው ሳይሆን እየሮጡ ነው የሚዘጋጁት ይህ ደግሞ አላስፈላጊ ዋጋ መክፈልና መባከን ያመጣል።በባህላችን ወግ የተለመደ አባባል አለ <<ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ሲሮጡ ይፈታል>>የሚባል አባባል ህይወታችሁ ሲሮጡ የታጠቁት እንዳይሆን ከመሮጣችሁ በፊት መታጠቅ ያለባችሁን መታጠቅ ማጥበቅ ያለባችሁን ማጠበቅ አለባችሁ ይህ ደግሞ ነጋችሁን ቀላልና ውጤታማ ያደርገዋል።

ነገ ምንም ከማድረጋችሁ በፊት ለምታድርጉት ወይም ለምታቅዱት ማንኛውም ጉዳይ በቂ የሆነ ዝግጅት ማድረጋችሁን እርግጠኛ ሁኑ።ስኬት ዕቅዶችን እየጀመሩ ማቆም አይደለም።ጀምሮ አለመጨረስን የመሰለ ነገ የሚያበላሽ

❖የመጨረስህ አቅም ያለው ዝግጅትህ ውስጥ ነውና።ስትዘጋጅ ምንም አትጀምር።ለነገ ዛሬ ተዘጋጀ ዛሬ የተሰጠህ ነገን እንድትሰራበት ነውና።እንዳለፉት አመታቶች ለነገ ነገ አትዘጋጀ ዛሬ ያልተዘጋጅህላቸው ነገዎች ከዛሬ በምንም አይሻሉም።የብዙዎች በሽታ ለነገ ነገ መዘጋጀታው ነው።