Get Mystery Box with random crypto!

የግጥም ረመጥ✍️

የቴሌግራም ቻናል አርማ abelaaaaam — የግጥም ረመጥ✍️
የቴሌግራም ቻናል አርማ abelaaaaam — የግጥም ረመጥ✍️
የሰርጥ አድራሻ: @abelaaaaam
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 679
የሰርጥ መግለጫ

የግጥም ረመጥ
አንዴ join ካሉ ሱስ የሚያስይዙ ግጥሞች የሚያገኙበት
ስለፍቅር
ስለሀገር
ስለቤተሰብ
ስለሁሉም ጉዳዮች የተገጠሙ ግጥሞችን የሚያገኙበት ምርጥ ቻናል ከግጥም ቻናሉ ያልተስሞሟት ነገር ካለ እንዲስተካከል አስተያየት ይስጡን እናስተካክላለን።
ለአስተያየቶች @SUNMAN111 👈👈 ይህን ይጠቀሙ።
@Abelaaaaam
@Abelaaaaam
@Abelaaaaam

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-16 15:49:29
ንቃት
"""""
የልብ መቅረዝ በርቶ
ነፍስ ሲኖር ለእምነት ቃል፤
በሺ እንቅልፍ መሀል
ልቡ ተቀስቅሶ አንድ ሰው ይነቃል!

ይነቃል...
ከሰመመን ሀሳብ እራሱን ያርቃል፤
የእውነት አታሞ ለዓለም ይደልቃል፤
ይነቃል...
ተስፋን ያ..ሰንቃል...!

ለአብነት

"ተመልከተው ኖህን"
የፈጣሪን ቁጣ ነቅቶ ቢጠረጥር፤
በኃጢያት ህላዌ
ዓለም ሲደነቁር፤
ጎንበስ ቀና ብሎ
መርከብ ሲቆረቁር...
ባበጃጀው መርከብ
ፍጥረትን ሲያሻግር
ወደመኖር ዓለም ጥፋትን ቀልብሶ፤
ግድ የለህም እመን
ንቃት ነው ምድርን ያቆማት መልሶ!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)

@Abelaaaaam
@Abelaaaaam
845 views*Abel# (የቃዬል ወንድም), 12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 15:45:15 ቀስቃሽ የለም

እምዬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ
ትሎች የሚወሩሽ እንደሞተ ገላ
ቀስቃሽም የሌለሽ ዜጋሽም ሬሳ
አይጥ ሚነግስብሽ ተገሎ አንበሳ

ተነሺ ሀገሬ

አቤል ጌታሁን


@Abelaaaaam
@Abelaaaaam
791 views*Abel# (የቃዬል ወንድም), 12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 14:15:45 ትንሽ ብርሀን
እግዜር ሆይ ትንሽ ብርሀን ብትሰጠን
ጨለማዉ ለከት ስላጣ ፥ ስለሌለዉ
መጠን ።

ትንሽ ብርሀን ፥ አለ አይደል
ሚያወጣን ፥ መንገዱን ከጠፋን
ከጨለማዉ ገደል ።
ትንሽ ብርሀን ፥ ለተስፋ እንዲሆነን
አለዚያማ
ተስፋ በሌለበት ፥ መኖሮ
እንዳይደክመን ።

ኬቲኤል
224 viewsEden, 11:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 13:37:33 መዘግየትህን አትጥላዉ !
ነገሮች በፍጥነት እንዲሳኩልህ አትፈልግ !
መዘግየትህን አትጥላዉ ! በትምህርት ፣ በስራ ፣ በሀብት
፣ በፍቅር ግንኙነት ወይ በትዳር
አንተ እንዳሰብከዉ አለመሆኑ
ለበጎ እንደሆነ አስብ ።


ወደ ኋላ የተንደረደረ ረጅም ርቀት
እንደ ሚተኮስ አስብ ፤ ወዳጄ
ጥያቄህ ቶሎ ያልተመለሰዉ ጊዜዉ
ስላልደረሰ ወይ ደግሞ ፈጣሪ የተሻለዉን ሊሰጥህ ይሆናል ።

አንተ ብቻ ጥረትህን ሳታቋርጥ
ታገስ ፤ የህይወትህ
ፀሀይ መዉጣቷ አይቀርም !
191 viewsEden, 10:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 13:37:33 በህይወት ጎዳና አንድ እርምጃ
ወደ ፊት ስትራመድ ብዙ
መንገድ ወደ
ሁዋላ ሊመልሱህ የሚችሉ ፈተናዎች
እንደ ሚገጥሙህ አምነ ተቀበል ።


ለምታገኘዉ ነገር ብቻ ሳይሆን
ላጣኸዉም ነገር አመስግን ። ምንአልባት
ስለማያስፈልግህ ይሆናል ከመንገድህ
ዞር የተደረገዉ ።
179 viewsEden, 10:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 13:37:32 ብዙዎቹ ስኬትን ተኝተዉ ያልማሉ
ጥቂቶች ከአልጋቸዉ ተነስተዉ
በተግባር ያሳኩታል ።


ወዳጄ ተነሳ የነገዉ የሚሳካዉ
ዛሬን ከሮጥክ ነዉ ፤ እህቴ
ከእንቅልፍ መነሳትሽ ወሳኝ ነዉ !

