Get Mystery Box with random crypto!

አቡነ ጴጥሮስ የተሰዎት ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም ነው።ታላቁ ባለቅኔና የተውኔት አዘጋጅ ሎሬት | 🦋እራስን ፍለጋ🦋🦋67

አቡነ ጴጥሮስ የተሰዎት ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም ነው።ታላቁ ባለቅኔና የተውኔት አዘጋጅ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ዘመን ተሻጋሪ የሆነችውን “ጴጥሮስ ያችን ሰዓት” የምትለዋን ግጥም የፃፈው አንድ ቀን ምሽት ከማዘጋጃ ቤት ሲወጣ ባየው ትዕይንት ምክንያት ነው።
ነገሩ እንዲህ ነው።
ፀጋዬ ገ/መድህን ከማዘጋጃ ቤት እንደወጣ ቁልቁል ወደ አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ሲያመራ አንድ ጀብራሬ (በሎሬቱ አነጋገር) ከአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ላይ ሸንቱን ሲሸና ተመለከተ።ፀጋዬም በደም ፍላት ወደ ጀብራሬው ተንደረደረ። ጀብራሬው ግን “አንተ ድንጋይ እሸናብሃለሁ።ድንጋይ ነህ…ድንጋይ ነህ...” እያለ በሐውልቱ ላይ ይሸናል።በዚህ ሰዓት ነበር ሎሬቱ“ጴጥሮስ ድንጋይ አይደለም”ብሎ ጀብራሬውን በደም ፍላት ዘሎ ያነቀው።ከዚያም አብረውት የነበሩት ሰዎች ገላገሉትና እየተብሰከሰከ አራት ኪሎን ተሻግሮ ቀበና ገባ።ማታውን አልተኛም አነሆ“ጴጥሮስ ያችን ሰዓት” የምትለዋን ግጥምና ኑዛዜ ሲጭር አደረ።

ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ «አቡነ ጴጥሮስ እንዴት ሞቱ?» ሲል ጣልያናዊ ጋዜጠኛን ጠይቋቸው እርሳቸውም የሚከተለውን ተናግረዋል።«አቡነ ጴጥሮስ የተገደሉ ዕለት እዚያው ነበርኩ።መጀመሪያ በእጃቸው ይዘውት የነበረውን መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ተሳለሙት።ቀጥለውም የያዙትን መስቀል አማትበው ሕዝቡን ባረኩ።የኪሳቸውንም ሰዓት አውጥተው ካዩ በኋላ መልሰው ከኪሳቸው ከተቱት።ወዲያው ወታደሮች በእሩምታ ተኩሰው ገደሏቸው።
ሂያጅ፡ ተሳፋሪ፡ ሰዎች፡ ከሆናችሁ
ኧረ፡ ለመቼው፡ ቀን፡ ቤት፡ ትሠራላችሁ።
መልሱን፡ ስጡት፡ እንጂ፡ ለምን፡ ዝም፡ አላችሁ
ተጣርቶ፡ ተጣርቶ፡ ያ፡ ሰው፡ ሄደላችሁ።
አቡነ ጴጥሮስ ለእናት ሀገራቸው ኢትዮጵያ ክብር ሲሉ የሞትን ፅዋ ተጎነጩ።
ምንጭ፦የኢትዮጵያና የኢጣሊያ ጦርነት በጳውሎስ ኞኞ