Get Mystery Box with random crypto!

አንዲት ሴት የገዛችውን የሱፐርማርኬት እቃ በጋሪ ከትታ ወደ መክፈያው ተጠጋች ቦርሳዋን ስትከፍተው | 🦋እራስን ፍለጋ🦋🦋67

አንዲት ሴት የገዛችውን የሱፐርማርኬት
እቃ በጋሪ ከትታ ወደ መክፈያው ተጠጋች
ቦርሳዋን ስትከፍተው ውስጡ ሪሞት ኮንትሮል ይዛ ስለተመለከተ ካሼሪው
አላስቻለውም ጠየቀ "ሁልጊዜ የቲቪ ሪሞት በቦርሳሽ ይዘሽ ነው የምትወጭው?"
"አይ ባለቤቴ ወደ ሱፐርማርኬት አብረን
እንሂድ ስለው ኳስ አያለሁ አልሄድም ስላለኝ ተናድጄ ይዤበት ወጥቼ ነው።
የታሪኩ ጨመቅ(ሞራል)ሚስትህን ሁልጊዜ መሄድ ወደምትፈልግበት አጅበህ ተከተላት...ታሪኩ አላለቀም
ይሄን እየተጨዋወቱ ሳለ ካሼሪው ስቆ እቃዎቹን ወደ መደርደርያው መመለስ
ጀመረ።
ምነው?ምን እያደረግኽ ነው?
ባልሽ ሳይናደድብሽ አይቀርም አሁን በዚህች ደቂቃ ATM ካርድሽን አዘግቶታል የታሪኩ ጨመቅ(ሞራል) የባለቤትሽን ስሜት አክብሪለት ...ታሪኩ አላለቀም
ሚስት ሆዬ ወድያው ከቦርሳዋ የባሏን ATM ካርድ አውጥታ አቀያይራ ሞከረች
አልታገደም። የታሪኩ ጨመቅ(ሞራል) የሴት ልጅን ብልሃት አሳንሰህ አትመልከት
...ታሪኩ አላለቀም
ካርዱ ከተለዋወጠ(swipe) በኋላ ማሽኑ ፒን ኮድ ጠይቆ ትክክለኛው (የባሏ) ስላልገባለት አዲስ ፒን ወደ ስልኩ በመሴጅ ላከ
"እባክዎ ወደ ስልክዎ በመልእክት የላክነውን ፒንኮድ ያስገቡ።ደግመውም
በትክክል ማስገባትዎን ያረጋግጡ" የሚል መልስ ሰጠ።
የታሪኩ ጨመቅ(ሞራል)ወንድ ልጅ ዝንጉ ሲሆን ማሽኑ ይታደገዋል....ታሪኩ
ይቀጥላል
ሚስት ሳቅ ብላ ከቦርሳዋ የሜሴጅ ድምፅ የሚያሰማ ሌላ ስልክ አውጥታ ፒኑን በማስገባት ከፈለች።ለካ እየገበየች ሳለ ባሏ እየደወለ ሪሞቱን እንዳይነዘንዛት
ስልኩንም ይዛበት ነው የወጣችው
የምትፈልገውን እቃ ተረጋግታ "ረብጣውን እየመዠረጠች" ገብይታ ስታበቃ ወደ
ቤቷ ተመለሰች የታሪኩ ጨመቅ(ሞራል) የተናደደች ሚስትህን አትፈታተናት ጉዳቱ ላንተው ነው...ታሪኩ ይቀጥላል
ሚስት ቤት ስትደርስ ባል ማስታወሻ
ፅፎላት መኪናውን አስነስቶ ሄዷል
"ውዴ ስልኬን ብፈልገው አጣሁት ቢሮ ጥዬው ሳልመጣ አልቀርም ላመጣው
ሄጃለሁ። ስጨርስ ኳስ ለማየት ከጓደኞቼ ጋር ማመሻሸቴ አይቀርም እንዳትቆጪ።
የምትፈልጊው ነገር ካለ ደውይ" የታሪኩ ጨመቅ(ሞራል) ባለቤትሽን የት ወጣህ ገባህ ብለሽ አትነዝንዥው
በተለይ ቅዳሜ ማታ!!


@erasnflega