ንብ ብትናደፍም ማሯ ግን ጣፍጭ
ነዉ ፤ ዝምብ አትናደፍም ግን
በሽታ ታመጣለች... በጠዋት መነሳት ምቾት ቢነሳም
ዉጤቱ ግን ጣፍጭ ነዉ ።
171 viewsEden, 10:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 13:37:32 ሰዉን ስታይ ትደክማለህ ፈጣሪን ስታይ
ትበረታለህ ሰዉን ስታይ ትጨነቃለህ
ፈጣሪን ስታይ ትፅናናለህ ሰዉ ይበድላል
ፈጣሪ ይቅር ይላል ሰዉ ያጠፋል
ፈጣሪ ይመልሳል ሰዉ ያቆስላል
ፈጣሪ ያክማል
ሰዉ ተስፋ ያስቆርጣል ፈጣሪ ተስፋ
ይሆናል ።
193 viewsEden, 10:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 13:37:32 መጣላት አለና ፡
ሚስጥር አትናገር ።
መታረቅ አለና ፡
ክፉም አትናገር ።
በዚህ አለም ኑሮ የሚሻለዉ ነገር
ብዙ ማዳመጥ ነዉ
ከብዙ መናገር !!
168 viewsEden, 10:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 13:37:32 ነጻ ዋጋ
ልጅ ወደ ኩሽና ይገባና ለእናቱ
እንዲህ የሚል
ጽሁፍ ፅፎ ይሰጣታል ፦
የግቢዉን በር
ላጨድኩበት .............
50.ብር
በዚህ ሳምንት ክፍሌን
ላጸዳሁት...... 40.ብር
ታናሽ ወንድሜን ከቤት
እንዳይወጣ ለጠበኩት
...... 15.ብር ቆሻሻ
ለደፋሁበት ...... 5.ብር
በድምሩ ............. 110.ብር
ትከፍይኛለሽ

እናቱ ትንሽ አሰበችና
እስኪብርቶን አንስታ እንዲህ
ብላ ፃፈችለት ። ዘጠኝ
ወር ሙሉ
በማህጸኔ ዉስጥ
ተሸከምኩህ...... ያ ለምንም ክፍያ
አማጥኩኝ ፣
ወለድኩህ...... ያ ለምንም ክፍያ
እስካሁን ድረስ
ተከባከብኩህ ፣ አሳደኩህ...... ያ ለምንም ክፍያ አልባሳትህን ፣ የምግብ ፣ የት / ቤትና የመጫወቻ
አሻንጉሊቶችህን ወጪ ሸፈንኩልህ
ያ ለምንም ክፍያ ልጄ በአጠቃላይ
ላንተ ላደረኳቸዉ የፍቅሬ መግለጫዎች ዋጋቸዉ ነፃ ነዉ ።

ልጁ የፃፈችለትን እንዳነበበ አይኖቹ
አቀረሩ ቀድሞ የሰጣት
ወረቀት ላይ ሁሉንም ከፍላኛለች
ብሎ እናቱ ላይ ተጠመጠመባት

<< እናት ባንክ ሆና እኔ ብበደራት ወለድ እየከፈልኩ ዘላለም ላኑራት >>

እናታችሁን ምትወዱ እናታቹህ
ሺ አመት
ትኑርልን
188 viewsEden, 10:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 12:41:25 ያንተ ጥንካሬ !
አይንህ ወደ ብርሀኑ አቅጣጫ ከሆነ ሊጋርድህ የሚፈልግ ጥላ ከኋላህ ያርፋል ፤ ሀሳብ መልካም ነገር ላይ ብቻ ካረፈ መጥፎ ነገሮች አንተ ጋር ሳይደርሱ ከጀርባህ ይወድቃሉ ።


ጨለማዉ ላይ ማፍጠጥ ብርሀን አይሰጥም ፤ ድክመትህን ብቻ አጉልተህ አትይ ! አንተ ባትሆን የማታልፋቸዉ ብዙ ችግሮች ነበሩ ፤ አንተ ግን ዛሬ ደርሰሀል ፤
ወዳጄ አሁን ያለህ ጥንካሬ የምታስበዉን
ሁሉ ለማሳካት ከበቂ በላይ ነዉ !
223 viewsEden, 09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